God is right

Rahel Fekadu Terefe

                                           ክፍል ስድስት

አይኖች ሁሉ እጆቹ ላይ

ሲያሻው ለንጉስ ፈርኦን እንቅልፍ አብዝቶ ሰጥቶ፡
ሲያሻው ከንጉስ አርጤክስ እንቅልፍን አባሮ አጥፍቶ፡
ከታች እስከላይ አሰልፎ ፡
ቀጭን ትዕዛዝ አስተላልፎ ፡
ባሪያዎቹን ያሰበ ዕለት፡
ወንጀለኛ ተብለው ከተጣሉበት እስር ቤት ፡
የእግር ጆንያ ሆነው ከተረገጡበት መሬት ፡
እንደዮሴፍ ሊያከብር ከከርቸሌ አውጥቶ፡
እንደ መርዶኪዮስ ሊሾም ከትቢያ አንስቶ፡
ይችላል ላመነ፡
እሱ እንደሆነ፡
መሾሚያ መሻሪያ የሀያላን ሁሉ፡
ው በእጁ ነው በክንዱ በሀይሉ፡
 
 
ኢሀኛው መሻቴ

አሁንም አሁንም
እንደልብ ምቴ፡
አሁንም አሁንም
' ይሰጠኝ' ማለቴ፡
ያ መሻቴ....፡
ዲታ ባለፀጋ
መባልን ፍለጋ
እጅግ መዋተቴ፡
አምላኬን አስገርሞ
አሳዝኖ አግባብቶ፡
ምንም ቢያሰጠኝም
ቁና አስሞልቶ፡

በዝቶ እጅግ በዝቶ

ምንም እንኳ ቢሰጠኝ
አዲስ አዲሱ፡
በዝቶ እጅግ በዝቶ
ምንም እንኳ ቢሰጠኝ
ትኩስ ትኩሱ፡

እስቲ ምን ይባላል

ለሰው ሳላካፍል
ሰስቼ ተንገብግቤ፡
በወጉ ሳልበላው
ራሴም እንደልቤ፡
ገና እንደተቀበልኩ
ትኩስ አዲስ ሆኖ፡
አይቼ ሳልጠግበው
በሙቀት ታፍኖ፡
ዜግነት ቀይረ
ሻገተና ቀረ
በእጄ እንዳለ ፈጥኖ።

  ገና ከአንድ

ቀንጭቤ ቀንሼ,
ጨልፌ ቆርሼ,
ቆርጬ ቀንጥሼ,
ዘግኜ ከዘመኔ,
ከዕለት ኑሮዬ
ከጥቂቷ ቀኔ,
እንዲያው በከንቱ
ሰዓቴን ሰውቼ,
ዓላማዬን ስቼ,
ተዘናግቼ,
ለሀጢያት ግፊት
እጆቼን ሰጥቼ,
መገስገሴን ትቼ,
ቆሜ ተገትሬ,
የጨው ዓምድ ሆኜ
እንዳልገኝ ሳይ
ወደ ኋላ ዞሬ,
ገና ከጅማሬ,
ከአሁኑ ከዛሬ,
ከእርጅናዬ በፊት
ወጣት ሳለሁ ጊዜ,
ጌታ ኢየሱስ ብቻ
ይነግሳል ይደምቃል
ይታያል በወዜ,
ብዬ
ምዬ
ራሴን ገዝቻለሁ,
ከቀኔ ላልሸርፍ
በልቤ አስቤያለሁ,
እኔ ወ ስ ኛ ለ ሁ።

                                           መድሀኒት

 

 

 እኛ ቤት ወረርሽኝ ገብቶ;
ሁሉ ሰው ታሞ ተኝቶ;
ለበሽታው መድሀኒት ጠፍቶ;
ሲፈለግ ሲፈለግ ሰንብቶ;
አንድ ግንድ ተገኘ;
እንደውም ከነስሙ
የወይን ግንድ የተሰኘ::

