God is right

Rahel Fekadu Terefe

                                                        አይ እኛ

አሁንም አይኔን አላመንኩም። ጋጣ ውስጥ ያሉትን በጎች ሳይ በጣም አንሰዋል። ተሳስቼ ይሆናል ብዬ መቁጠር ጀመርኩ። አዎ ቁጥራቸው አንሷል። የለም እንደገና መቁጠር አለብኝ ብዬ ቆጠርኩ። በትክክል የተወሰኑ በጎች ጎለዋል። እንዴ? እንዴት ሊሆን ይችላል? አንጋፋዎቹን በጎች ስለሁኔታው ልጠቃቸው ከበሩ ዘለቄ ወደ መሀል ገባሁ። ኦ! ገበያ የገባሁ ነው የመሰለኝ። እኑካ የተባለችውን ጠጋ ብዬ

"አንቺ የጠፉ በጎች አሉ መሰለኝ" ስላት አየት አርጋኝ ዞረች። ባለፈው የተሰበረው እግሯ በወጌሻ ተጠቅልሎታላል። እስካሁን አልተሻላትም። የመጣሁበትን መጠየቅ ትቼ እሷን ማፅናናት ገባሁ። ጋጣ ውስጥ ያለው ረብሻ ግን እንዴት እንደቻለችው አልገባኝም።

"አይዞሽ እኑካ ነገር ሁሉ ለበጎ ነው" ስላት በፍራት ነበር። አንቺ መች አየሽውና ነው...መች ይገባሻል የምትለኝ መስሎኝ ነበር። ግን እኑካ ፊቷ በደስታ በራና "አሜን ዛንዚባርዬ" አለችኝ። ያለ አንዳች ማስጠንቀቂያ ከሷ ጎን ያሉ አውራ በጎች ቴስታ መጋጨት ሲጀምሩ ጋጣው ቀውጢ ሆነ። አንዳንዱ "ድብድብ ድብድብ" እያለ ይጮሀል። አንዳንዱ ራሱን ለማዳን ጥሩ ወደ መሰለው ቦታ ይሮጣል።

እኔ ምንም አልገባኝም "ጋጣው ውስጥ እንዴት ይደባደባሉ" እያልኩ እያሰብኩ ድንገት ከየት መጣ ሳልለው አንድ ቴስታ ራሴ ላይ ሲያርፍ አቅሌን ስቼ ወደኩ። በሰመመን ሆኜ በጎች ከበውኝ ይታየኛል። በርግጥ አልሞትኩም ምክንያቱም ከላይ የጋጣው ጣሪያ ይታየኛል። "የጠፉ በጎች አሉ..." ጥያቄዬን ልጨርስ አልቻልኩም። እንቅልፍ ይዞኝ ጭልጥ አለ።

ጫጫታ ሰሰማ ነቃሁ። "እረኛችን መጣ የስ" ምናምን እያሉ የሚንጫንጩ በጎችን አየሁ። ተንጠራራሁና አካባቢዬን ስቃኝ ሁሉም ነገር ትዝ አለኝ። አንድም ሊደግፈኝ ከአጠገቤ ቆሞ የጠበቀኝ አላገኘሁም። ዳሩ እኔም ምንም አልመሰለኝም። ብቻ ግን እረኛችን መምጣቱን ስለሰማሁ ልቤ ተንቀዠቀዠብኝ።

የጋጣው በር ተከፍቶ በጎች ሁሉ እየሮጡ ወደእኛ እየመጣ ወዳለው እረኛ ለማምራት ሞከሩ። እኑካ በደስታ ተሞልታ እያነከሰች ስትሮጥ ላግዛት ብዬ ወደ እሷ ተጠጋሁ። እሷ ግን ተቆጣችኝ።

"ሂጂ እደርሳሁ። ይልቅ ማንም ሳይቀድምሽ ሮጠሽ ተጠምጠሚበት" አለችኝ እየገፋችኝ። እንደዛ ስትለኝ ደስ አለኝ።

"እወድሻለሁ እኑካ" ብያት ወደእረኛችን ለመድረስ አስቂኝ ፍርጠጣ ፈረጠጥኩ። ልክ ስደርስ ትንፋሼ እየተቆራረጠ ነበር። ሌሎቹም ከእኔ እኩል የደረሱ በጎች ነበሩ። ሁላችንንም እያነሳ አቅፎ አሻሸን። የኔ ተራ ሲደርስ ብድግ አርጎ ኢየሱስ አቀፈኝ።

"ኢየሱስ ኢየሱስ" እያሉ ሁሉም በግ ይንጫጫል። እኔም በልቤ የነበረውን ጥያቄ ነገረኩት።

"ጌታ ኢየሱስ ...በጎች ጎለዋል። የጠፉ በጎች አሉ። ቡርኖን አላየሁትም እስካሁን። እጠፋለሁ ብሎ ሲዝት ነበር። አደረገው ማለት ነው። ጅብ አይበላውም እንዴ ኢየሱስዬ?" አልኩ ትንፋሼ እየተቆራረጠ። እረኛ ኢየሱስ ፊቱ ሲለዋወጥ ታየኝ። ከዛ ቀስ ብሎ መሬት ላይ መልሶ አቆመኝ።

ወዲያው እኑካ እየሳቀች ደረሰችና ሁላችንም በፍቅር ሄደን አቀፍናት። ኢየሱስም እሷን እቅፍ አድርጎ ከአሻሸ በኋላ ወጌሻ የታሰረላትን እግሯን በእጆቹ ዳሰሰው።  በኋላም እኑካን ጋሪው ላይ ጭኖ በአንድ እጁ ደሞ አንዲት አዲስ የተወለደች በግ እንዳቀፈ እኛን አልፎ ወደፊት ሄደ። እኛም ተከተልነው። ሁሉም በግ የጠየቀው መልስ እየተሰጠው ነው። የኔ ጥያቄ ግን የነቡርኖ መጥፋት ሆነና ምላሽ ወዲያው ላገኝ አልቻልኩም። ብዙ ጥያቄ በውስጤ ነበር።

ምን አገባኝ! እረኛው ካለ ሁሉ ደህና ይሆናል። እሱ የሚያረገውን ያውቃል ስል አሰብኩ። የለመለመ መስክ ላይ ስንደርስ

"እዚህ ቆዩ" አለና እረኛችን ከመካከላችን አልፎ ሄደ። እኔ ይህን ጊዜ ኩልል ብሎ የሚወርደውን ውሀ ልጠጣ ወደዛ ሄድኩ። እየጠጣሁ ሳለ በውሃው ተንፀባርቆ የታየኝ ነገር ግን አስበረገገኝና ቀና አልኩ። ወደኋላ ዞር ብዬ ተራራውን ሳይ ተኩላዎች እኛን እያዩ ቆመዋል። ወደ ኢየሱስ ሳይ ገና ርቆ አልሄደም። ስሮጥ ወደሱ ሄድኩኝ።

"ኢየሱስ...ተኩላዎችን አይተሀል?"

"አዎ"

"እኔ ፈራሁ"

"አትፍሪ። ምንም ማድረግ እንደማይችሉ አንቺ ጠንቅቀሽ ታውቂያለሽ"አለኝና ዞር ብሎ በእጆቹ ዳሰሰኝ። ይሄኔ የልብ ልብም ተሰማኝ።

"ይልቅስ ወንድምና እህቶችሽን ጠብቂያቸው። መጣሁ እነቡርኖን ልመልስ ልሂድ።" አለኝ።

"እሺ ኢየሱስዬ" ብዬ ከእረኛዬ ተለይቼ ወደ ለመለመው መስክ ሳቀና ተኩላዎቹ አሁንም እያዩኝ ነበር። ምን ታመጣላችሁ በሚል ጭራዬን ወዘወዝኩባቸው። ተኩላዎቹ ተናድዱ መሰለኝ እርስ በርስ ተያይተው አካባቢውን ጥለው ሄዱ።

ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን ፍርሀት ፍርሀት ይለኝ ጀመር። ተኩላዎቹ ቢመጡብንስ ብዬ አጉል መጨነቅ ጀመርኩ። እዚሁ ተራራው ላይ እያየኋቸው ቢቆዩ ይሻል ነበር ስል አሰብኩ። እኑካ ስለ ተደረገላት ተአምር ገድል እያጫወተችን ሰብሰብ ብለን የተወሰኑ በጎች ተቀምጠናል። ኮሽ ባለ ቁጥር የምበረግገው እኔ ብቻ ነኝ መሰለኝ። በገዛ መደናገጤ አፈርኩ። አንዱ ኮሽታ ግን በጣም በቅርብ የሚሰማ ኮቴ ሆነብኝ። ትንሿን ጆሮዬን ቀጥ አደረኩና አዳመጥኩ። እነ እኑካ ነገር አለማቸውን ረስተው በውይታቸው ተጠምደዋል። አውራዎቹ በጎችም እኛ ያንበት አካባቢ የሉም። ኮሽኮሽታው ድምፁ እየጨመረ መጣ። እንዴ? ተኩላ ማንኛችን ዘሎ ሊበላ ነው ብዬ ብድግ አልኩ።

"ምነው ዛንዚባር ምስክርነቴ አልተመቸሽም?" አለች እኑካ ስነሳ አይታኝ።

"እረ በጭራሽ። ትንሽ ደክሞኝ ነው። መጣሁ" አልኩና ዘወር አልኩ። ፍርሀቴን ላጋባባቸው አልፈለግኩም። ደግሞም እነሱን የመጠበቅ ሀላፊነት አለብኝ ብዬ እያሰብኩ ኮሽኮሽታው ወደሚሰማበት አቅጣጫ በዝግታ አመራሁ። ድንገት አንድ አካል ከላይ ብቅ ሲል የድንጋጤዬ ብዛት ወደኋላ ልወድቅ ምንም አልቀረኝም ነበር።

እረኛችን ነበር። ኢየሱስ እረኛችን። እሱን ስናይ ሁላችንም በደስታ"እንኳን ደህና መጣህልን" ልንለው ወደሱ መጠጋት ጀመርን። ሆኖም ሌሎች ስድስት በጎች ከእሱ ኋላ ተከትለውት ሲመጡ አየሁ። ሳያቸው ላይ ላዩን ደስ አለኝ። ላይ ላዩን ቦረቅኩኝ። ላይ ላዩን ዘለልኩኝ። ብዙም ሳይቆይ ኢየሱስ

"ቡርኖን ፍለጋ እንደገና እሄዳሁ።" አለ። ይህን ጊዜ በግልፅ ከፋኝ። ለእኛ በቂ ጊዜ ሳይሰጠን የጠፉ በጎችን ፍለጋ ሁሌ መንከራት ምን ማለት ነው? የነቡርኖ አይነት አቋም የለሽ በጎች ቢመጡም በግ አይሆኑም። ሌላ በግ ይዘው ነው በዛው የሚኮበልሉት። ልባቸውን ራሳቸው ካላረጋጉ ታዲያ ማን እንዲያረጋጋላቸው ነው የሚፈልጉት? ስል አኮረፍኩ።

ጌታ ኢየሱስ ነገሬ ቢገባውም አልተቆጣኝም። ግን ደግሞ የጠፋውን በግ ፍለጋ አሁንም ከመሄድ እግሩን አልከለከለም። በእጁ ዳሰሰኝና ሩቅ ቆመው ወደነበሩት አውራዎቹ በጎች አምርቶ ከእነሱ ጋር ጥቂት አወራ። ከዛም ሄደ። ፍለጋ የለመደው እግሩ ዛሬም ወጥቶ ሄደ። አይኖቼ የጠፉትን መፈለግ የማይሰለቸውን እረኛዬን ሊሸኙ ተከትለው ነጎዱ። ለነገሩ አልኩኝ መልሼ በቆምኩበት። የጎደለብኝ ነገር አንዳች የለም። ፍቅር አልጎደለብኝ። ደስታ አልጎደለብኝ። ሰላም አልጎደለብኝ። ምንም አልጎደለብኝ...ታዲያ ምን አይነት ራስ ወደዳድነት ነው ጌታ ኢየሱስን ለራሴ ብቻ ማለት?  ከየት ተማርኩት? ብዬ ራሴን ወቀስኩ። ተፀፀትኩ። ቡርኖም ያለሞት በሂወት እንዲመለስ ተመኘሁለት። አይ እኛ በጎች...

                                                                                     ፍ  ፃ  ሜ

This next is a fantasy short story which is a form of fiction based on imaginative or fanciful characters and premises. (according to literature)

 መጨረሻው ሰዓት

ጠርቃቃ ውስጥ ሳያስበው ገብቶ በጣም ጨንቆታል። መተንፈስ እያቃተው ዙሪያ ገባውን ለማየት ታተረ ግን ድቅድቅ ጨለማ ነው። እግሮቹና እጆቹን እንዳሻው ማንቀሳቀስ አልተቻለውም። ድንገት ድም … ድም … ድም የሚል ድምፅ ጆሮው ላይ በሀይል ጮኾ አስተጋባና መልሶ ዝም አለ። ምን እየተከናወነ እንደሆነ ለማወቅ እሱም መታገሉን አቁሞ አዳመጠ። ፀጥ ረጭ ብሏል። ወዲያው የእድር ቤት ጥቅርሻ አረንጓዴ ወፍራም ድንኳን ከመሰለው ጭብጥ ያለ ነገር መውጣት ጀመረ። እንዴት እንደሆነ ባያውቀውም አጨናንቆት ከነበረው ድንኳን ራሱን አላቀቀና ወገቡን ይዞ ቆመ። አዳፋው የእድር ቤት ድንኳን የሚመስለውን ነገር እያየ እየሆነ ያለውን ነገር ለመረዳት ጥቂት ቆየ። ሌላ ሁለት አካላት ከጎኑ መኖራቸውን ያወቀው አንዱ አካል ሲናገር ነው።

 "እንሂድ" አለ አንደኛው አካል። በዚህን ጊዜ ሁለቱም አካላት የባዬን ክንዶች ይዘው ብድግ አሉ።

"ቆይ… ቆይ…" አለ ባዬ አግራሞት በተሞላበት ድምፀት። ሁለቱ አካላት ግዙፎች ነበሩ። ከሱ በጣም ይገዝፋሉ።

"በመጀመሪያ ደረጃ እናንተ እነማን ናችሁ? ጊዜ ስለሌለኝ የትም መሄድ አልችልም። ብዙ ስራ ይጠብቀኛል። እና ቶሎ ቶሎ ጉዳያችሁን አስረዱኝ።" አለ ትኩረቱን ሁሉ በእነዚህ ሁለት አካላት ላይ በማድረግ።

"ባዬ… አንተ አስተዋይ ሰው ነህ። የእኛን ማንነት ላንተ መንገር አያስፈልገንም።" አለ አንደኛው አካል።

"መላዕክት ናችሁ?" አለና ባዬ ሁለቱን መላዕክት እያፈራረቀ ሲያይ ቆይቶ የራሱን አካል ለማየት ራሱን አዘነበለ። ማመን አልቻለም። በፍፁም ማመን ተሳነው። በፍጥነት ሁለት እጆቹን አንስቶ ጭንቅላቱ ያዘ።

"ሞቻለሁ እንዴ? ሊሆን አይችልም። ሊሆን አይገባም።" አለ ባዬ።

"እንሂድ" አለ አንደኛው መልዓክ። መላዕክቱ የባዬን ክንዶች ያዙና ወደላይ መንሳፈፍ ጀመሩ። ባዬ ቀስ እያለ ሁሉም ነገር ግልፅ እየሆነለት መጣ። የማስታወስ ችሎታው እንዳለ ነው። ጥቂት የስሜት ህዋሳቶቹ እንዳሉ አሉ። ያሸታል፣ ያዳምጣል፣ ይናገራል፣ በደንብ ያያል።  ሞት እንዲህ ነው? በቃ? ዓላማዬን ሳላሳካ . . .