ወዲያው
እንደምንም ብሎ ተነስቶ;
አባዬ ጎትቶ አምጥቶ;
እንደ ነጭ ሽንኩርት በሽታን ሰብስቦ;
የቤተሰብን ህመም እንድያጠፋ አስቦ;
ክር አጥብቆ አስሮ እንዳይበጠስ ፈልጎ;
ወስዶ አንጠለጠለው በሩ ላይ ከፍ አድርጎ::

ግን አልተሻለንም
እንካንስ ሊሻለን ቅዘን በቅዘን;
ሆንን እና አረፍን::

ከራሳችን አልፎም ቤቱ ተበላሸ::
የሚያፀዳው ጠፍቶም ቆየ እንደቆሸሸ::
አባዬም ተስፋ ቆርጦ ዝም ብሎ እንዳለ;
ወንድሜ ከግንዱ ሊበላ ከጀለ;
ከጅሎ ከጅሎ ከጅሎ ከጅሎ;
ምን እንደሆነ እንጃ ብቻ ተወው ችላ ብሎ::

 እማዬና እኔ ግን በአይን ተነጋግረን;
ቀስ ብለን ተነስተኔ ከግንዱ ላይ ከፍለን;
አኝከን አኝከን መድሀኒቱን ዋጥን;
ብታምኑም ባታምኑም ያኔውኑ ተሻለን::

አንድ ቀን ግን አባዬ ስንጠፋበት ሰግቶ;
በርጋታ ሲፈልገን ካልጋው ላይ ተነስቶ;
እኔና እማዬ በመጋረጃው ከለላ;
እጅ ከፈንጅ ተያዝን ከግንዱ ስንበላ::

 
ከዛማ ምን ይወራ;
ምኑ ይወራ;
ምን አለ ያልተሰራ?
ጨሰ አባራው አባራው ጨሰ;
በአባዬ ቁጣ ቤቱ ተተራመሰ::
‘’ውጪ ሄዳችሁ ሙቱ መሞት ካማራችሁ;
እንዴት ብትንቁኝ ነው ይህን መዋጣችሁ?’’
ብሎ ሲደነፋ ሲደነፋ ውሎ;
መሄዱን ቀጠለ ሽንት ቤት ቶሎ ቶሎ::
ከዛ ያጠናን ጀመር እኛን ቀስ ብሎ::

ጥርቅም አድርጎ አፉን እንደቆለፈ;
ደፈራችሁኘ ብሎ እንዳኮረፈ;
እንድችው ሲያጠናን ብዙ ቀን አለፈ::
በሃlላ ላይ ከራሱ እየተከራከረ;
የእኔና የእማዬ በሽታ እንደተሻረ;
አምልጦት በአፉ ራሱ መሰከረ::

እኛም
ቤተሰብ አይደለን የተጎነጎነ?
መድሀኒቱ ሚሰራው ሲዋጥ እንደሆነ;
እንነግረው ጀመር ሁሉ ነጋ ጠባ;
እንወተውተው ጀመር ሲወጣ ሲገባ::

አንድ ቀን
‘’ልጅ ለእናታ ምጥ አስተማረች:
ለራሳ ምንም አታውቅ አስተማሪ ሆነች::’’
ብሎ ተርቶብን ቀልድ ቢጤ ቀልዶ;
ከዛ አኝኮ ዋጠው መድሀኒቱን ወስዶ::
ብታምኑም ባታምኑም ወዶ ሳይሆን ተገዶ;
ያኔውኑ በሽታው ጥፍት አለ ነዶ::

ከዛማ በቃ
እንደነጭ ሽንኩርት ከፍ አድርጎ ማሰሩ;
በሽታን እንዳላስወገደ ነቃቅሎ ከስሩ;
አባዬ ተድቶ ሲገረም ቆይቶ;
ማንንም ሳያማክር በፍጥነት ተነስቶ ;
ያሰረውን ፈትቶ አውርዶ ፈላልጦ;
ለእያንዳንዳችን ሰጠን ከግንዱ ላይ ቆርጦ::