 ወደላይ ከፍ እያሉ እየሄዱ ቢሆንም ከስር ያለው ነገር ሁሉ ግልፅ ሆኖ ይታየዋል። የሰው ሰዓት አቆጣጠር አሁን እንደማይሰራ ተገነዘበ። የቦታ አገላለፁም ምድር እንደሚያውቀው አይደለም። በምድር ላይ እየተከናወነ ያለው ነገር እንዴት እንደሆነለት ባይገባውም ይታየዋል። የኢትዮጲያ ህዝቦች፣ መሪዎችና ቤተሰቦቹ በሱ ሞት ልባቸው ተሰብሮ በእምባ እየተራጩ ነው። ዙሪያ ገባውን ተመልክቶ ኢትዮጵያ አዝና እንዳለች አወቀና "አይ አንቺ ኢትዮጲያ" አለ። ከዛ ደግሞ የኢትዮጲያን ዳር ዳር ተከትለው የከበቧትን ነገሮች አየ። አጥርቶ ለማየት ሲሞክር እንስሳቶች መሆናቸውን ተረዳ። ጥቋቁር ጅቦችና አመዳማ ተኩላዎች ድምፃቸውን እጥፍተው በኢትዮጲያ ዙሪያ ቆመው አየ። ብዙ የጅብና ተኩላ መንጋ። የሚጠብቁትን ነገር ለማወቅ እሱም እነሱ የሚያዩትን ነገር ሊያይ አይኑን ወረወረ። ግዙፍ ዘንዶ ጅቦቹና ተኩላዎቹን "ቀጥሉ" ለማለት በተጠንቀቅ ቆሞ አየ። ዘንዶው ጀሌዎቹን ጀምሩ ለማለት አመቺ ጊዜ እየጠበቀ እንዳለ አወቀበት። እንዴ ይቺ ኢትዮጲያ ስንት አይነት ጠላት ነው ያለባት? ጅቦችና ተኩላዎች? ምን ማለት ነው? ሲል አሰበ።

 ድንገት የእሪታ ድምፅ ሲሰማ ወደዛ ዞረ። ባለቤቱ ጂቱ ነበረች። በጣም አዝናለች። ራሷን ሳያማት አይቀርም። ያለማቋረጥ ታነባለች። ተጎድታለች ሲል አሰበ። ሆዱ ተላወሰ። የሚወዳቸውን ልጆቹን ሲያይ ጊዜ ግን የአባት አንጀት ሆኖበት አለቀሰ። ልቡ ተሰበረ። እምባው እየወረደ ህዝቡን ተመለከተ። ህዝብ ሁሉ ሙስሊም ሳይል ክርስቲያን ሳይል በእምባ ይራጫል።  ዋይታው እዬዬው ፈጣሪን ለመጥራት ይመስላል። "አይ አንቺ ኢትዮጲያ … ግን ጊዜዬ እኮ ገና ነው። እኔ ታጋይ ነኝ አይደለም? ታጋይ ደሞ ተስፋ አይቆርጥም። ለሞት እጅ አልሰጥም" አለና አሰበ። ከዛ መታገል ጀመረ።

 "መልሱኝ በአሁን ሰዓት እኔ አልሞትም፤ መልሱኝ" አለ ባዬ።ሆኖም የሚሆን አልሆነም።

"ለዚህ ምስኪን ህዝብ ሂጄ መንገር አለብኝ። ጅቦችና ተኩላዎች እነሱ ከማያዩት አለም ጠላት ሆነው እንደተነሱባቸው ላስጠንቅቃቸው። ዘንዶ እንደተነሳባቸው ልጠቁማቸው።" አለ ባዬ በሀዘን ተሰብሮ ቅጭም ብሎ።

"አንተን የፈጠረና ለህዝብህ ንጉስ አርጎ የቀባህ እግዚአብሔር ሌላ ሰው አዘጋጅቷል። እሱ ይነግራቸዋል። አንተ የዘመንህን ቁጥር ሞልተሀል።" አለ አንደኛው መልዓክ። ባዬ ዝም አለ። ከነዚህ መላዕክት ጋር ግብግብ እንደማያዋጣ ገብቶታል።

"የት ነው ግን የምትወስዱኝ? እናንተ ማናችሁ? ክፉ መላዕክት ናችሁ? ደጎቹ?" አለ ባዬ። መልስ የሰጠው አልነበረም። ስለዚህ ኢትዮጲያን ወደማየት ብቸኛው አማራጭ ተመለሰ። ለአፍታ ከመብረር አልቦዘኑም።

 ባዬ ኢትዮጲያን ዝቅ ብሎ እያየ ሳለ ዘንዶው ዙሪያን የቆሙትን የአውሬ ሰራዊት "ተዘጋጁ" ሲል ሰማ። ጅቦቹ በመቋመጥ አሽካኩ፣ ተኩላዎቹ አላዘኑ። ተንጫጩ። ዘንዶው ምልክት ሲሰጣቸው መቋመጣቸውን ሳይቀንሱ ዝም አሉ። ነገር ግን ማጥቃት ከመጀመራቸው ፊት ድንገት ካልጠበቁበት አቅጣጫ ግዙፍ የእሳት ኳስ እነሱ ላይ ተወረወረ መሀላቸው ሲያርፍ ረብሻ ሆነና ሁሉም በመዝለል ስርዓት ማጣት ያዙ። ቀጥሎም የእሳት ፍላፃዎች ከኢትዮጲያ ምድር በሀይል፣ በፍጥነትና በብዛት እነሱ ላይ መዝነብ ጀመረ። ባዬን ይዘው ይበሩ የነበሩ መላዕክት ቆም ብለው የሚሆነውን አዩና ተያዩ። ተያዩ። ከዛ ሁለቱም በአንድ ድምፅ "መጨረሻው ሰዓት" አሉ።

 ባዬ አልገባውም። ብዥ ብሎበታል። የሚያየው ነገር የልቡን ትርታ ጨምሮበታል። የእሳቱ ፍላፃ መዝነቡን ያለማቋረጥ ቀጥሎ ሳለ ጅቦቹና ተኩላዎቹ ነፍሳቸውን ለማዳን አይናቸውን እንደታወሩ ሁሉ እርስ በርስ እየተረጋገጡ ይዘነጣጠሉ ገቡ። በላይ በላይ እንደዶፍ የሚወርደው የእሳት ኳስ መቆሚያ መቀመጫ አሳጣቸው። እየዘለሉ ወደዘንዶ በመሄድ ለመዳን ቢዳክሩም አልቻሉም። ጭንቅላቱ በወጥመድ ተጠፍንጎ ያለው ዘንዶም በእሳት ኳሶቹ ከመደብደብ አላመለጠም። አካባቢው ጋየ። ዘንዶ ጭራውን ወዲያ ወዲህ በስቃይ ሲያላጋ የሚጨፈልቃቸው ጅቦችና ተኩላዎች ብዙ ነበሩ። በየት መጣ ሳይባል መልዓኩ ገብርኤል በታላቅ ቁጣ ሰይፉን ሰንዝሮ በአንድ ሽክታ የዘንዶውን ራስ ከሌላው አካሉ ለያየለት። "ጎበዝ፣ ጎበዝ" አለ ባዬ ለማጨብጨብ እየጣረ። ክንዶቹ በመላዕኩቱ ተይዘው ስለነበር ያሻውን ማድረግ አልቻለም። መልዓኩ ገብርኤል የባዬን ማበረታቻ የሰማ አይመስልም ወዲያው ከአካባቢው ተሰወረ። ባዬ ቢፈልገውም አላገኘውም። ያኔ የእሳት ፍላፃ ዝናብ ቀስ ቀስ እያለ እየቀነሰ መጣ። መሳሪያ ቁጠባ መሆኑ ነው? ሲል አሰበ ባዬ።

 ወዲያው በወጭት ሆኖ የተጣለውን የዘንዶው ራስ ለመቀጥቀጥ ትጥቁን ያሟላ ቀጥቃጭ መጣ። ቀጥቃጩም የዘንዶውን ራስ ደህና አድርጎ ቀጠቀጠው። እስኪበቃው ከቀጠቀጠው በኋላ እንደምግብ በነፍስ-ወከፍ ለእያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ  ሲሰጥ ባዬ አየ። በዚያን ሰዓት መደነቅ ጀመረ። ኢትዮጲያ ቀሰ ቀስ እያለች አበባ በአበባ፤ ዘንባባ በዘንባባ ሆና አያት። የፊልም ቅንብር እስኪመስለው ድረስ ትዕይንቱ አስደመመው። ኢትዮጲያውያኖች ለቅሶ አቁመው ቀና ቀና ብለው ከእንቅልፍ እንደነቃ ሰው እየተያዩ ሰላም ተባባሉ። ከዛም እየተሳሳቁ እየተቃቀፉ ወደየስራ ገበታቸው ሲሰማሩ አየ። ይህ ምን ማለት ነው? ለማስታወስ ሞከረ። የሆነ ሰው አስቀድሞ ነግሮት ነበር? ወይስ እሱ ራሱ አስቦት ነበር? ባዬ እጁን ባፉ ላይ ጫነ። ሙስሊሙ ቆቡን ደፍቶ በስርዓት ስራውን ያከናውናል። ክርስቲያኑም በስርዓት የእለት ተግባሩን ሲከውን አየ። ሰላም በአካባቢው ሰፍኖ፤ አካባቢው ሁሉ በልምላሜ ተሞልቶ አየ። ከኢትዮጲያ ደማቅ ብርሀን ፍንትው ብሎ ሲወጣ አየ። አካባቢው ሁሉ ብርሀን ተላበሷል። አፍሪካ በኢትዮጲያ ብርሀን ፈካች። ከምድሪቱ የሚወጣው ብርሀን አረብ ሀገራትን አልፎ ውቅያኖሶችን አቋርጦ አለምን ሲያዳርስ አይቶ ተደነቀ። ጀርመን ሳትቀር ከኢትዮጲያ በሚወጣው ብርሀን ስትደነቅ አስተዋለ። ደስ አለው። የአረብ አገራት ገና ከድሮ የኢትዮጲያ ጥገኛ ሆነዋል።

 "ይህ በርግጥ የሚጠበቅ ነው ነገር ግን በእንደዚህ ቆንጆ አይነት ሁኔታ ይሆናል ብዬ አላሰብኩም" አለ ባዬ።

"እንሂድ" አለ አንደኛው መልዓክ ከዛ ጉዟቸውን ቀጠሉ።

"ወዴት ነው ግን የምትወስዱኝ? እየተጫወትን እንሂዳ" አለ ባዬ።

"ወዴት ይመስልሀል?" ሲል መልሶ ጠየቀ አንደኛው መልዓክ።

"እኔ አላውቅም። የትም ብትወስዱኝ ግድ የለኝም። በሀገሬ መበልፀግ በጣም ተደስቻለሁ። በሀገሬ ሙስሊሞች ሀገር ወዳድነት፤ ጨዋነት ረክቻለሁ። በሀገሬ ክርስቲያኖች ታማኝነት፤ መሰጠት ተደምሜያለሁ። በህዝቤ ታታሪነት፣ ስራ ወዳድነት ተደንቄያለሁ።… ዓላማዬ ተሳክቷል።"

"ባክህ አትቀባጥር… የት እንዳለህ አውቀሀል ለመሆኑ? እንኳን ወደ ሲኦል በደህና መጣህ ባሪያው። እኔ ሂትለር እባላለሁ።" አለ አንድ ሰው ጮክ ብሎ ከሚያልፉበት አካባቢ። አካባቢው በከፍተኛ ቆሻሻ ሽታ ታጥኗል። ከመጠን ባለፈ ይሞቃል። የሰዎች ዋይታና ለቅሶ፤ ፀፀት አየሩን ሞልቶታል። ባዬ ቦታውን አይቶ ተፀየፈው።

"ሲኦል መሆን ግን አልፈልግም" አለ ጮክ ለማለት እየሞከረ። እያለፉ ሄዱ። ሲኦልን አልፈው በመሄዳቸው ባዬ ትንሽ ተነፈሰ።

 ***

 ጥግ ላይ ጦር ይዘው ቁጭ ካሉት የሲኦል በር ጠባቂዎች ድንጋጤ ውስጥ ያሉ ይመስላሉ። ሌሎቹ ደሞ ስራ አንደበዛበት እየተጣደፉ ከዛ ወደዚ፤ ከዚ ወደዛ ይራወጣሉ።

 "ሰምተሀል? ሌላኛው የአፍሪካ መሪ መጥቷል። ግን እዚ ይሁን እዛ ይሁን አላወኩም።" አለ አንዱ ክፉ መልዓክ።

"ምንድን ነው የሚሻለው? ሁሉም ነገር እየፈጠነብን ነው። በቃ የኛ መጨረሻ እንደዚህ ሆነ?" አለ ሌላኛው።

"ምን ሆነሀል? ባለቀ ሰዓትማ ተስፋ መቁረጥ ብሎ ነገር የለም። የመጨረሻው ተስፋችንን ሀሰተኛው ክርስቶስ መነሳትን እንጠብቃለን። እስከዛ ብዙዎችን ከወንጌል አርቀን ወደሞት መንዳት ነው። ዋናቸው ከመመለሱ በፊት ምድርን እንጨምቃታለን። ከዛ…"

"አዎ እንደዛ ማሰብ ይሻላል። ቢያንስ ያን ማሰቡ ያረጋጋህና ስራህን ባግባቡ እንድትሰራ ትሆናለህ" አለ ሌላ ክፉ መልዓክ። ጨዋታቸው ያልተዋጠለት ሌላ ክፉ መልዓክ ጦሩን መሬት ሰክቶ እንደያዘ ጭንቅላቱን ወዘወዘ።

"አትሳሳቱ።ይሄ ነገር እኮ ያበቃለት፤ ያከተመ ነገር ነው። እንደ ስፖርት ውድድር ማን ያሸንፍ ማን ያሸንፍ ለማወቅ እስከመጨረሻው መጠበቅ አለብን የምትሉት አይነት አይደለም።ጥቁር ጥቁር ነው። ነጭ ነጭ ነው። እመኑ እኛ ተሸንፈናል። ግዛት ብንከልል ነው የሚሻለን። ሲኦልን የምናስብ ከሆን ተሳስተናል። ቁልፍ ያስፈልገናል። የሲኦልን ቁልፍ ያ ተንከሲስ ከእኛ ነጥቆ ለነዛ ኮሳሳዎች ያኔ ሰጥቷቸዋል። ይልቅ ሌላ ነገር ማሰብ ብንጀምር ነው ጥሩ። ምንድን ነው ድርቅ ማለት።" አለ። ሌሎቹ ግን አላስጨረሱትም።