ዛረ እኛ ቤት በዛቷል ደስታና ጤንነት;
በቤተሰብ ሳይሆን በየግል ስለምንወስድ
ያን ብርቱ መድሀኒት::

ልዩ

 

አዝ/ ኢትዮጲያ ሀገሬ…

እጆችሽን የምትዘረጊበት፡

ሰዓቱ ደርሷል እምባ ሚደርቅበት፡

ካፈርሽ ሰላም ይታጨዳል፡

ከወንዝሽ አለም ይባረካል።

 

አያለሁ አዲስ ቀን ከደመናው ማዶ፡

ብርሀን ሲወጣልሽ ጨለማውን ቀዶ፡

የራቁት ልጆችሽ ይሰበሰባሉ፡

እውነትም እግ/ር ሀያል ነው እያሉ፡

ባማሩት መቅደሶች ወንጌል ይሰበካል፡

ህፃን ሽማግሌው ላምላክ ክብር ያመጣል፡

እግዚአብሔርም ቃሉን በተዓምር ያፀናል፡

ሊሰራ ሲወጣ ማን ይቃወመዋል

ማን ይከለክላል።

 

…/አዝ/…

 

እውቀትና ጥበብ ካምላክ የተቸሩ፡

ሀጢያትን ጠልተው ለፅድቅ የሚኖሩ፡

ንዋይና ዝና ከቶ ማይገዛቸው፡

ለፍርድና ለውነት ቅናት የበላቸው፡

ልጆች አሉሽ ገና ተግተው የሚነሱ፡

ስለምስኪኑ መውደቅ ከልብ የሚሳሱ፡

የተገባልሽ ቃል በርግጥ ይፈፀማል፡

አምላክሽ ሊያድንሽ ሊታደግሽ ወጥቷል።

                           ክፍል አራት

     ለግጥምህ ምላሽ

"የሚያስብ ጭንቅላት - ከፈጠርክ በኋላ፣

አትመራመር አልክ - የሰውን ልጅ ሁላ፣

ኩልል ያሉ አይኖች - ለሰው ሰጠህና፣

ግራ አጋባኸው - አትመኝ አልክና፣

አንተ ሆነህ ጠሪው - ስትሆን ከልካዩ፣

እንግዲስ ተውናችሁ"

ብለህ ስትል ሰማሁ "ይስፋችሁ ሰማዩ።"

ግን

የሰው ልጅ ልጄ - ከሰማይ ከምትቀር፣

አይንህ እንዳይመኝ - አሳውርህ ነበር፣

እንዳትመራመር - አደድብህ ነበር፣

በግጥም የፃፍከውን - ይህንም አቤቱታ፣

ባልሰማሁት ነበር

ይድረስ ያልከውን - ለሰማዩ ጌታ።

እኔማ

ራሴን አስመስዬ - አንተን በጅቼ፣

ጠራሁህ ሰው ብዬ - በእጆቼ ሰርቼ።

እኔን እያመለክ - እንድትኖር ተመኝቼ፣

እኔን ምታይበት - አካላት ሰጥቼ፣

ኪዳን ገባሁልህ - ባንተ ተደስቼ።

ግን አንተ

አክብሬ የሰጠሁህን - ሁሉ አበላሽተህ፣

የማይታይ አይተህ - ማይበላ በልተህ፣

አጥር ጥሰህ ድሰህ - ፈርጥጠህ እርቀህ፣

በግጥም በዘፈን

ባገኘኸው ሁሉ - እኔን ተከሳለህ?

ምንም ብታስቆጣም - መንፈሴን አስሬ፣

እንዴት ቃል አጥፌ - ኪዳኔን ቀይሬ፣

ከምድረ ገፅ ላጥፋህ - ንገረኝ በል ዛሬ።

ግን…

በፍቅሬ ከቀለድክ - ቃሌ ከሆነ መለፍለፍ፣

ስምርህ እንደምደሰት - ቁጣዬን ሳሳልፍ፣

ሳጠፋህ አላዝንም

ቁጣዬን ባትፈራ - ቀጥል ስድብ መፃፍ።

 - the first 6 lines not mine 

             ብዕሬና ልቤ

ስለሌላ እየፃፈ - አንተን ከሚያስቸግር፣

ብዕር የያዘው እጄ - ጌታ ሆይ ይሰበር።

ስበር እጄን ስበር - ጌታ ሆይ ስበረው፣

ስለሌላ እንዳይጭር - አንተ ስለማታውቀው፣

ትኩረት ስለማትሰጠው።

ሌላ ነገር ጭሮ - ሰደድ አስነስቶ፣

ሰውን አስቆጥቶ - እርስ በርስ አጋጭቶ፣

ወይ ደግሞ አነሳስቶ - አሳስቶ አስቶ፣

እንዳያሳዝንህ - አንተን እየረሳ፣

ልትሰብረው እጄን - ጌታ ሆይ ተነሳ።

ብዬ ልዩ ፀሎት - አልፀልይም ከቶ፣

መኖር ይከብዳልና - እጅ መፃፍ ተነስቶ።

ግና ምፀልየው - ለእጄ ለበዳዩ፣

ግልብ ልብ አፃፃፍ - እንዲወድቅ ከላዩ፣

በምድራዊ ሳይሆን - እንዲካን በሰማዩ፣

ሀሳብን አፍልቆ - የሚሰጥ ለብዕሬ፣

ልቤ ከውስጥ ያለው - የተሸፈነው ከስሬ፣

ይገረዝ ይፈወስ - ይሰበር ዛሬ።

አላስፈላጊው ወድቆ - አብልጦ እንዲያፈራ፣

ስለአንተ ፅፎ - አንተን እንዲያኮራ፣

ብዕሬ እንዲያከብርህ - አንተን እየፈራ፣

ድንጋይነት ቀርቶ - ስጋ ሆኖልህ፣

ያልከውን ሁሉ እሺ - እሺ ጌታ እንዲልህ፣

ይሰበር ልቤ ይሰበር - እግዚአብሔር በፍቅርህ።

ያኔ
ሲነደፍ በፍቅርህ - ፍቅር ሲይዘው ልቤ፣

እንኩቶ ከማማሰል - ብዕሬን አቅቤ፣

ስለፍቅርህ መፃፍ - ብቻ ይሆናል ሀሳቤ፣

ስለፍቅርህ ብቻ - መፃፍ ይሆናል ግቤ።

                                                       ክፍል ሶስት     
                        
                                ይ ገ ባ ሀ ል

እንደተለመደው፡

ሽማግሌዎች ተሰብስበው፡

ሸንጎ ጀመሩ -በህዝብ ተከበው።

ከፊት ከመድረኩ -ወርቅ ቀረበና፡

"የነጠርኩ እንደሆንኩ -ተመልከቱ ኑና።"

አለ

ብድግ ብድግ ብለው -ሁሉም አዩትና፡

አረጋገጡለት -የሱን ንፅህና።

ከዛም

በሀይለኛ እሳት ውስጥ -ማለፉን ሲሰሙ፡

ከፊት ለፊታቸው -ወርቅን እንዳቆሙ፡

በአንድ ነገር ተስማሙ።

በየሰዉ አንገት በየሰው ጆሮ ላይ- እያንጠለጠሉት፡

"ወርቅ ሆይ ልታይ -ልታይ ብትል አንተ

ይገባሀል" አሉት።

ቀጥሎም በተራው -አንድ የታረደ፡

በግ መጥቶ ቆመ ደሙ እየወረደ።

"ከነገድ ከቋንቋ -ከዘር የዋጃችሁ፡

ይኸውላችሁ ደሜ- አንድ ያደረጋችሁ።"