"ዝም በል አንተ ደሞ። …ዝም ብለህ ትቦጠርቃለህ እንዴ?... ወሬ አማረልኝ ብለህ…" እያሉ ተንጫጭተው ዝም አሰኙት።

  ***

 እነባዬ መብረራቸውን አላቆሙም። ሲኦልን አልፈው ሄዱ። ሄዱ ሄዱና ገነት ደረሱ። እያለፉ ሳለ ባዬ እነአብርሀምን፣ እነሐዋርያው ጳውሎስን፣ እነ አባ እስጢፋኖስን አይቶ "ለእኔ በዚህ መሆን መልካም ነው።" አለ። ነገር ግን መላዕክቱ አልሰሙትም። ገነትንም አልፈው እየበረሩ ሄዱ። ባዬ ግራ ገባው። ጥቂት ከሄዱ በኋላ ይዘውት የመጡት መላዕክት ባዬን ለሌሎች መላዕክት አስረክበው ተመለሱ። እነዚህኞቹ መላዕክት ደሞ የባሰ ይገዝፋሉ፤ ክንፎቻቸውም በርከት ያለ ናቸው።  ፀሀይ ወደሚመስል ነገር ይዘውት በረሩ። ባዬ ፈርቶ የማያውቀው ልቡ ፈራ። ልቡ ጠረጠረ። አንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ቃል ትዝ አለው። "ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል" የሚለው ቃል ትዝ አለው። ይዘውት የመጡት አዲሶቹ መላዕክት የሆነ ቦታ ጋር ሲደርሱ ባዬን አቆሙትና ገለል አሉ። እውነት ሆነ ማለት ነው። በአለም ሁሉ ፈጣሪ ፊት ነው የቀረብኩት ሲል አሰበ። ከፊቱ ያለውን ለማየት ቢሞክርም አልተቻለውም።  አይኑ ተጥበረበረ። አይኑ እንዳይጠፋ ከሚዋጋው ብርሀን ለመሰወር በክንዱ ፊቱን ለመከለል ሞከረ።

 

ሆኖም እንደምንም ብሎ ታግሎ ባንዲት ቅፅበታዊ ቀዳዳ ደማቁን ብርሀን አየ። ኢየሱስን ነው ቆሞ የማየው? ለማጣራት በደንብ ሊያይ ሞከረ ግን አልቻለም። ብርሀኑ ከፀሀይ ይደምቃል። ወዲያው ከሀይለኛ ስፒከር የሚለቀቅ የሚመስል ነጎድጓድ ድምፅ መናገር ጀመረ። ይህ ሁሉ ለኔ ነው? አይበዛም? አለና ጆሮውን ለማዳን በእጁ ያዘው።

 "የአብርሀም፣ የይስሀቅ፣ የያዕቆብ አምላክ እኔ ነኝ። የእስራኤል ቅዱስ እኔ ነኝ። እኔ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ነኝ፣ እኔ እኔ ነኝ።" አለ ታላቁ ድምፅ። ይሄኔ ባዬ ነፍስም ስላልቀረለት ራሱን መቆጣጠር ተስኖት መሬት ተደፋ። ቶሎ ብለው ሁለቱ መላዕክት ባዬን መጥተው አነሱትና አቆሙት።

 "ሰውን ሁሉ የማውቀው በልጄ በወልድ ነው።… ባዬ ሆይ ወልድ አለህ?" አለ ታላቁ ድምፅ በሚያስፈራ ሁኔታ። ባዬ ራሱን ለማቆም ታገለና አፉ እየተንቀጠቀጠ የመጀመሪያውን ጥያቄ መመለስ ጀመረ።

ፍፃሜ

                          ሶስቱ ምስማሮች  ( The Three Nails )     

 ስው ሁሉ ከያለበት ተሰብስቦ የሚነገድበት ሰፊው ገበያ በቀራኒዮ ከተማ መሀል ላይ ሰፍሯል። ከዚህች ከተማ ትንሽ ራቅ ብሎ አንድ የገጠር መንደር ነበረች። ጥቂት ሰዎች ብቻ በተን ብለው ከሰፈሩበት ከዚህ መንደር ውስጥ አንድ ሽማግሌና ወንድ ልጃቸው ይገኙበት ነበር። ሽማግሌው ዮሀና ቋሚ የሆነ የገንዘብ ምንጭ አልነበራቸውም። ነገር ግን ዕቃቆችን በመግዛትና በመሸጥ ራሳቸውን ያስተዳድሩ ነበር። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ግን ኑሮ እጅግ ከብዶባቸዋል። ኑሮ ተወዶባቸዋል። ትንሽ ገቢ ቢጤ የነበረው አንድያ ልጃቸው በጨረቃ በሚነሳ በሽታ ተመትቶ አልጋ ላይ ወደቀ። ለእሱ መዳን ሲሉ ያልወጡት ተራራ ያልቧጠጡት ነገር አልነበረም። ተስፋ የለሽ ሆነባቸው። ያጠራቀሟትን ገንዘብ ዕለት ዕለት በባለመድሀኒት አለቀች። ልጁም ባሰበት እንጂ አልሻልም አለው። በሽታው ሲነሳበት ቦታ ሳይመርጥ የትም ይወድቅ ስለነበር የልጁ ሰውነት እንደጨርቅ ነተበ። በቁስል ተሞላ።

 አንድ ቀን ዮሀና የሚላስ የሚቀመስ የጠፋበትን ቤታቸውን ዘግተው በትካዜ የልጃቸውን መጨረሻ እየተከታተሉ ሳለ ማምሻውን አካባቢ ልጁ በሽታው ተነስቶበት ያንፈራግጠው ጀመር። ዮሀና የሚይዙት የሚጨብጡትን አጡ። ምግብ ሳይቀምስ የከረመው ጎናቸውን እያዋከቡ ልጃቸውን በገመድ ታግለው ጠፍረው ካሰሩ በኋላ

"ልጄ! አይኔ እያየ አትሞትም" ብለው መፍትሄ ፍለጋ ቦታውን ሲያተራምሱ ድንገት ለረዥም ዘመን ሳይከፍቱ የቆዩትን አንድ መሳቢያ ላጥ አድርገው ሳቡት። ሲስቡት አይናቸው ሶስት ትልልቅ ምስማሮች ላይ አረፈ። ሶስቱን ምስማሮች አነሱትና ዋጋ ተመኑለት። የጥቂት ቀናት ቀለብ መሸመት የሚችል ዋጋ ያለው ሆኖ አገኙት። ጊዜ ሳያጠፉ ምስማሮቹን ሸጠው የሚበላ ነገር ለመግዛት በችኮላ በትራቸውን ይዘው ወጡ። እስኪመለሱ ልጃቸውን እንዲያቆይላቸው አምላካቸውን እየተማጠኑ የአንድ ቀን መንገድ ተጓዙና ቀራኒዮ ገቡ። ወገባቸው በድካም መንቀጥቀጥ ጀምሯል።

 ቀራኒዮ ሲገቡ የሀገሬው ሰው በአንዳች ነገር የተወጠረ ይመስል ሁሉ ሰው እዛና እዚ ሲራወጥ አስተዋሉ። እጅብ ቆመው የሚወያዩ ቡድኖች እዛም እዚም ይታያሉ። ዮሀና በግራመጋባት ወደ አንዱ ብላቴና ጠጋ አሉና

"ልጄ ዛሬ ምንድን ነው?" አሉት። ከግብፅ የወጡበትን ቀን የሚያከብሩበት ፋሲካ ገና ሶስት ቀን እንደሚቀረው ልባቸው እየታወቀው። ብላቴናውም

"እንዴ? ኢየሱስ የሚባለው ሰውዬ እኮ ሊሰቀል ነው። ኑና ይዩት" አለ። አንዳች ትርዒት ሊያይ እንደተዘጋጀ ሰው አይኖቹን እያቁለጨለጨ።

ዮሀና የሰሙት ነገር ደስ አላሰኛቸውም። ይህ ኢየሱስ የሚሉትን ወጣት ከአንዴም ሁለቴ ጮሆ ሲያስተምር ለመስማት እድል አግኝተዋል። አዳምጠውትም በጣም ወደውታል። ሁሌ ቢያገኙት የመኙም ነበር። በወጣቱ የማስተዋል ብቃት ሳይደነቁ የቀሩበት ጊዜ አልነበረም። ምንም ወጣት ቢሆንም በሳቸው ልብ ግን የተናቀ አልነበረም። ከልባቸው ስፍራ ሰጥተውት ነበር። ምነው ልጄ በሆነ! እስኪሉ በጣም ያደነቁትና የወደዱት ወጣት ነበር፡ ይህ ኢየሱስ።

 ዛሬ ግን ለስንት ነገር ይበቃል ብለው ይጠብቁት የነበረውን ወጣት ሊሰቅሉት ነው? ቀልድ ነው ወይስ ምንድን ነው ነገሩ? ምን አጥፍቶ ይሆን? ማንን ሰርቆ ማንን ገድሎ ይሆን? ምንም ወንጀለኛ አልመስል አላቸው። ደስ አላላቸውም፣ ተቀየሙ። እዚህ ሀገር በቃ ቅን ሰው አይበረክትም ማለት ነው? ሲሉ አሰቡ። በዚህ መሀል ወጣቱ ኢየሱስ እየተገፈተረና እየተገረፈ በህዝብ ታጅቦ ከወደፊት ሲመጣ ሲያስተውሉ ልጃቸው ትዝ ብሏቸው፣ ያባት አንጀት ሆኖባቸው "ውይ ልጄ እኔው በደማሁት፣ እኔው ያረጀሁት በቆሰልኩት …" ብለው ሮጥ ቆም እያሉ ኢየሱስን ሊደግፉ ወደ ኢየሱስ ተጠጉ። ድንገት ሳያስቡት አንድ የወፍራም ጅራፍ ዥልጫ ጎናቸውን አወላወለውና ወደቁ። የሳቸውን መውደቅ ማንም ልብ ያለ አይመስልም።

"ይሰቀል…ይሰቀል… ይሰቀል!" እያሉ ግር ብለው እየጮሁ ግንድ የተሸከመውን ኢየሱስ ይከተላሉ። ዮሀና ከወደቁበት እንደምንም ተነሱ ቆሙና የኢየሱስን መጨረሻ ለማየት ህዝቡን ተከትለው ሄዱ።

* * *

ሐሙስ  ዕለት ማታ የተወሰኑ ሰዎች የማታውን ብርድ ለመቋቋም እሳት አንድደው ተቀምጠው ነበር። ከመሀላቸው ሄዶ የነበረው ልጅ ሲመለስ አዩትና

 “ምንድን ነው?” አለ አንዱ ከተቀመጡት

 “ምን ባክህ ስራ ታዘናል።” መለሰ መጤው ለመቀመጥ ቦታውን እያመቻቸ። አለቃቸው ቢሆንም ማንም ቦታ ሊለቅለት የወደደ አልነበረም። ከጥቂት ቆይታ በኋላ...

 “የምን ስራ?” አለና ጠየቀ ያነኛው መልሶ

 “ሰዎችን መስቀል።” ሲል አለቃው መለሰ።

 “ስንት ናቸው... እነማን ናቸው?” አለና ጠየቀ ሌላ ሰው።

 “ሶስት ናቸው ብለውኛል። አንዱ ከበርናባስ ጋር ሰው ሲገድል የነበረው ወንጀለኛ ነው።” አለና መለሰለት። ቅር ያለው መሆኑን በድምፁ ቃና አወቁበት።

 "ታዲያ ወሰዶ መስቀል ነዋ። ሌላ ምን አለው?" ብሎ ጠየቀ የመጀመሪያው ተናጋሪ።

 "ባክህ እኔ ምንም ደስ አላለኝም።...እናንተው ጨርሱት።" አለ ፍርጥም ብሎ። ከዛ ተነስቶ ቆመ "ሁሉንም ነገር አዘጋጅላችኋለሁ። ነገ ጠዋት ተነስታችሁ ብቻ እቃዎቹን ሰብስባችሁ የመስቀያው ቦታ በጊዜ እንድትገኙ።" ብሎ ካዘዛቸው በኋላ ተቷቸው ሄደ።

 በነጋታው እንደታዘዙት ወደ ቀራኒዮ ሄደው እንጨቱን፣ ገመዱን፣ ሚስማሩን ሲያስተካክሉና ሲያሳስሩ በዛውም የሚሰቀሉት ሰዎች እስኪመጡላቸው ድረስ እየጠበቁ እስከ ስድስት ሰዓት ቆዩ። ሶስቱ ወንጀለኞች ከመጡላቸው በኋላ ምንም ጊዜ ሳያጠፉ ስቅላቱን ጀመሩ። የመጀመሪያውን ወንጀለኛ በሶስት ምስማር ሰቀሉት። ከሌላ ቀን በበለጠ ዛሬ ስራቸውን ሊያይ በመጣ ብዙ ህዝብ ተከበዋል። ብዙ የሮማ ወታደሮችም አብረው ነበሩ። ቀጠሉና ሌላኛውን በሌላ ሶስት ምስማር ቸንክረው ሰቀሉት። ስራቸውን እንዲህ በማጧጧፍ ላይ እያሉ በመሀል የቀሩት ምስማሮች ለስቅላት እንደማይሆኑ ተነገራቸው። ህዝቡ የኢየሱስን መሰቀል በጉጉት የሚጠባበቅ ነበርና ቢዘገይ የሚቦጫጨቋቸው አይነት ነበሩ። እንዴት እንደሆነ ባይታወቅም የሚፈለገው የምስማር አይነት ደግሞ ከገቢያ ላይ ታጣ። ሰቃዮች የህዝባቸውን ጭካኔ ስለሚያውቁ ምህረት ለማያውቁ የሮማ ወታደሮች አሳልፈው እንዳይጧቸው በመስጋት በምስማር ፍለጋ ሰበብ ተተረማመሱ። በጭንቀት ስብሰብ ብለው ሲነታረኩ አንዳንዶች የዛሬን ብቻ ከጉድ አውጣን እያሉ ወደ ፈጣሪ ሲለምኑ ይከታተል የነበረ አንድ ታዳጊ ምስማር እንደሚፈልጉ አውቆ ተጠጋቸውና

 "ምስማር ነው የምትፈልጉት? ቅድም አንድ ሽማግሌ ምስማር ወድቆባቸው አንስቼ ሰጥቻቸዋለሁ። ምስማሩ እናንተ የምትፈልጉት አይነት ይመስላል።" ብሎ ነገራቸው።

 ታዳጊው በጠቆማቸው መሰረት ሽማግሌው ዮሀናን ከህዝቡ መሀል ይፈልጓቸው ጀመር። ፈለጉና አገኙዋቸው። ከዛም የያዙትን ምስማር እንዲሸጡላቸው መደራደር ሲጀምሩ ዮሀና በቁጣ

 "ስታስቡት እኔ ... ልጄን የምትሰቅሉበትን ምስማር የምሸጥላችሁ ይመስላችኋል? ሂዱ ከፊቴ!" አሉ በደም ፈላት።

 ሊያግቧቧቸው ቢሞክሩም ዮሀና እሺ የሚሉ ሆነው አልተገኙም። ሰቃዮቹ ግን እርስ በርስ በአይን ተነጋገሩና ዮሀና የያዙትን ምስማሮች ነጥቀዋቸው ሄዱ። ከመሀላቸው አንዱ ዞር ብሎ