አለ

ሁሉም አዩትና- ተነስተው አንድ ባንድ፡

አረጋገጡለት- የአንገቱን መታረድ።

ከዛም

ታላቅ ነኝ ባይ ሞትን- ማሸነፉን ሲሰሙ፡

የታረደውን በግ -ፊታቸው  እንዳቆሙ፡

ሽማግሌዎች ሁሉ - አንድ ነገር ተስማሙ።

ዘንባባ ዘንጥፈው እያነጠፉለት፡

"አቤቱ ታርደሀልና - ይገባሀል" አሉት

እየሰገዱለት።

 

                                                         ባመት መጀመሪያ

እኖርበት የለኝ ቤት ተጠግቼ፣
እጠጣው የለኝ ውሃ ተጠምቼ፣
እበላው የለኝ ምግብ ተርቤ፣
እከብርበት የለኝ ክብር ተሰድቤ፣
እለብሰው የለኝ ልብስ ታርዤ፣
አንድም ለመጽደቅ አስቤ - አንድም በችጋር ተይዤ፣
በሀሳብ ናውዤ፣
ናውዤ ናውዤ ናውዤ ናውዤ፣
ሳለሁ -


ካለሁበት አልፋ መሄዷን ሰርዛ፣
እንቁጣጣሽ መጣች ኢየሱስን ይዛ።
ቤት የለ ምግብ የለ፣
ልብስ የለ ምን የለ።
በምን ልቀበለው ብዬ ስንደፋደፍ ሳለ፣
በሩ ሳይከፈት ተቆልፎ እንዳለ፣
እልቤ ውስጥ ገብቶ አካባቢው ሁሉ አመትባል መሰለ።


ታዲያ ምን አለ -
“እንቁጣጣሽ እንኳን ደህና መጣሽ፣
የአለምን ንጉስ ኢየሱስን ይዘሽ።”
ተብሎ ቢጨፈር ከበሮ ቢመታ አበባ ተይዞ፣
ከዛ ደሞ ቢቀር እህል መደፋፋት ቄጤማ ጎዝጉዞ?!

ቄጤማ እሺ ይጎዝጎዝ…
ምናለበት ቢዋል የእንቁጣጣሽ ለት አምላክ ተስተውሶ፣
ሁሌ ባዲስ አመት ባመት መጀመሪያ ጌታ ኢየሱስ ነግሶ?!

                  ይብራ                                                                                                          ብኩርና

 

መች ጨልሞ ያውቃል የአምላኬ ፊቱ

ዛሬስ እንዴት ልበል ፊትህ ይብራ አቤቱ

መታወሬን ሳውቀው አይኔ እንደማይሰራ

ልለምን ሲገባኝ የፈውስ እጁን ልጠራ

ስውሩ የልቤ አይን ቦግ ብሎ እንዲበራ

ዛሬስ እንዴት ልበል አቤቱ ፊትህ ይብራ።

 

 

 

የምስር ወጥ በልቶ

ጠግቦ አገሳስቶ

ከማዕድ ቤት እንደወጣ

ብኩርናውን እንዳጣ

አላወቀም ኤሳው

ኤሳው ግድየለሹ

በእጁ እንዳስገባው

ያዕቆብ ታናሹ።

            እኛና ሰይጣን                                                                                                   መንገድ

 

ስንቆሽሽ ተጠርተን ታጥበን በደም ዕዳ

እኛ ስንዘንጥ መልሰን ስንፀዳ

ሰይጣን ግን ይላካል ወደ እሳት ገንዳ።

የሱ ስለማይለቅ ካልተዘፈዘፈ

ዘለዓለም ካልኖረ እሳት እየላፈ።

 

   

መንገዶቹ በዝተው እየተጠላለፉ

እዛው ነዋሪውን ተሳስረው ካስለፉ

ከውጭ ከገጠሩ የሚመጡትማ

እንዴት ነው የማይጠፉ።

ግን አንድ መንገድ አለ በእጅ ያልተሰራ

ወደመንግስተ ሰማይ ቀጥ ብሎ የሚያመራ።

                                                                                  ስለስሙ

ድካማችሁ የወደቀ

ወገባችሁ የታጠቀ

መብራታችሁ የበራ

ህይወታችሁ የጠራ

ይሁን ተብሏል

አንበል ሲሉት ይቀላል።

                    Big

He is so big, I want to cry.

He never leaves me, I wonder why.

I tried so hard, to push him away.

But in my tiny mind,

He becomes big, unshakably.

                       Why?

                      Why? Why? Why?

                      Like the sky,

                      He is so high,

                      Like the earth,

                      Thick was his strength.

 “Why?

Why? Why? Why?”

I used to say all yesterday.

Until I come to understanding,

There is a bigger big,

To this horrible thing.

             No matter how it may seem coward,

            “My problem” I firmly said.

             “Your big nesses now totally freeze,

             You are not big, but my God is.

             You tried hard, to cover God,

             To make my life, a living dead.

              I was colonized by your strength,

             Till Big God broke your teeth.

 You mountain now move away,

God is so big in my life today,

If God allows, you may choose to stay,

But give you attention, never will I.

Bye bye bye bye”

                                            ክፍል ሁለት                     

ቱ…ቱ…ቱ

የውበትህን ቀመር ለፍጥረት እንዲያስረዳ፣

የሾምከው አዘማሪ ዜማ እንዲቀዳ፣

ሱሰኛ ሆኖብህ በውበትህ ተለክፎ፣

ታላቁ መልአክ ተደናቀፈብህ - በቅናት ተጠልፎ።

ብዕር አይገልፅህ ብሩሽ አይገልፅህ፣

ዜማ አይገልፅህ ተውኔት አይገልፅህ።

ብቻ…

በውበት መግነንህን በአይኖቹ ያየ፣

ሚፈጥረውን ስሜት ሲያጣጥም የቆየ፣

እንዳላየ ሆኖ ዝም ስለማይል፣

ለራስህ ቢያስቅህ የቱን ያህል ቢቀል፣

እኛ በአማርኛ በምናውቀው ቃል፣

…በምናውቀው ፊደል፣

ቱ…ቱ…ቱ ከአይን ያውጣህ

ከአይን ያውጣህ ብለናል።

 

ምላስ

ለአይን መነፅር ያዙለታል፣

ምላስንስ ምን ያደርጉታል?

ከሆነ ጥያቄዎ፣

የሚያስጨንቅዎ፣

መፍትሄው በእጅዎ።

ማለትም

ለአይንዎ መነፅር ሲሰጡ፣

ምላስዎን በጥርሶ ይርገጡ።

 

ለምን

ማልቀስና መሳቅ የአንድ ኢትዮጲያዊ ፣

ዲሞክራሲያዊ መብቱ ነው ህገ-መንግስታዊ።

ታዲያ…

እየሳቁ ለቅሶ የሚቻል ከሆነ፣

እያለቀሱ ሳቅ ለምን ተኮነነ?

 

እሷ

ብዙ ተምሬያለሁ ብላ የምትል ነፍስ፣

በድንጋይ መበለጥ የማትወድ ነፍስ፣

ያዳም ዘር እንደዛፍ ቆሞ ሲተነፍስ፣

እሷ ያለይሉኝታ ወዳምላኳ በርራ፣

ብዙ ታረግዳለች መቀነቷን አስራ።

ያያል

ባራኪው ሸምግሎ፣

አያይም ተብሎ፣

የበግ ለምድ ተለብሶ፣

እጅን አስዳስሶ፣

እንደያዕቆብ አታሎ፣

በረከት ቆልሎ፣

መውጣት አጭበርብሮ፣

የለም ዘንድሮ።

ስለዚህ እንዳታፍር፣

ስምህን ሳታስቀር፣

የሆንከውን ተናገር።

ምን ቢሸመግል አልታወረምና

እንደይስሀቅ እግዚአብሔር።

 

ሆሳዕና /አቤቱ አሁን አድን/

 ለምንድን እላለሁ ጌታ ሆይ ቶሎ ና፣

አዲስ ነገሮችን ሳላጣጥም ገና።

እዛጋ አይታችኋ? ቆንጆ ካፌ አለ፣

እንድንዝናናበት ተብሎ የተተከለ።

ቀለበት መንገዱም ይኸውና አለቀ፣

ብዙ ብር ፈሶበት ተጠናቀቀ።

አይታችኋል ንድፉን አምሮ እንደተሰራ?