 "ምስማሩን መልሰው ማግኘት ከፈለጉ ሰዎቹ ጭናቸው ከተሰበረ በኋላ ከመስቀል ላይ ሲወርዱ ያገኙታል። ሌላ ሳይቀድሞት እንግዲ ቀድሞ ተገኝቶ በደም መጨማለቅ ነው።" አለና በሹፈት ተናገራቸው።

 ዮሀና ልጁ ማሾፉን ቢረዱም አልሳቁለትም። በሽበታም ቅንድብ የተደበቁ ትናንሽ አይኖቻቸውን ተክለውበት ቀሩ። ልባቸው በከፍተኛ ቁጣ ተሞልቷል። ሰቃዮቹ ጥላዋቸው ከሄዱ በኋላ ኢየሱስ በገዛ ምስማሮቻቸው ሲሰቅሉት እያዩ በቀስታ ማልቀስ ጀመሩ።

 "ምነው እነዚህን ምስማር ያዩት አይኖቼ በጠፉ ኑሮ..." አሉ። እጆቹ ተወጥረው እግሮቹም ተጨምደደው በምስማር ሲቸነከሩ የሚሰሙት የኢየሱስን አንጀት የሚቆርጥ የስቃይ ጩኸት ልባቸውን በሀዘን ጦር ክፉኛ ወጋው።

 "ምነው እነዚህን ምስማሮች የያዙት እጆቼ በተሰበሩ ኑሮ..." አሉ በፀፀት እየተንገበገቡ። የስቅላቱ ስነስርዓት እንደተጠናቀቀ ህዝቡ ሁሉ አንድ አንድ እያለ ሄዶ ለብቻቸው ቀሩ። ምስማሮቹን መልሼ እወስዳቸዋለሁ ብለው ወስነው ሰዎቹን ከመስቀል እስከሚያወርዷቸው መጠበቅ ጀመሩ። ማምሻውን አካባቢ በህይወት የነበሩትን ጭናቸውን ከሰበሩ በኋላ ከመስቀል አወረዷቸው። ኢየሱስ ግን ሞቶ ስለነበር የሬሳውን ጎኑ በጦር ከወጉት በኋላ ጭኑን ሳይሰብሩ ሲያወርዱት ትንፋሻቸው ቁርጥ ቁርጥ እያለ ሄዱና ሶስቱን ምስማሮች ቶሎ ሰብስበው ከዛ አካባቢ ጠፉ። ሶስቱም ምስማሮች ልብሳቸውን እስከሚያበላሹ ድረስ በደም ተጨማልቀው ነበር። ልጃቸውን በገዛ እጃቸው የገደሉት ያክል እየተሰማቸው፣ በብሽታ ለሚሰቃየው ልጃቸውም መፍትሔ ሳይዙ በተስፋ መቁረጥ ለምነው ያገኙትን መብል ነገር ይዘው ወደቀዬያቸው መንገድ ጀመሩ።

 ዮሀና ቤታቸው ደረሱና ገቡ። ልጃቸውን አስረውት እንደሄዱ ነበር ያገኙት። ለሞት አንድ ቀን የቀረው ይመስል ጣዕረሞት እንደያዘው ድርቅ ብሎ ሲያዩት ደንግጠው ደሙ የደረቀባቸውን ምስማሮች የልጁ አካል ላይ ወረወሩትና የሸመቀቁትን ገመድ ይፈቱ ጀመር። ፈትተው ጨርሰው ኋላ ዞር ሲሉ ልጃቸውን በሙሉ ጤንነት ከአልጋ ላይ ወርዶ ቆሞ አዩት። ቅድም ጣዕረሞት የመሰለው ሰው አሁን ውበቱ የልጅነት መልኩ የተመለሰለት ውብ ወጣት ሆኖ ሲያዩት ማመን አልቻሉም። ቀስ በቀስ ዮሀና በመደነቅ ተሞልተው ከወዲያ ወዲህ መዝለል ጀመሩ። እርጅና ተረሳ።

 "ተፈወስክ እኮ ልጄ! ተፈወስክ" እያሉ ጮኹ። በደስታ ሲሯሯጥ የነበረው ልጃቸውም ተኝቶ የከረመበትን አልጋ ሊያነጥፍ አንሶላውን ሲጎትት ከአልጋው ላይ ሶስት ትልልቅ ቀይ ምስማሮች ተከታትለው መሬት ወደቁ። ዮሀና ሮጠው ነበር ያነሷቸው። ከዛም ልጃቸው እንዲቀመጥ አደረጉና የመፈወሱን ሚስጥር አንድ በአንድ ሊያስረዱት

"ልጄ እነዚህ ደም የደረቀባቸው ምስማሮች እኮ . . . " ብለው ታሪኩን ጀመሩለት።

                                                                                    ፍ ፃ ሜ

                                                                  * * *

ድህነት ለብልፅግና ድብቅ ደብዳቤ ጻፈ

አንድ ማንነቴን ደብቁልኝ ያለ, ለብልፅግና የቅርብ የሆነ, ሰው ይሁን መንፈስ የማይገለፅ  አካል ክፍተኛ ሚስጥር ያለውን መረጃ አቀብሎን ተሰውሯል። እኛም አንዳች ሳንጨምር ሳንቀንስ እንደተቀበልነው እንድታነቡትና አስተያየት እንድትሰጡበት ቀጥሎ ያለውን ደብዳቤ እነኋችሁ ብለናል።

  ክቡርነቶ፡-

ይህንን ደብዳቤ መጻፌ ቢታወቅ, የኔ ነገር ፈጽሞ ያበቃል። እስትንፋሴ በእጅዎ ነውና እባክዎ ይታደጓት።

እንደሚታወቀው ለረዠም ዘመን ደቁሰን አስለቅሰን በገዛናት በዚች አገር - አቢሲኒያ, ኢትዮጲያ ውስጥ ከፍተኛ የፀረ-ድህነት ዘመቻ ተጀምሮ የሚበርድ የማይማስል እሳቱም ተንቀልቅሎ እየነደደ መቆም መቀመጫ እያሳጣን ነው።

ለቁጥር የሚታክቱ የሰቡ እንቅልፎች ለክቡርነቶ እየተሰዉ, እነስራ-ተነሳሽነትም ሳይቀሩ ከዚህ በፊት አሳይተውት በማያውቁት ድፍረት ወግቶ የሚይዝና ጡንቻ የሚያፈነዳ, ጫፉን መርዝ የነከሩትን ቀስታቸውን እንደ ሃይለኛ ዶፍ እያዘነቡብን ይሀው የመጠለያችን ክዳን ተበሳስቶ 30 ጊዜ መድፈኑ እና መበሳቱ እንደሻሽ አንትቦት ዛሬ ለነፍሳችን በሚያሰጋ ሁኔታ በአደጋ ላይ እንገኛለን።

ቀድሞ ዊግ ሲቀጠልባቸው, ቀለም ሲፈራረቅባቸው, ቅቤ ሲለደፍባቸው የሰነበቱ, ፍሪዝ አፍሮ ሹሩባ እየተባለ ብቻ ሲሽሞነሞኑ የከረሙ የሴትና የወንድ ጭንቅላቶች ዛሬ ማሰብ በመጀመራቸውና ያለ ምንም ቅድመ-ማስጠንቀቂያ እኛን ለማጥቃት መፈለጋቸውን ደርሼበት እስከነአካቴው ዘርማንዝራችንን ያጠፉታል ብዬ በማሰብ የገባኝን ስጋት ለአጋሮቼ - ለድንቁርናና ለጥላቻ በማዋያቸው ጊዜ እንኳን ሊቀበሉኝ ፈጽሞ ሊሰሙኝ አልፈቀዱም።

እኔ ግን ''አማኝ አጥር ላይ አይሸናም። አለዚያ ትቀሰፋለህ።'' ብሎ ከሚያስፈራራው ትንሹ የሀይማኖት ሰው ጀምሮ እስከ አገሪቱ መሪዎች ድረስ ያሉት ሁሉ እና በፀረ-ድህነት ዘመቻ ረዥም ስልፍ ውስጥ ዝም ብሎ ገብቶ እጁን የከነዳው ሸውራራ ወፈፌ ሳይቀር ለህልውናዬ አስጊ አቋም ላይ እንዳለ ለማመን ተገድጃለሁ።

በመሆኑም በአጋሮቼ ግዴለሽ መሆንና በተቃራኒው ሀይል ተጠናክሮ መደራጀት የተፈጠረብኝ ስጋት ሰላሰገደደኝ በሌላም በኩል "ድሃና ችግረኛ ከምድረ-ገፅ አይጠፉም "ስለሚል ትልቁ መፅሀፍ, ሁሉን በቁጥጥሮ ስር ያስገቡ ጊዜ ከቶውንም እንዳያጠፉኝ ለሂወቴ ምህረት እንዲያደርጉላት ስል አጥብቄ እለምኖታለሁ። ያው በመልክ ከድንቁርናና ከጥላቻ ጋር ስለምንማሰል የፍልሚያው ወቅት እኔን ለይተው እንዲያውቁ እንዲረዳዎት አንገቴና እጄ ላይ ቀይ ክር አስራለሁ። እርሶ ብቻ አፉ ይበሉኝ እንጂ እድሜ ልኬን ፀባዬን በማሳመር ሰጥ ለጥ ብዬ እገዛሎታለሁ, ዘመኑ የእርሶ ነውና ምን አደርጋለሁ።

ጥያቄዬን እሺ ቢሉኝ የስራ አጋሮቼን /የድንቁርናና ጥላቻን/ ሰነድ ለእናንቱ በመሸጥ ንቅናቄያችሁን ልተባበር ቃል እገባለሁ። የምቀበለውንም ገንዘብ የወደፊት ኑሮዬን ለማሻሻል እንዲረዳኝ እስቀምጠዋለሁ። ይህም ብዙ ካሰብኩ በኋላ የወሰንኩት የመጨረሻ ውሳኔዬ ነውና አይጠራጠሩ አደርገዋለሁ። ደግሞስ, እንኳንስ እነሱና ዝነኛውና ታዋቂው ኢየሱስ ራሱ በ30 ብር ተሽጦ የለም እንዴ?  "አገሪቱ ያለኛ መኖር አትችልም, ሰዎቹ ይፈልጉናል።"ብለው የሚያምኑት ጥላቻና ድንቁርና በየትኛውስ ዋጋ ቢሸጡ ምን ያስደንቃል? እርሶ ብቻ ጥያቄዬን እሺ ይበሉኝ። ሂወቴን ይታደጓት።

 

ብልፅግና በአይነቱ ልዩ የሆነ መግለጫ አወጣ

 በድህነት ስም የተላከ ደብዳቤ ወደ ቢሯችን መጥቷል። ተኣማኒነቱ ከተረጋገጠ በኋላ ውይይትና ምክክር በማድረግ የምንደርስበትን ውሳኔ በተገቢው ሰአት, በተገቢው የመገናኛ ዘዴ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለፅን ለተላከው ደብዳቤ አቻ ምላሽ የማንሰጥ መሆኑን እናስገነዝባለን።

 

 ድህነት የላከው ሌላ ደብዳቤ

 ክቡርነቶ፡- እረ በፈጠሮት ሚስጥሬን ይጠብቁልኝ።

 እስካሁን ባለን መረጃ ብልፅግና ምንም አይነት ምላሽ ወይም መረጃ ከመስጠት በመቆጠብ ዝምታን -ዝም ጭጭ ማለቱን- መርጧል።

 ተፃፈ በዛሩጣ

To my childhood friends - A letter

 I haven’t seen such a thing when Quirinius was governing Syria. It was the first population census.  The whole world was ordered to be counted by Augustus Cesar. Everybody was going to the center of his own home town to be counted. The city I’m in was Bethlehem and I don’t need to tell you what she look like. It is believed that nothing good can come out of Bethlehem. It was the dirtiest city ever known. Bethlehem was a city that no one wants to stay in. But these days were different. It brought us so many new people. People were coming from the four corners of David’s city, Judah.

 There was huge number of them. There were rich guys, there were poor guys, there were lords…they were all kinds. But I felt a pity when I saw those who go in to my neighbor’s house as a guest were very rich. But mine were poor. My neighbor’s guests had many luggage. And they pay more. My neighbor’s sheep house was even taken by servants who took care of their rich masters. So I was jealous. Looking at the situation, the running and everything, you would think of Easter as it is about to be celebrated. I was busy of checking of foods if served right, giving tasks to my servants, baking that thin bread, preparing the wine…it was a unique day.

 My childhood friends, I will tell you in detail of what had happened exactly when I come to visit family and you. I wrote this because I have questions to ask you. You need to hear me. I told you our home town Bethlehem was full of guests. So we, the town dwellers, received them in to our guest houses, gave them food, washed their feet, prepared their beds. My neighbor Hanania came to borrow some kitchen equipments from me. She was very proud that all of her guests were rich and lords. And she told me that the fame of her house was heard all over the place. I was jealous. She told me that all of her guests liked her food that they were asking for more. At no time we found some gap to rest from the running. We wanted to talk alone so we went to the back of my garden. We can hear the laughter of our guests. It didn’t take Terfesa, my servant, to come and disturb us.

“My lady, there are persons who want to come in and rest.” Said my servant Terfesa “shall I bring them in?”

Hanania answered him back quickly.

“Are they lords?” said Hanania and when she saw that Terfesa didn’t understand what she was saying she explained “Do they look like rich? Do they have bodyguards and luggage?”

Terefesa felt embraced by Hanania’s attitude, I knew that he wanted to ignore the question.

“No, I don’t think so. They are two. The woman is pregnant. The man is young. Both seem newlywed.” said Terfesa. He was looking up to me for answer but Hanania kept talking. I can tell that he was very annoyed. Now I looked at Hanania and seem sad.

“Oh ho? These one, I refused them letting in. such persons don’t have the pay. Even if you let them in for no money, they don’t know how to keep their environment clean. Don’t let them in. You won’t lose anything. Wait for a while, people are still coming.” said Hanania. She then went out to check on her guests.

“Tell them there is no more room here that we are very sorry.” I said to Terfesa. He then went out too. I was standing alone in the middle of the garden. Before long, I saw Terfesa coming back to me. I didn’t like his action.

“What is it?” I said furiously.

“Ow my lady, they don’t listen to me …what shall I do?” said Terfesa. I guess he liked the fact that those persons refused to go away. I was so mad at him and at these persons who are waiting at the gate. I left him there talking. I went straight to the gate. I opened the gate and what I saw was the unexpected. The woman is pregnant and Terfesa forgot to tell me she is in labor. There was no room in the inn. But I couldn’t let these poor guys go in this way. I asked them for their name and where they come from. The young man told me his wife’s name was Marry and his name was Joseph. I hesitated for a while but I let them in. Terfesa was behind me. I ordered him to prepare them the cattle's house. Terfesa is a good servant. He incorporated the servants under him and prepared the cattle's house. I led them in. They don’t talk too much. And the young man treats his woman with affection.  Not long, Marry brought forth her first born son and wrapped Him in swaddling clothes and laid Him right in the manger because there was no room in the inn. Then amazing thing happened. The house was filled by people who came to visit these young couples and the new born baby. I knew Hanania my neighbor regretted refusing Marry and Joseph to receive them in to her house.

 Then wise men come to my house saying “where is He who has been born king of the Jews? For we have seen His star in the east and have come to worship Him” they rejoiced with exceedingly great joy. They fell down before the baby and worshiped Him. I couldn’t stop my tears from dropping. The whole thing touched my heart. The wise men opened their treasures and presented gifts to Him: gold, frankincense, and myrrh.  I received some good staffs too. When I go out and check my guests in the inn, I run back quickly to Marry and Joseph to see their amazing baby. My cows and sheep seem to know the baby is not an ordinary baby. They just kept winning.

 Now while I was seeing the baby with His parents, there come shepherds who straight to my house from the fields. That really amazed me. I received them with joy. They were very happy to see the baby with Marry and Joseph. They told us that they saw angels and told the things which were told them concerning the Child by the angel. All of who heard it marveled at those things which were told by the shepherds. It is really marvelous!

 My childhood friends, I wrote this thinking that you may have answers to my questions. Is this Babe our savior? Do you think He is the glory of our people Israel? Is He the one who is called Christ who will save us from our oppressors? Remember His mere presence just turned my life upside down. What will you do if you were in my place? Please don’t tell to my mother about this since she is scared of new thing that she will curse me. You just answer me back as quickly as possible, my heart had already melted. I am waiting for your answers eagerly.

 Lastly, my lord Fanuel, who wrote this letter, sends his regards.

From the city of David

Rebecca

አገልግል

የመፀዳጃ ቤቱ መስታዊት ፊት ቆሜያለሁ። እጄን ከታጠብኩ በኋላ ከጎን ተቀምጦ የነበረውን የሽንት ቤት ሽቶ እጄ ላይ አንጠባብኩ። ቀና ብዬ በመስታዊቱ ባሻገር ያለችውን የቤት እመቤት የሆነችውን ሴት አየሁዋት። ፀጉሬ ደህና ነው። ከጥቂት ዘለላ ሽበቶች በስተቀር ቀለሙ እንዳለ ነው።በዛ ያሉ መስመሮች ፊቴ ላይ ሳይ ግን ተገረምኩ። ስስቅ ምን ልመስል ነው ታዲያ ብዬ ሳቅኩ። መስመሮቹ  ተበራከቱ። መሳቁን ትቼ ተኮሳተርኩ። መስመሮቹ ግን ድብዝዝ ይላሉ እንጂ የሚጠፉ አልሆነም። መልሼ ፈገግ አልኩ። ሂወት ግን ምንድን ነው? ሰሞኑን የድብርቴ መጠን በጣም እንደጨመረ ለራሴም ገርሞኛል። ባለቤቴን እንዳስቸገርኩት አውቃለሁ። በኔ ምክንያት ተጨቃጫቂ ባል ለመሆን በቅቷል። የባንክ ደብተሬ የናጠጠች ሀብታም የሚያስብለኝ ቁጥር ተፅፎበታል። ግን እኔ ደስታ የለኝም። ገንዘብ የማይገዛው ነገር የለም ይላሉ። ውሸት ነው። አይን ያወጣ ውሸት። ሁሉም አለኝ ግን ደስተኛ አይደለሁም። ደብሮኝ ነው የምውለው። እለኔ መኖር ምን ትርጉም አለው? አረጀሁ አላረጀሁ ጣጣ የለኝም። ብቸኛው ልጄ እንደሆነ ከፍተኛ ተቋም ተቀላቅሎልኛል። ሞትኩ ኖርኩ ብዙም ልዩነት የለውም። ከእንግዲህ እዚች ምድር ላይ ምን እሰራለሁ? ብዬ ለራሴ አሰብኩና መፀዳጃ ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ። ሁሉንም ክፍሎች በጨረፍታ አየት እያደረኩ አለፍኳቸው። ሁሉም ፀድተው ተውበው ተዘጋጅተዋል።  

ጥሩ ክፍያ የምከፍላት ሰራተኛዬ ብርዙ ምግብ ቤት ውስጥ ስትንጎዳጎድ ይሰማል። አረብ አገር ነበረች። ለዛ ይሁን፡ ተፈጥሮ የለገሰቻች ፀባይዋ ይሁን አላውቅም ባህሪዋ መሬት ነው። እወዳታለሁ። ግን ለምን ስለሷ አስባለሁ? ገድል ትግባ ብትፈልግ ብዬ አሰብኩና ሀሳቤን ሳጤነው ድብርት ውስጥ እንዳለሁ ተረዳሁ። ከምግብ ቤቱ ይወጣ የነበረው የምግብ ሽታ ሆዴን አላወሰው። እንግዶቼ ከ30 ደቂቃ በኋላ ይደርሳሉ። ባለቤቴ  ፈረንጅ ጓደኛውን ይዞ ይመጣል። ለየት ያሉ እጮኛሞች ናቸው ብሎኛል። ባለቤቴ እንከን አይወድም። በተጠንቀቅ እየጠበኩት ነው። ሁሉንም ነገር በጊዜ አስተካክዬ ስለጨረስኩ ቁጭ ብዬ መፅሀፍ እያነበብኩ ልቆይ አሰብኩ። ትዝ ሲለኝ ግን እንግዳ መቀበያው ክፍል ያለው ትልቁ ጠረጴዛ ላይ ያላለቀ ስራ አስቀምጬ ነበር። ወደዚያው ሄድኩና የአፍ እና እጅ መጥረጊያ ሶፍቱን እየለያየሁ ማስቀመጥ ጀመርኩ።

ክፍሉ ውስጥ ሬዲዮ ይሰማል። ብርዙ ሬዲዮ መስማት እንደምወድ ስለምታውቅ ከፍታልኝ ነበር። ዘፈን ይዘፍናል። ዘፈን እወዳለሁ። ዘፈን ብቻ የሚለቅ ራሱን የቻለ የሙዚቃ ኤፍ ኤም ቢኖረን ጥሩ ነበር። ዘፈን ማዳመጥ ስፈልግ እዛ ሂጄ አዳምጣለሁ። አሁን ግን ሳልፈልግ ዘፈን እንዳዳምጥ እየተገደድኩ ነው። ምክንያቱም በየመሀሉ ለማዝናናት ታስበው ጥልቅ የሚሉት ዘፈኖች እየሰማሁት ያለሁትን ቁምነገር ያቆረፍዱብኛል። ከቁምነገሩ ተደናቅፌ ዘፈኑን አዳምጬ ወደ ዘገባው ከሚመልሱኝ አንድኛውን ሌላ ጣቢያ ደርሼ ብመጣ እመርጣለሁ። ደሞም ብዙ ጊዜ ያጋጥመኛል። አንዱ ጣቢያ ዘፈን ሲያዘፍን አንደኛው ቁምነገር እያወራ አገኘዋለሁ። መሸጋገሪያ ሙዚቃ በቂ ነበር ብዬ እያሰብኩ ተነስቼ እየዘፈነ የነበረውን የሬዲዮ ጣቢያ ቀየርኩት።

ይህኛው ሬዲዮ ጣቢያ ላይ የስልክ ውይይት እየተደረገ ነበር። አዳመጥኳቸውና ትኩረቴን ስለሳቡት ጣቢያውን ሳልቀይር እዛው ላይ ትቼው ወደ ስራዬ ተመለስኩ። የሚወያዩት አንድ ሴትና አንድ ወንድ ናቸው። አንዲት ሴት ስልክ ደዋይ ሀሳቧን ለማጋራት ገባች።

" እኔ አሁን ለምሳሌ ሌዝቢያን ነኝ። ምንም አላፍርበትም እንደውም እኮራበታለሁ።" አለች ደዋይዋ። በጣም ደነገጥኩ። ምን?

"ስምሽን መናገር ለምን አልፈለግሽም? እንድትታወቂ ባትፈልጊ ነው። ያ ደሞ የሚያሳየኝ ከዚህ ጋር ተያይዞ ሊደርስብሽ የሚችለውን የህብረተሰቡን ተቃውሞ ከመፍራት ይመስለኛል።" አለች ሴቷ አወያይ። እያንሸራሸሩ ባሉት ሀሳብ ልቤ ተንጠለጠለ። ደሞ ምን ሊሉ ነው? ሮጥ ብዬ ሂጄ የሬዲዮኑን ድምፅ ጨመርኩና ተንቀሳቃሽ ስልኬ ላይ ያለውን ሰዓት እያየሁ ወደስራዬ ተመለስኩ።

" አይደለም ቆይ ኤልሀም። እሱ ሌላ ጉዳይ ነው። አሁን አድማጫችን ሀሳቧን ትጨርስ።" አለ ወንዱ አወያይ። የደዋይን ሀሳብ የሚጋራ መሰለኝ።

"ጌይ መሆን የተፈጥሮ ማንነት ጉዳይ ነው። ለምን ጥቁር ሆንክ ለምን ነጭ ሆንክ ብለህ የመጠየቅ መብት እንደሌለህ ሁሉ ለምን ጌይ ሆነህ ተወለድክ ብለህ መጠየቅ አትችም። እንኳን ልትከለክለው ቀርቶ ማለት ነው። በቃ እግዚ/ር ሲፈጥረን እንዲህ ነን። ይህንን ምረጭ ብሎ ማንም ሊያስገድደኝ አይገባም። ምርጫዬ ይሄ ነው።"

" አሁን እየተወያየን ያለንበት ረዕስ ስለ ሱስና መፍትሄው ነው።" አለች ኤልሀም።

" ገብቶኛል። ከኔ በፊት የገባው ደዋይ በግብረ ሰዶም ሀሳብ እየተሰቃየሁ ነው። ሱስ ሆኖብኛል ላለው ምላሽ ለመስጠት ነው እኔ የደወልኩት። ግብረሰዶማዊነት ሱሰኝነት አይደለም። ይህ ውዥንብር መጥራት አለበት። ወጣቶቻችን ፈሪ እንዳይሆኑ ከፈለግን ብናስረዳቸው መልካም ነው። ጥቂት ጊዜ ይወስድ ይሆናል እንጂ ይሄ ነገር መቀየሩ አይቀርም። ግብረሰዶማዊን ማግለል የሚቀርበት ቀን ሩቅ አይደለም። የባሪያ ንግድ እንደቀረ ሁሉ እኛም አንድ ቀን ነፃነታችንን እናውጃለን። ይህ ሱስ አይደለም።"

" በህጋችን እኮ ግብረሰዶማዊነት ህገወጥ መሆን ነው። ያስቀጣል" አለች ኤልሀም የደዋይን ንግግር አቋርጣ።

" አሁን እየተንቀሳቀስን ያለነው ለሱ ነው።" አለች ደዋይዋ ረጋ ብላ። ደሞ አታፍርም እንዴ ብዬ ብግን አልኩኝ። የሷን አይነቶቹን ሰብስቦ በእሳት ማቃጠል ነበር ስል አሰብኩ።

" አየሽ? ሴት የሚደፍር እንደሚቀጣ ሁሉ ያለሁለቱ ፍላጎት የሚፈፀም ነገር ካለ… እኔም ይስማማኛል። ያ ሰው መቀጣት አለበት። እ… በነገራችን ላይ ህጉ የሚለው ድርጊቱን ሲፈፅም የተያዘ ነው እንጂ የሚለው ጌይ መሆን አትችሉም የሚል ነገር አልተቀመጠም። ሊቀመጥም አይችልም። እኛ ገሀድ መውጣት የምንፈልግበት ደረጃ ላይ ስለደረስን ህጉን ትንሽ ለወጥ ማድረግ ነው የሚጠበቀው። አሁን እየተንቀሳቀስን ያለነው ለዛ ነው" አለች ደዋይዋ።

" እሺ ደዋያችን ስለሰጠሽን ሀሳብ እጅግ አድርገን እናመሰግናለን። ወደሌሎች አድማጮች እናልፋለን።" አለች የኤልሀም። ሙስሊም ልትሆን እንደምትችል ገመትኩ። አቋሟን አደነቅኩት።  ሰዶማዊነትን ትቃወማለች። ጎሽ የኔ ልጅ።

ሁለቱ አወያዮች መወያየታቸውን ቀጥለው ሳለ ኤልሀም የወንዱን ስም ስትጠራ ያዝኩት። ቴድሮስ። ቴድሮስና ኤልሀም በግብረሰዶማዊነት የተለያየ አቋም እንዳላቸው ገባኝ።

" አድማጫችን የግብረሰዶማዊነትን ጉዳይ ለማብራራት ቀለምን አንስታለች። ይህ ግን በፍፁም ልክ አይደለም። ይሄ የፆታ ጉዳይ ነው። የቀለም ምሳሌ ልትሰጠው አትችልም። ሴትና ወንድ አለቀ። ከቀለም ወይ ከማንነት ጋር መዛመድ የለበትም።" አለች ኤልሀም።

" እኔ ግብረሰዶማዊ አይደለሁም። ግን ሰዎች ሲጨቆኑ ሳይ ዝም ማለት አልችልም። በዛ ላይ ውይይታችን ሱሰኝነት ላይ እንጂ ግብረሰዶማዊነት ላይ አይደለም።" አለ ቴድሮስ የኤልሀምን ንግግር ነጠቅ አድርጎ።

" እኔ ደግሞ ሰዶማዊነት ሱሰኝነት ነው። እንደነሀሺሽ መወገዝ አለበት። ይህን ነገር ዝም ብለን ስላየነው ህብረተሰቡን እያበላሸ ነው። ትውልድ እንዳይቀጥል ያደርጋል። አለም ቀውስ ውስጥ ትገባለች ነው የምለው።" አለች ኤልሀም።

" አለምማ ቀውስ ውስጥ ናት። የኢኮኖሚ ቀውስ፡ የተፈጥሮ አደጋ፡ ህዝባዊ አመፆች ሁሉ ቀውስ ፈጥረውባታል ነገር ግን ትወጣዋለች። ብዙ ቀውሶች ተወጥታ ነው እዚ የደረሰችው።ነገር ግን እንነጋገር ከተባለ ፅንፈኞች ናቸው ግብረሰዶማዊው ላይ ቀውስ እየፈጠሩ ያሉት። አንድ ሰው ግብረሰዶማዊ መሆኑ ከታወቀ በህብረተሰቡ ወዲያው ይገለላል። ለምን የተከበረ ትልቅ ሰው አይሆንም። ህብረተሰቡ እንደቆሻሻ ነው የሚያሽቀነጥረው። ለህብረተሰቡ የሚያበረክተው ነገር ይቀራል። ሀገራችን ደሀ ናት። ባገኘነው ምክንያት ሁሉ ሰዎችን የምናገል ከሆነ እንዴት ነው ልንለወጥ የምንችለው? ይህ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ እንደማለት ነው።" አለ ቴድሮስ። ልጁ በሚሰጠው ሀሳብ ተናድጃለሁ። እሱንም ጨምሬ ጠላሁት። መፀየፌ ሲበዛብኝ ጊዜ አየሩ ላይ ቱፍ ብዬ አበስ ገበርኩ አልኩ።

"በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ማለትማ ግብረሰዶማዊነትን ስንቀበል ነው። በሀይማራኖት ራሱ ለምሳሌ በቁርአን በግልፅ ተቀምጧል። አይፈቀድም። ክርስቲያን ጓደኞቼም ቢሆኑ እንደሚሉት ከሆነ በእነሱም አይፈቀድም።" አለች ኤልሀም። እንደገመትኩት ሙስሊም ናት ብዬ አሰብኩ።