ፎቶ ሳልነሳበት …

ጌታ ሆይ ና ብዬ እንደምን ልጣራ?

በቤት ኪራይ ብዛት የተማረራችሁ፣

ይኸው ኮንዶሚኒየም ድርድር አለላችሁ፣

ሁሉም ይደርሰዋል ትዕግስት ይኑራችሁ።

ቆይ እንጂ እንደሰት በተጠን ጊዜ፣

የምንድን መፍዘዝ ነው ደርሶ በትካዜ፣

ጌታ ይመጣል በሚል አጓጉል አባዜ?

ለማንም አይቀርም ታላቁ ሞት እንደው፣

ዛሬን ብንዝናና ነገን እረስተነው ክፋቱ ምንድን ነው?

ህምምም…

ይህኛው ከላይኛው አይወዳደርምና፣

እኔ ግን እላለሁ ጌታ ሆይ ቶሎ ና።

ሂወት ነኝ ብለሃል አቤቱ አሁን አድን፣

የሞትን ክንፍ ሰብረህ ታደግ ፍጥረትህን፣

አዎን ማራናታ አባ ቶሎ ናልን።

 

 

                                                       ክፍል አንድ                    

 ግባ

ታፀዳለህ ሲሉ ያደፈ የቆሸሸ፡ 

የተመሳቀለ የተበለሻሸ፡

ተስፋ አርጌ መጣሁ ወዳንተ አንድዬ፡

የተጎሳቆለች ነፍሴን አንጠልጥዬ።

እንጃ …

ከየት እንድትጀምር ባይገባኝም እኔ፡

ተቀብዬሃለሁ የልቤ ቁልፍ ይኸው

ግባበት መድህኔ።

 

ተረፈው

ተዘንግቶት ኑሮ ካፈር መለወሱ፡

መጨቅየቱን ጠልቶ ፂቅ ቢል መላሱ ፡

የጭቃው ማስጠላት እግሩን እንዳይነካ፡

የጫማውን አናት መሬት እየሰካ፡

ላለመርገጥ ብሎ ለእግሩ ቢጠየፈው፡

ሚዛኑን አጥቶ ተንሸራቶ ወድቆ

ለቂጡ ተረፈው።

 

 

 

ቀንዶቹ 

ሰብስቤ ስበትን የምስጋና ጥርጥር፡

እንዳላየ ሆኖ የቱን ያህል ቢጥር፡

ጠቆር ጠቆር ብለው ቀስ ቀስ እያሉ፡

እግምባሩ ግድም ቀንዶች ቢበቅሉ፡

ጊዜ …

በስውር በሽሽግ በእኔ እንዳረረ፡

መደበቅ አቅቶት ሰይጣን ተፎገረ።

  

 

 

 እንፋሎት    

 እሳት ላይ ያለውን ድስት ሲከፍቱ፡

ግልብጥ ብሎ ወጥቶ ሙቀት እንፋሎቱ፡

አየሩ ላይ ታይቶ ደምቆ ለአንድ አፍታ፡

ሽቅብ እየሄደ በፍጥነት በዝምታ፡

ደግሞ ድርግም እንደሚል ያለንግግር ያለገለጣ፡

እንዲህ ናት የኛም ነፍስ ከስጋችን ስወጣ።

በቃ አበቃ።

 

 

 

  