"እሱማ ዘፈንም የተከለከለ ነው። ግን ዘፈን ሊቆም አልቻለም።" አለ ቴድሮስ ፈጠን ብሎ።

"ርዕሱን አንልቀቅ። አሁን እኮ ይህንን ነገር ቢያደርጉ የማይገርመው በልተው የጠገቡቱ ናቸው። እርዳታ እንሰጣለን፡ ፊልማችንን እዩ እያሉ ይህንን ነገር ወደ ሀገራችን ያስገቡት እነሱ ናቸው። እኛ የራሳችን ባህል ያለን ሰዎች ነን። ራሳችንን እንደነሱ ባንቆጥር ጥሩ ነው።" አለችና ኤልሀም መለሰች።

"ግን እኔ የሰማሁት ነገር አለ።ገጠር… ስሙን መጥቀስ አያስፈልግም። አዲስ ሙሽራ ሊሆን ያለ ወጣት ከሰርጉ በፊት ወንድነቱን ሄዶ የሚፈትሽበት አንድ ሽማግሌ አለ። ሽማግሌው ይከፈላቸዋል። ምን ልልሽ ፈልጌ ነው…ምዕራባውያን ያመጡት ነገር ነው አንበል። ሁሉን ነገር ምዕራባውያን ላይ ለድፈን እንዴት እንዘልቀዋለን? እነዚህ ሰዎች ስልጣኔ ገና አልገባቸውም ግን ማንም ሳይነግራቸው ራሳቸውን እንደዚህ  ሆነው ነው ያገኙት።"

" ከየትም ይምጣ! ከሰማይም ይውረድ፡ ከመሬትም ይፍለቅ። ግብረሰዶማዊነት መበረታታት የለበትም። ጤነኝነት አይደለም።" አለች ኤል ሀም።

" እሱ እኮ ነው ችግሩ። ግብረሰዶማውያን ጤነኞች ናቸው! አገሪቱ የምትጠብቅባቸውን ነገር ማበርከት ይችላሉ። አናግላቸው እንቀበላቸው" አለ ቴድሮስ። ድምፁ እየተለወጠበት መሆኑን አስተዋልኩ።

" ቴድሮስ ሱሰኞች እኮ ጤነኞች ናቸው። ከጥቂቶች በስተቀር መንገድ ለመንገድ የሚዞሩ አይደሉም። ግን ሁሉም ደሞ ጤነኞች አይደሉም። ሱሳቸውን ለማርካት ሲሉ የህዝብ ሀብት የሚመዘብሩ፡ ሰዎች የሚገድሉ አሉ። ጥፋት የሚያደርሱ ሱሰኞች በጣም አሉ። እንዲህ አይነቶቹን እንዴት መርዳት እንችላለን የሚለውን ነው አሁን እየተነጋገርንበት ያለነው። አይ፤ ተውኝ! ሱሴን ተቆጣጥሬ ጉዳት ሳይደርስብኝ ሌሎችንም ሳልጎዳ መኖር እችላለሁ የሚል ካለ ደሞ ተደብቆ መቀጠል ይችላል። ግን እስከ መቼ? ነው ጥያቄው።" አለች ኤልሀም። ቴድሮስ ለአፍታ ድምፁ ጠፋና መልሶ ብቅ አለ።

"አድማጮቻችን እየተነጋገርን ያለነው ሱሰኝነት ላይ ነው። በተቻለ መጠን ርዕሱ ላይ አተኩረን እንወያይ። ውይይቱ በሚቀጥለው ሳምንትም የምንቀጥልም ነው የሚሆነው። አሁን ግን አንድ አድማጭ መስመር ላይ አለ…ሄሎ ማን ልበል?"

" ሄሎ…. አገልግል እባላለሁ።" አለ ደዋዩ በቀጭኑ ሽቦ አልፎ። የዚህኛውን ሀሳብ ለመስማት ጓጓሁ። ሰዶማዊነትን የሚቃወም በሆነ ስል ተመኘሁ። የስልኬን ሰዓት አየሁት። ባለቤቴ እና ባለትዳር ጓደኛው ቤት ሊመጡ ጥቂት ደቂቃ ነው የቀራቸው። እዚህ ተዘፍዝፌ ባለቤቴ ቢያገኘኝ ማቆሚያ የሌለው ጭቅጭቁን ይጀምራል።  ልቤ ደሞ በውይይቱስለተንጠለጠለ እንዳያቋርጡኝ ብዬ ሰግቼ እንግዶቼ ዘግይተው በመጡ ስል ተመኘሁ።

" ደስ የሚል ስም ነው ያለህ።" አለ ቴድሮስ።

አመሰግናለሁ ሊል ፈልጎ መሰለኝ አገልግል የተቆራረጠ ሳቅ አሰማ።

" እየተነጋገርን ያለነውን ነገር ሰምተሀል?"

" አዎ" አለ አገልግል" ስለ ሱሰኝነት ነው።" አለ አገልግል። ኤልሀም የሆነ ነገር ልትል ፈልጋ ድምፅ አሰማች። ሆኖም አገልግል የሰማት አልመሰለኝም ገለፃውን ያለማቋረጥ አወረደው።" ግብረሰዶማዊነት ከተፈጥሮ ውጪ የሆነ ድርጊት ነው። እንዲህ የሚለማመዱ ሰዎች የስነልቦና ቀውስ ውስጥ ያሉ ናቸው። ሱስ ብቻ አይደለም በጣም አስከፊ ረቀቅ ያለ የመንፈስ በሽታ ነው…" አለ አገልግል። ይህን ጊዜ ቴድሮስ ጣልቃ ገባ።

"ቆይ ቆይ አቶ አገልግል? በጭፍን ከመናገር ይልቅ የራስህ ተሞክሮ ካለ ብታካፍለን ጥሩ ነው። ሀኪም ነህ? ይህን መልስልኝ። አለበለዚያ ሀሳብህን ተቀብለናል በዚሁ እንሰነባበታለን።"

"አይ ሀኪም አይደለሁም። ግን ባነሳችሁት ርዕስ ላይ ተሞክሮ አለኝ።" አለ አገልግል። " ያደኩት በጣም ሰፊ እጓለሞታ ውስጥ ነው። እዛ እያለሁ በተቆጣጣሪያችን በተደጋጋሚ ለመደፈር በቅቻለሁ። ለመናግር ስሞክር የሚያምነኝ ጠፋ። ሲብስብኝ ጊዜ እጓለማታውን ትቼ ጎዳና ላይ ወጣሁ። ማንም የማውቀው ሰው ስላልነበር ጓደኞቼ ዘመዶቼ ጠባቂዎቼ ጎዳና ላይ ያሉት ልጆች ሆኑ።"

" በመደፈርህ ምክንያት ጎዳና ላይ ከመውደቅ ውጪ ሌላ የደረሰብህ ነገር ነበር?" አለች ኤልሀም። ቴድሮስም ከሷ ተከትሎ ተናገረ።

"ስለሱሰኝነት እየተናገርክ አይደለም አቶ አገልግል።" አለ ቴድሮስ

"ልመጣልህ እኮ ነው። ወንዶች ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አደረብኝ። ነገር ግን ከወንድ ጋር እንድገናኝ ይገፋፋኛል። በህልሜ ሳይቀር ወንዶች ሲገናኙ አይና ባንኜ እነሳለሁ። ከዛ ፈፅሞ መተኛት አልችልም። መስመር የለቀቀ ሂወት ውስጥ ልገባ እንደሆነ ጠረጠርኩ። አይምሮዬ በጣም ይጨነቅ ነበር።" አለ አገልግል። ከስልኩ እጀታ ትንሽ ራቅ ብሎ ኡሁ ኡሁ ብሎ አሳለና እንደገና መናገር ቀጠለ።

"አሁን ከራሴ ጋር መታገሉን ስላልቻልኩት ወደሀይማኖት ሰዎች ሄጄ ሁኔታዬን ነገርኳቸው። በሽታ እንደሆነ ገና ከጅምሩ ስለተጠራጠርኩ ነገሩ በውስጤ አድጎ ሳይሰፋ በፊት በሀይማኖት ሰዎች እርዳታ ቶሎ እርምጃ ወሰድኩበትና ከውስጤ ነቅዬ ጣልኩት።"

" እኔ አሁንም ሱስ የቱ ጋር እንደሆነ አልገባኝም።" አለ ቴድሮስ የአገልግልን ንግግር አቋርጦ።

"ወንድሜ እመነኝ በዚህ ነገር የሚሰቃዩ ብዙ ናቸው። ሂወቴን የቀየረውን ነገር ልንገራችህ። ጎዳና ላይ እያለሁ ብረታ ብረት ብሎኖች ቁርጥራጮች የመሳሰሉትን እየሰበሰብኩ እሸጥ ነበር።" አለ አገልግል። ኤልሀም ጣልቃ ስትገባበት ጊዜ አገልግል ቶሎ ፀጥ ብሎ አዳመጠ።

"አሁን ምን ደረጃ ላይ ነህ? ይቅርታ ስላቋረጥኩህ።" አለች ኤልሀም።

" እግዚ/ር ይመስገን አሁን ጥሩ ደረጃ ላይ ነኝ። ሰራተኞች ቀጥሬ አሰራለሁ። ጎን ለጎን ራሴ ያቋቋምኩት የበጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ነኝ።"

" እሺ ቀጥል ሀሳብህን።" አለች ኤልሀም

"እሺ እና አንድ ምሽት ለመተኛት ተጋድሜ ሳለ ከሁላችንም የሚያንሰው ትንሽ ልጅ ይመጣና እንዲህ አይነቱን ብረት ስጠኝ ብሎ ይወስዳል። እንቅልፌ መጥቶ እያንጎላጀሁ ነበር። ልጁ ተመልሶ መጥቶ ይህን አይነት አይደለም ሌላ አይነት ነው እያለ ሶስቴ ይሁን አራቴ ተመላለሰ። በቃ የፈለከውን ብሎን ውሰድ፤ ጠዋት እንነጋገራለን ብዬው ብቻ ሳንጎላጅ ሳለሁ የሆነ ለስለስ ያለ ነገር ቆዳዬን ሲነካው ላስቲኳ ቤቴ ውስጥ እባብ የገባ መስሎኝ በርግጌ ተነሳሁ። ሳይ ትንሹ ልጅ መለመላውን ሆኖ ከአጠገቤ ተጋድሟል። እንዴት እንደበብኩት ልነግራችሁ አልችልም።"

" አቶ አገልግል ሰዓት እየሄደብን ስለሆነ ፈጠን ፈጠን በልልን። ዝርዝሩን ተወውና ዋና ሀሳብህን አስተላልፍ።" አለ ቴድሮስ። ይሄ ቀዥቃዣ መጨረሻውን ሳልሰማ እንዳያቋርጠው ብዬ ስጋት ገባኝ።

" እሺ። በቃ ባደረገው ነገር ተበሳጭቼ ልጁን ስደበድበው ምንም ጩኸት ሳያሰማ እዛው ተገላበጠብኝ በኋላ እጄ ላይ እንዳይሞት ፈርቼ መደብደቡን አቆምኩ። ከተረጋጋሁ በኋላ ምን ሆነህ ነው ግን? ብዬ ስለው ማልቀስ ጀመረ። እሱም እንደኔ ተደፍሮ ነበር። ከውስጡ እንዳያወጣው አቅም አጣ። እንዳይረሳው ነፍሱ አላርፍ አለች። ማድረግ ባይፈልግም ራሱን ሲያደርግ ያገኘዋል። እባክህ ከዚህ ነገር አላቅቀኝ ወይ አሁኑኑ ግደለኝ እያለ ሌሊቱን በሙሉ ሲያለቅስ አነጋው። እኔም አብሬው አለቀስኩ። ያን ጊዜ ወሰንኩ። እንዲህ አይነት ሰዎችን መርዳት አለብኝ ብዬ ለራሴ ቃል ገባሁ። እግዚ/ር ረዳኝና ከጎዳና ሂወት ስወጣ ማናቸውንም አይነት ሱሰኞችን የሚረዳ በጎ አድራጎት ድርጅት አቋቁሜ አሁን እያሰራሁ እገኛለሁ።" አለ አገልግል

"እስቲ ንገረን ምን አይነት ሱሰኞች ይመጣሉ ? እስቲ ንገረን" አለች ኤልሀም። የኔም ጥያቄ ነበርና አልሀም ጥያቀውን ስታነሳው አዕምሮዬን ያነበበች መሰኝ።

"ሁሉም አይነት ናቸው የሚመጡት። የሀሺሽ፡ የሲጋራ፡ የመጠጥ፡ የዝሙት፡ የራቁት ፊልም… በቃ ሁሉም አይነት። በጣም የሚገርመኝ እኔ ጋር ከሚመጡት መሀል ከግማሽ በላይ ከተፈጥሮ ውጪ በሆነ ግብረስጋ ግንኙነት በሽታ የሚሰቃዩ ናቸው። ከነዚህ መሀል ደግሞ ግብረሰዶማውያንን ዋነኞቹ ናቸው። ደስ የሚላው ያ ትንሽ ልጅ አሁን ነጭ ጋዎን አጥልቀው እነዚህን ሰዎች ከሚረዱት የስነልቦና አማካሪች መሀል አንዱ ነው። አብሮኝ ይሰራል።"

" እህ…" አለች ኤልሀም። ቴድሮስም በአገልግል ታሪክ እንደተመሰጠ አሰብኩ። እኔ ተመስጬ ነበር።

" በርግጠኝነት የምነግራችሁ ብዙ ብዙ በጣም ብዙ ሰዎች ከዚህ በሽታ መላቀቅ እንደሚፈልጉ ነው።" አለ አገልግል።

"ምናልባት ይህንን እርዳታ ማገኘት የሚፈልጉ አድማጮች ሊኖሩ ስለሚችሉ ፈቃደኛ ከሆንክ የድርጅትህን ስምና ሊያገኙህ የሚችሉበትን አድራሻ በቀጥታ ማስተላለፍ ከፈግክ እድሉን ሰጥቼሀለሁ።" አለች ኤልሀም። እንደዛ ሲለባለብ የነበረው ቴድሮስ ድምፁ ጠፋ።

"ያው እኔ ከዚህ ችግር የተላቀኩት በወንጌል ነው ከሚል ሀሳብ ተነሳስቼ የድርጅቱን ስያሜ ወንጌል የሱሰኞች መልሶ ማቋቋሚያ የሚል ስም ሰጥቼዋለሁ። ከስራው ታላቅነትና ስፋት አንፃር በርከት ያሉ ሰራተኞችን መቅጠር አለብን ግን ያለብን የአቅም ውሱንነት ያን አልፈቀደልንም። ግን ባለችን አቅም ተጠቅመን ብዙ ሰዎችን ለመርዳት ጥረት እያደረግን ነው።" አለ አገልግል

" በጎ አድራጊዎች ወይም እርዳታውን ማግኘት የሚፈልጉ በየት በኩል ሊያገኙህ ይችላሉ?" አለች ኤልሀም።

"7771777 በዚህ ስልክ ቁጥር ደውለው ሊያገኙኝ ይችላሉ" አለ አገልግል። ቶሎ ብዬ ቁጥሩን ስልኬ ላይ መዘገብኩት። ቀጥሎ አወያዮቹ ተሰናበቱና ዘፈን ተለቀቀ። ብድግ ብዬ ሂጄ ጣቢያውን ቀየሬ የመዘገብኩትን ቁጥር እየመታሁ በረንዳ ላይ ወጣሁ። ስራዬን አገብድጃለሁ። የደወልኩት ስልክ ተነሳ።

"ሄሎ። አቶ አገልግል?" አልኩ።

"ነኝ ማን ልበል?" አለ በዛኛው በኩል ያለው ድምፅ።

"ቅድም ሬዲዮ ላይ ሰምቼህ ነው። በገንዘብ ልረዳህ እፈልጋለሁ። በሀሳብና በጉልበትም የምችለውን ያክል አግዝሀለሁ።" አልኩት።

"ኦው በጣም ጥሩ። መጀመሪያ ግን ሱሰኞችን የሚወድ ልብ ሊኖርሽ ይገባል። አንቺ ልበልሽ?" አለ አገልግል። ፈቀድኩለት። "ስራው ትዕግስት የሚጠይቅ ነው።ይህን የሚያደርጉት አውቀው ነው የሚል ሀሳብ በውስጥሽ ፈፅሞ መኖር የለበትም። አለበለዚያ ልፋትሽ ሁሉ ሲባዛ ዜሮ ነው የሚሆንብሽ። በርግጥ እንዲህ አይነት ሰዎችን ለመርዳት ከፈለግሽ ልክ ተጠፍንጎ ታስሮ ሞቱን የሚጠባበቅ እስረኛ ልትፈቺ እንደምትሄጂ ሁሉ ለነሱ የሀዘኔታ ልብ ሊኖርሽ ይገባል። ስራው ታይታ የሚፈልጉ ሰዎች የሚሰሩት አይደለም። ይከብዳቸዋል።" አለኝ።

" ምን ማድረግ አለብኝ?" አልኩት።

"ስለወንጌል የምታውቂው ነገር አለ?"