ኳስ 

 አምሬ ወፍሬ ስወጣ ከቤቴ፡

ኳስ መስዬው ብቻ ሲያየኝ ጠላቴ፡

ተታሎ በምቾቴ፡

(ምፅ) እግዚአብሔር አባቴ፡

ሲሳይ ሆኜ እንዳላርፍ ለሸፋፋ እግሩ፡

አስበኝ በመልካም አስበኝ በጥሩ።

(ምፅ) ኢየሱስ ብትወድስ፡

ጠላቴን እራሱን ቀይረው ወደኳስ፡

በሃይል እንድለጋው ጅማቱ እስኪበጠስ።

 

ድህነት 

ያፋቅራል ሲሉ ሰዎች ሰማሁና፡

ማፋቀርን ልማር ወደሱ ባቀና፡

ሁለት እግሬን ይዞ ወፌ ላላ አስሮ፡

ገልብጦ ቀጥቅጦ ውድ ቅስሜን ሰብሮ፡

ዠልጦ ዠልጦ ጀርባዬን አሳብጦ፡

ድህነት ለቀቀኝ አጣሞ አጉብጦ።

እግዚአብሔር ይይልህ አንት አሳፋሪ፡

ደርሶ ጥሩ መሳይ ደርሶ አፋቃሪ።

 

የኔስ ገዳይ 

  ልብ ይሟሟል ወይ እረ እስቲ ንገሩኝ፡

ነፍስስ ይፈሳል ወይ እረ እስቲ ንገሩኝ፡

ነፍስ ፍስ የሚያደርግ ከፍታ ወጥቼ፡

ልብ የሚያሟሟ ሙቀት ውስጥ ገብቼ፡

ሀውልት ሆኜ እንዳልቆም ኢየሱስን አይቼ፡

የያዝኩትን ሁሉ ዘፍ አርጌ ጥዬ፡

በቃ ራሴን ሳትኩ ተልፈስፍሼ ወደቅኩ

ሙት ሆንኩ ተቅልዬ።

 

 ፖለቲከኞቻችን

ጎራ እየለዩ ፡

ጎሪጥ ላይተያዩ፡

ርቀው እየቆሙ፡

ሲቀርቡ ላይላተሙ፡

ፖለቲከኞቻችን

አየሁ ሲሳሳሙ።

 

ማናችን ማናቸው

  ልዑልን በሀይሉ ቅዱሱን በዙፋኑ፡

ለማየት የሚጓጉ ለማየት የሚቀኑ፡

እንደኤሊ ልጆች አውራ እንደነበሩት፡

ማናቸው አስናቁት ማናቸው አስደፈሩት፡

በቤቱ እየተጉ ሲዳሩ እንደሚያድሩት።

 

የኛ ሰርቢ

ወባ እንደያዘው እየተርገፈገፈ፡

እንዳበደ ውሻ እየተክለፈለፈ፡

የሚሄድ

አራት እግሮች ያሉት አፅም ሆኖ ሳለ፡

ከመኪኖች እኩል የኛም ሰርቢሳችን

መኪና ተባለ።

 

ምስረታ 

በጎበዞች ስብስብ በገንዘብ ብልጫ፡

እንደእግር ኳስ ክበብ በሚችሉ ፍጥጫ፡

አትመሰረትም ቤተ ክርስቲያን ከቶ፡

ከላይ ከፀባኦት ፊሽካውን ካልነፋው

እግዚአብሔር ተነስቶ።

ተቀልባሽ 

ስሟማ ነበር ጭራ ተቀጥላ፡

ጉድ የምትሸፍን ከወደኋላ፡

ግና ገመናን አወጣች አርክሳ፡

የፍየል ጭራ ወደላይ ተቀልብሳ።

                                           - lidia

ዘአመነ  ዘአመለጠ 

ፃድቅ ለመሰለ፡

ሽር ብትን ላለ፡

ላሸረገደ ፡

ላረገደ፡

ለወጣ ለወረደ፡

አይደለም አይደለም፡

አይደለማ

አ… ይ…ደ…ለ…ም።

ምህረት ለወደደ

አይደለም ለሮጠ፡

ከሚምር እግዚአብሔር

አንድ ልጁ ተሰጠ።

ዘአመነ  ዘአመለጠ።