"በፊት ሚስዮን ቤት ያስተምሩን ነበር። አብዛኛውን ረስቼዋለሁ። አሁን ቤ/ክ የምሄደው ታላቅ የንግስ በዓል ያለ ጊዜ ወይ የበዓል ጊዜ ብቻ ነው።"

"ፈቃደኛ ከሆንሽ ስለወንጌል በደንብ እናስተምርሻለን። አይ ይቅርብኝ። እንዲሁ አብሬያችሁ እንድሰራ ፍቀዱልኝ ካልሽም ትችያለሽ። ወንጌል ከኑክሊየር የበለጠ ሀይል አለው። የመለወጥ ሀይሉን እዚህ ከመጣሽ በኋላ በምትሰሚያቸው የግለሰቦች ታሪክ ታረጋግጫለሽ።" አለ።

"ፈቃደኛ ነኝ።" አልኩ። የሚገኝበትን አድራሻና ቀን ቀጠሮ ተለዋውጠን ስልኩን ስዘጋ የግቢው በር ተከፍቶ የባለቤቴ መኪና ገባች። እንግዶቼ መጡ። ባለቤቴ መጀመሪያ ወረደ ከዛ ጥቁር መልክ ያለው ወንድ ወረደ። እጮኛሞቹን ልቀበል በፈገግታ ፊቴን አስውቤ ወደነሱ አመራሁ። መጨረሻ ከመኪናው የወረደችው ግን ሴት አልነበረችም። ነጭ ወንድ ነው። በጣም ደንግጬ አየሁት። ነጭነቱ ሳይሆን ወንድ መሆኑ አይኔን አስፈጠጠኝ። ሆኖም ባለቤቴን ሳየው ባአይኑ የተቆጣኝ መሰለኝ። ልቤ ላይ የቀረው የአቶ አገልግል ምክርም በአይምሮዬ አቃጨለ። ለግብረሰዶማውያን ያለኝን ጥላቻ ዛሬ አውጥቼ እጥለዋለሁ። አዝንላቸዋለሁ ብዬ አሰብኩ። ስራዬን በቅርብ ካገኘኋቸው ከነዚህ ምስኪኖች ልጀምር ወሰንኩ። መኖር እፈልጋለሁ። ከእንግዲ 80 ዓመት እንኳ እንድኖር አምላኬ ቢፈቅድልኝ የምኖረው 27 ዓመት ነው። አይበቃኝም። እንደዚህ ያደጉ ሰዎችን መርዳት ደግሞ ውስብስብና ከባድ ነው። ቢሆንም እርዳታዬን ከአሁኑ መጀመር አለብኝ። ፈጣሪ ኮሌጅ የገባውን ወንድ ልጄን እንዲጠብቅልኝ እየተማጸንኩ ባለቤቴንና ግብረሰዶማዊ እንግዶቼን ሞቅ ባለ አቀባበል ወደውስጥ እንዲገቡ ጋበዝኳቸው።

                                                                               ፍ ፃ ሜ

ይህ ታሪክ ልቤን ነክቶታል። እርዳታ እፈጋለሁ የሚል ካለ በኢሜይል  yetibeblisan@ymail.com  ሊያገኙኝ ይችላሉ። ጭንቀት ይዘው አይቀመጡ። ፃፉልኝ እንነጋገር።

translation

         


በተከታታይነት ታትሞ የሚወጣ

 

 

 

 

 

 

 

እግዚአብሔር የሚሸልመው ሕይወት

ዛሬ የምታከናውናቸው ማናቸውም ተግባራት ለሁልጊዜም አስፈላጊ ሆኖ ለምን ይወሰዳል?

 

 

 

 

 

ብሩስ ዊልኪንሰን

ከዴቪድ ኮፕ ጋር በመተባበር

 

 


ማውጫ

መግቢያ.. 1

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ወደ ኮከቦቹ የሚያመራ የቁልፍ ቀዳዳ</b>.. 2

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ሊቋረጥ የማይችል ግንኙነት</b>... 9

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ስለ ሽልማት መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይለናል</b>... 17

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">የዚያች ቀን</b>.. 26

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">የሕይወትህ ጥያቄ</b>.. 35

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ዋጋን መልሶ የሚሰጥ እግዚአብሔር</b>.. 44

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">የመጀመሪያው ቁልፍ</b>... 53

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ለዘላለም ወደ ሆነው ነገር መመልከት</b>... 63

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


 

 

መግቢያ

 

ውድ አንባቢ፣

          ዛሬ በምትሰራውና ነገ ለዘላለም በሚገጥምህ ሕይወት መካከል ስለሚኖረው ግንኙነት በማስመልከት ኢየሱስ ያስተማረውን ትምህርት ልትቀስም ነው፡፡

         ኢየሱስ ሁለት ነገሮች የዘላለም ሁኔታዎችን ሊወስኑ እንደሚችሉ ገልጿል፡፡ እነዚህንም እንደ ቁልፍ አድርገህ አስባቸው፡፡ የመጀመሪያው ቁልፍ እምነት ሲሆን ይህም ወደ ዘላለም መዳረሻህ ሊወስን የሚችል ነው፡፡

        ሁለተኛው ቁልፍ ግን ምንድን ነው? ከእግዚአብሔር የሚገኘውን መዝገብ እንዲገኝ በምን ሁኔታ ያግዛል? ለምን ኢየሱስ በልዩ ሁኔታ በዚህ ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጠበት?

        የዚህ መፃሀፍ አብይ ትኩረትም በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው፡፡

        ኢየሱስ በማንኛውም ሀይማኖትም ሆነ በየትኛውም የዓለም ክፍል ትልቅ መምህር እንደሆነ ይታወቃል፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ግን ተከታዮቹንም ጨምሮ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዛሬም ኢየሱስ እግዚአብሔር ስለሚሸልመው ሕይወት የተናገረውን ያስተዋሉት አይመስልም፡፡

        በዚች አነስተኛ ፁሁፍ ላይ የሰፈረው መልዕክት ከእግዚአብሔር ስለምትጠብቀውና በአፅኖት ለእርሱ ለማድረግ በምትፈልገው ጉዳይ ላይ ዛሬ ከፍተኛ የሆነ ለውጥ ለማምጣት አቅም አለው፡፡ በፀሎትና በልዩ ጉጉት ይህችን መፅሃፍ እንደምታነበው ተስፋ አደርጋለሁ፡፡

         ከምሥጋና ጋር፣

              ብሩሰ ዊልኪንሰን

 

 

 


 

                                  1

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ወደ ኮከቦቹ የሚያመራ የቁልፍ ቀዳዳ</b>

“እነሆ፡ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ፤ዝለሉም”

ኢየሱስ በሉቃስ 6፡23

 

ሬ ለቀሪው የሕይወትህ ዘመን በእርግጥ የመጀመሪያዋ ቀን ብትሆንስ? ዛሬ የንግድ ተግባርህን ማለትም ልታከናውነው የሚገባህን ሥራ ጨርሰህ በምትኩ ከእግዚአብሔር ልታገኝ የሚገባህን ነገር በመጠባበቅ ላይ ብትሆን፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነህ ወደ ዘላለም ወደሚባለው ምዕራፍ ውስጥ ለመግባት በመንደርደር ላይ ብትሆን፡፡

 

     ምን ዓይነት የተለየ ጊዜ ነው! ምን ዓይነት አስገራሚ የንግድ ልውውጥ ነው! ማለቂያ የሌለውን የእግዚአብሔርን ቀን ከመቅፅፈት የምትመለከትበት ሁኔታ መኖር፡፡ በማንኪያ ለምትጨለፈዋ ውሃ በአማዞን ወንዝ ውስጥ ያለውን ውሃ ማግኘት፡፡

    አንድ ደረጃ ወደፊት ማለት፡፡ በእጅ መዳፍ የምታክለዋን ጊዜ ጥሎ ዘላለም የሚሆን ሕይወትን ማንሳት…..

  ቀላል የሕይወትህ ምርጫ የሚባሉትን ማለትም ከአለቃህ ጋር በምን ሁኔታ ግንኙነት መፍጠር እንዳለብህ፣ ማንን ራት መጋበዝ እንዳለብህ እና የመሳሰሉትን በቀጣይነት ሊፈጠር ስለሚችለው ሁኔታ የራሳቸው የሆነ ውጤት እንዳላቸው ብነግርህስ?

   ይህ ሁኔታ ያስደንቅሃል?

   አሁን በያዝካት ትንሽ መፅሃፍ በአሁን ጊዜ ለምናከናውናቸው ተግባራት በዘላለም የሕይወት ምዕራፋችን ውስጥ ወሳኝ ድርሻ እንደሚጫወት ኢየሱስ የገለፀውን ሃሳብ ትገነዘባለህ፡፡ በሚያስገርም ሁኔታ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢየሱስን የተከተሉ ሠዎች ኢየሱስ የተናገረውን ነገር በውል ያልተገነዘቡ አሉ፡፡

  አንተም ከነዚህኛዎቹ ውስጥ አንደኛው ትሆን?


 

     እኔ ነበርኩኝ፡፡ እኔ በየጊዜው ቤተ ክርስቲያን ከሚከታተሉ ቤተሰብ ውስጥ ያደኩኝ ከመሆኑም በላይ ከልጅነት አንስቶ መፅሃፍ ቅዱስን እንድማርም ተደርጌያለሁ፡፡ በኃላ ግን ለዘጠኝ ዓመታት ያህል የቲዎሎጂ ትምህርት ሥልጠና ወሰድኩኝ፡፡ በዚህ መፅሃፍ ውስጥ የተመለከተው ርዕሰ ጉዳይ ልክ አንድ ሠው በቤቱ ውስጥ ያለን ዕንቁን ማወቅ እንዳልቻለ ሁሉ ለመረዳት አስቸግሮኝ ነበር፡፡ በስተመጨረሻ በዚህ ጉዳይ ላይ ኢየሱስ ያለውን ነገር ስረዳ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርጉም ሊሰጥ የሚችል ንሮ ለመኖር እንድችል በር ከፈተልኝ፡፡

    ወደ ፊት ምን ሊገጥመን እንደሚችል በውል አሁኑ ማወቃችን አሁን ለምንኖረው ሕይወት ድጋፍ እንደሚሰጠን ራሳችንን ልናሳምን ይገባናል፡፡ ለእኛ ምቹ ሁኔታን ይፈጥሩልናል ብለን የምናስባቸውን አስተሳሰቦች ዘልቀው እንዲቆዩ በምናደርገው ርብርብ ወደፊት ትክክለኛውን የሆነውን እውነት እንዳንመለከት ይጋርድብናል፡፡ ልክ ህፃናት በቁልፍ ቀዳዳ በሰማይ ያለውን ክዋክብትን ለመቃኘት እንደሚሞክሩት ዓይነት ይሆንብናል፡፡

    እውነታው ግን በቁልፍ ቀዳዳ የምንመለከተው በጣም ትንሽ የሆኑትን ትዕይንቶችን ሲሆን መመልከት የሚገባን ግን በሰፊው ነው፡፡ ስለሆነም ኢየሱስ የቁልፍ በሩን ከፍቶ ሰፊ የሆነውን ነገር ሊያሳየን ይፈልጋል፡፡

    ብዙ ብዙ ነገሮችን፡፡

ለመደነቅ ራስን አሰናዳ

    ከሕይወት በኃላ ሊገጥመን ላለው እውነታ ከናዝሬቱ ኢየሱስ በስተቀር ማንም በልዩ ሁኔታ ያስቀመጠ የለም፡፡ የእርሱ አስተምሮት የተከታተሉት በትምህርቱ ተደንቀዋል፤ አፋቸውን አዘግቶዋቸዋል ብሎም እንዲቆጡም አድርጎዋቸዋል፡፡ በ 12 ዕድሜው ለመጀመሪያ ጊዜ ለሕዝብ ለመጀመሪያ ጊዜ የታየበትን ሁኔታ እንደአብነት አድርገን እንውሰድ፡፡ “የሰሙትም ሁሉ በማስተዋሉና በመልሱ ተገረሙ” (ሉቃስ 2፡47)

 

    ኢየሱስ መደበኛውን የአገልግሎት ጊዜውን ሲጀምር ሁሉም በአስተምሮቱ “ተደነቁ” (ማቴ 7፡28) የተራራው ስብከበት በሚባለው ስብከቱ ኢየሱስ፡-

     “ሰዎች ሰለ ሰው ልጅ ሲጠሉዋችሁ ሲለዩአችሁም ሲነቅፋችሁም ስማችሁንም እንደ ክፉ ሲያወጡ ብፁዓን ናችሁ፤ እነሆ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና” ሉቃስ 6፡22-23

    ከላይ የተመለከተውን ጥቅስ በደንብ ታውቀው ይሆናል፡፡ ይህንን ጥቅስ በአፅንኦት ከማንበቤ በፊት መቁጠር አይሆንብኝና ለደርዘን ያህል ጊዜ ያነበብኩት መሆኔን ልናዘዝ፡፡ ኢየሱስ የተናገራቸው ንግግሮች የሚደንቁ ናቸው፡፡ አይደለም እንዴ? ከዚህ በፊት ኢየሱስ የተናገረው የምረዳው የነበረው “ስለ አኔ በተሰደዳችሁ ጊዜ ደስተኛ እንደምንሆንና ከደስታችን የተነሳ እንደምንፈነጥዝ” ነበር፡፡

    በጥሞና ሆናችሁ በምታነብቡት ጊዜ ግን ኢየሱስ ሊል የፈለገው ከላይ የተመለከተውን ሃሳብ አይደለም፡፡ ቀጠል አደረገና፡-

    “እነሆ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ ዝለሉም፤ አባቶቻቸው ነቢያትን እንዲህ ያደርጉባቸው ነበርና” ቁጥር 23

    ከላይ የተመለከቱት  ኢየሱስ የተናገራቸው ውስን ቃላቶች እኔ እና አንተ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብንሆን ለምን እንደምንደሰት የሚገልፅ ነው፡፡ ለምን? ለዚህም ምክንያቱ ለእርሱ ብለን በዚህ ምድር የምናደርጋቸው ማናቸውም ተግባራት በሰማይ ኢየሱስ “ትልቅ” የሆነ ለእኛ ባዘጋጀው ነገር ላይ ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት ያላቸው በመሆኑ ነው፡፡

    አንድ ሰው ማድረግ ያለበትን ተግባር በመተግበሩ ምክንያት የሚያገኘው ሽልማት ለምሳሌ አንድ ሰው በማመኑ ምክንያት ከሚያገኘው ስጦታ እንደሚለይ ኢየሱስ በተናገረው ሃሳብ ልዩነት እንዳለው ልንገነዘብ ያሻናል፡፡ ከዚህም ባለፈ የሚሰጠው ሽልማት አንድ ሰው ሊያደርገው የሚገባ ግላዊ እና ልዩ ነገር በመኖሩ ሲሆን የሚጠበቀውን ድርጊት ካላከናወነ (ለምሳሌ ከስደት የተነሳ የምንሸሽ ከሆነ) ሽልማቱን እንደማናገኝ ነው፡፡

    ኢየሱስ በእርሱ ምትክ መከራ እንድንቀበልና እንድንደሰት እንዳልተናገረ ልታስተውሉ ትችላላችሁ፡፡ ይልቁንም ኢየሱስ በሰማይ ሊገጥመን የሚችለውን ውጤት በምድር ከምናከናውነው ተግባር ጋር  መቆራኘቱ አስገራሚ በመሆኑ ይህንን እውነታ ማወቁና ትልቅ ሚስጥሩንም መረዳት አሁን በምን ሁኔታ መኖር እንዳለብን ከፍተኛ የሆነ ለውጥ እንድናደርግ ስለሚያስችለን ነው፡፡ ትክክል ነው ከዚህም አልፎ ያልተጠበቀ ደሰታ ባላሰብነው ሁኔታ ከውጣችን አፈትልኮ እንዲያወጣ የሚያስደርግ እውነታ ነው!

    በሰማይ የምናገኘው ሽልማት አስመልክቶ ኢየሱስ ያስተማራቸው ትምህርቶች እንደሚነጣጠሉ አድርገን ልንወስዳቸው አይገባም፡፡

·         “የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል፡፡” (ማቴዎስ 16፡27)

·         “ኢየሱስም ፍፁም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድሆዎች ስጥ፤ መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤መጥተህም ተከተለኝ አለው፡፡” (ማቴዎስ 19፡21)

·         “የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤በፃድቃን ትንሳኤ ይመለስልሃልና፡፡” (ሉቃስ 14፡14)

    የእነዚህን ጥቅሶች በምትመረምርበት ጊዜ በውጣቸው የያዙት መልዕክት እንደምታ ትልቅ ነው፡፡ በአንድ በኩል ስንመለከተው እግዚአብሔር በየዕለቱ ልንጓዝበት የሚገባውን መንገድ ግልፅ የሚያደርግ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ከምንገምተው በላይ እርሱን በማገልገላችን የተነሳ ትልቅ ነገር እንደምናገኝ ነው፡፡

ወደተገባ ተስፋ ቃል መጓዝ

ይህንን መፅሃፍ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ምክንያት ምን እንደሆነ ልግለፅልህ፡፡ እ.ኤ.አ በ1885 ኢየሱስ በሰማይ የምናገኘውን ሽልማት አስመልክቶ የተናገረውን ሀሳብ ስረዳ በጣም ተደነኩኝ፡፡ አብዛኛዎቹን የተናገራቸው ትምህርቶች ከዚህ ቀደም ከተማርኩትና ከማምንበት ጉዳይ አፈንግጦ የወጣ መስሎ ታየኝ፡፡

    ከዚህ የተነሳ እውነቱን ለማወቅ ዘላለማዊ ሽልማትን አስመልክቶ የተጠቀሱ ጥቅሶች ላይ  ጥልቅ የሆነ ምርመራ ውስጥ ገባሁ፡፡ ሥነ መለኮታዊና ሙሁራዊ ሥራዎችንም አጠናሁ፡፡ ኢየሱስ ሊያስተላልፈው የፈለገውን ትክክለኛ መልዕክት ለመረዳት በተቻኮልኩበት ፍጥነት ውስጥ ለሠዓታት ያህል ማውጠንጠን ጀመርኩኝ፡፡ በማስከተል በብዙ ሚሊዩን የሚቆጠሩ የኢየሱስ ተከታዮችን ጨምሮ መንፈሳዊ ተግባራትን ለማከናወን የሚፈልጉ ሠዎች ትልቅ የሆነ እውነታ እና ተስፋ በትክክሉ እንዳልተመለከቱት አምኜ ወደ ትክክለኛው መንገድ መመለስ እንዳለብኝ ተገነዘብኩኝ፡፡

    ከአምስት ዓመታት ጥልቅ ጥናትና ከአስራ ሁለት ጥራዝ ምርምሮች በኃላ ያገኘኃቸውን ውጤቶች በማጠናቸው ሼልፎችን ላይ ማስቀመጥን ቀጠልኩበት፡፡

    አንድ ቀን በኦሪጎን የዌስተርን ሴሜናሪ ፕሬዝደንት የሆነው ዶ/ር ኤርል ራድማቸር ስልክ ጥሪ አድርጎልኝ ያገኘሁትን ውጤት ለሳምነት በሚቆይ የተመራቂዎች ሰሜናሪ ኮርስ ላይ እንዳቀርብ ጋበዘኝ፡፡ በሽልማት ዙሪያ የሚያጠኑ ምሁራንን ጨምሮ ሌሎች ታዋቂ ሙሁራኖች ተገኝተው የማቀርበውን ሀሳብ እንዲገመግሙ እንደሚደረግ ቃል ከገባልኝ በኃላ በቀረበልኝ ሃሳብ ተስማማሁ፡፡

   የማስተምርበትን ማቴሪያሎቼን ይዤ ከበርካታ ወራት በኃላ በሚያዝያ ወር ጠዋት ወደ ሰሜናሩ ካምፓስ አቀናሁኝ፡፡ ወደ ሌክቸር ማቅረቢያው ክፍል ስደርስ ክፍሉ ከዚህ ቀደም ያላገኘኃቸውን ታዋቂ እና ጥራዝ ነጠቅ የሆኑ ሰዎች ማለትም የግሪክና የዕብራይስጥ ቋንቋዎች ትምህርት ክፍል ሊቀ መናብርት፣ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አዋቂዎች፣የመፅሀፍ ቅዱስ አስተማሪዎች እና ከተለያዩ የእምነት ተቋማት የተወከሉ መጋቢዎች ተገኝተው ነበር፡፡

    በየጠዋቱ ለአራት ሰዓታት ማስተማሬን ቀጠልኩኝ፡፡ በየከሰዓቱ ወደ ዶ/ር ራድማቸር ቤት በማምራት በተነሱት ነጥቦቸ ላይ የተለያዩ ሙሁራን ክርክር ያደርጉበት ነበር፡፡

    አንድ ቀን ሮማናዊ የሆነ የቤተ ክርስቲያን ታሪክ አዋዊ እያጠናንበት ያለው ርዕሰ ጉዳይ አዲስ የሥነ መለኮት ጉዳይ እንዳልሆነ አረጋገጠልኝ፤ ከመጀመሪያ ምዕተ ዓመት አንስቶም የክርስቲያኖች እምነትና አስተምርሆት አካል እንደሆነ በመግለፅ፡፡ ሀሳቡንም ይበልጡንም ለማብራራት “ በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የነበራቸው እንደ አጉስቲን፣ ሉተር፣ ካልቪን፣ ዊስሊ እና እስፐርጆን አንድ የሚያደርጋቸው ነገር ምንድነው?” ብሎ ጠየቀኝ፡፡

    ሀሉም ሰው በጥርጣሬ ሁኔታ ውስጥ በነበሩበት ጊዜ “ሁሉም ዘላለማዊ ሽልማት እንደሚኖር አፅኖት ሰጥተው እንደሚያምኑና ተስፋ የሚያደርጉ በመሆኑ ነው” ብሎ መለሰ፡፡

    ወደ መጨረሻው ሳንምት አካባቢ የተለየ ለውጥ እንደመጣ ተገነዘብኩኝ፡፡ በሌክቸር ክፍል ውስጥ የነበሩት ሙሁራን ከክርክር ከመግባት ይልቅ በተዘጋጀው ማቴሪያል ላይ ያላቸውን ሀሳብ በየተናጥል ይገልፁ ጀመር፡፡ በአንድ የከሠዓት በኃላ ጊዜ ላይ የትምህርቱ ተካፋይ የነበሩት በእድሜያቸው ገፋ ያሉ ሠው ወደ እኔ ጎተት አድርገውኝ “እግዚአብሔር ስለ ዘላለማዊ ሽልማት በልዩ ሁኔታ እንድማር እዚህ እንደመጣሁ አስቤ ነበር” አለና ቀጥሎ “ግን ተሳስቻለሁ፡፡ እዚህ ያመጣኝ ልቤ እንዲቀየር ነው፤ስለዚህም የተቀየረ ፕሮፌሰር ሆኜ እመለሳለሁ” አለኝ፡፡

    በመጨረሻው ቀን ተሰብሳቢዎችን “ ሽልማትን አስመልክቶ ሳስተምራችሁ የነበረው ትምህርት ኢየሱስ ካስተማረው ጋር አብሮ የሚሄድ ስለመሆኑ ታምኑበታላችሁ?” የሚል ጥያቄ ጠየኳቸው፡፡

    “አምነንበታል” በማለት ምላሻቸውን ሰጡ፡፡ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ እኔም ወደ ኃላ አላልኩም፡፡

ሁለቱ ቁልፎች

በዌስተርን ሴሜናሪ ለሳምንት በነበረው የትምህርት ጊዜ የተማመንበትን ሃሳብ ከዚህ ገፆች በኃላ አንተም ትመለከተዋለህ፡፡

    ኢየሱስ ስለ ሽልማት አስመልክቶ የተናገራቸውን ትምህርቶች ለአንተ አዲስ ቢሆንም ባይሆንም በልዩ አፅንኦት ይህንን ንባብ እንድታነብ አበረታታሃለሁ፡፡ በመንፈሳዊ አመለካከት ረገድ ልዩ የሆነ ሃሳብ እንድትጨብጥ ያስችልሃል፡፡

     ኢየሱስ ካስተማራቸው ትምህርት በመጀመሪያ በመነሳት የተለየና ትክክለኛ የሆነ አጠቃላይ የሕይወትህ ምንነት ሊያስረዳ የሚችል ሃሳብ እንገነዘባለን፡፡ ሁልጊዜ የምታቃቸውን ቃላቶች ማለትም ሰማይ፣ መዝገብ፣ ሥራ እና እምነት የሚሉትን በምንባቡ ውስጥ እንጠቀማለን፡፡ ልዩ የሆነውን ሚስጥር ለማብራራት ሲባል እነዚህን ቃላቶችን በምንጠቀምበት ጊዜ ትዕግስት እንዲኖርህ አበረታታሃለሁ፡፡

    የመጀመሪያው ቁልፍ እምነትህ ነው፡፡ ይህ ቁልፍ የዘላለም ሕይወት በር የሚከፍትና ወደ ፊት የዘላለም ሕይወትህን የት እንደምታሳልፍ የሚወስን ነው፡፡

    ሁለተኛው ቁልፍ የአንተ ባህሪ ነው፡፡ ይህኛው ደግሞ የሽልማት በርን የሚከፍትና እንዴት አድርገህ የዘላለም ሕይትህን እንደምትኖር የሚወስን ነው፡፡

    የሁለተኛው ቁልፍ እግዚአብሔር የሚሸልመው ሕይወት ርዕሰ ጉዳይ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ነው፡፡ ምንም እንኳን የአንድ ሰው ባሕሪ (የአንድ ሰው ድርጊት ወይም ሥራ ብለን ልንጠቀም እንችላለን) የወደፊት ሁኔታን ልክ እንደ እምነት የሚወስን ባይሆንም በአሁኑ ጊዜ ሊዘነጋ ከማይገባው በላይ እየተረሳ የመጣንበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ግን ይህ ቁልፍ ይከፍታል በሚል የተነገረለት ተስፋ በተለይ ለኢየሱስ ተከታዮች የሚኖረውን እውነታ መረዳት ቀላል የማይባል ነገር ነው፡፡ ይህንን ምንባብ እንደጨረስክ የእያንዳንዷን የሕይወትህ እንቅስቃሴ በልዩ ሁኔታ እንድትመለከተው ያስችልሀል፡፡ ቀላል ሊባሉ የሚችሉ ውሳኔዎች ማለትም እንዴት ገንዘብን እንደምትጠቀም እንዲሁም እንዴት ጊዜህን መጠቀም እንዳለብህ ትክክለኛ አቅጣጫ እንድትመለከት ያስችልሀል፡፡ ከዚህም ባለፈ ለምታከናውናቸው ለእያንዳንዱ ድርጊት ወደፊት ለሚኖርህ የዘላለም ሕይወት የራሳቸው የሆነ አስተዋፅኦ እንዳላቸው አውቀህ ንሮህን በእርግጠኝነት እንድትኖር ያስችልሀል፡፡

ሠማያዊ አሳነባሪ አስመልክቶ የተነገረ ቀልድ

በመጀመሪያው የዚህ ተከታታይ የመፅሀፍ እትም ውስጥ የያቤፅ ፀሎት በተዘጋጀው ፁሁፍ ላይ በዚህ ዓለም እግዚአብሔር እንዲባርከን፣ ተፅእኖዋችን እንዲያሰፋ ወይም የግዛታችንን አድማስ እንዲያሰፋ እንድንፀልይ እንደሚፈልግ ተምረን ነበር፡፡ የወይኑ ሚስጥር በሚል በቀጣይ በወጣው መፅሀፍ ባለን የግዛት ወሰን ውስጥ ኢየሱስ ጥሩ ሥራዎችን በማከናወን ሰፊ ምርት እንዴት ልንሰበስብ እንደሚገባ የሚያስገነዝብ ነው፡፡

    እግዚአብሔር የሚሸልመው ሕይወት በሚል ርዕስ በተዘጋጀው በዚህ መፅሀፍ ውስጥ በዚህ ምድር ላይ የሰበሰብከው ምህርት በሰማይ ለሚኖርህ ሕይወት ወሳኝነት እንዳለው ከመረዳትህም በተጨማሪ ይህን እውነታ በመረዳትህ ለተሻለ ነገር ሕይወትህ እንዲለውጥ የሚያስችል ነው፡፡

    ዘላለም በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ በሚሰጥበት ጊዜ በጥንቃቄ እና በየዋህነት መሆን እንዳለበት እረዳለሁ፡፡ በዚህ ጉዳይ ላይ ሐሳብ ማንሳት እኛ ልክ በእንጭጭ ላይ ያለች እንቁራሪት የሰማያዊ አሳነባሪ ሕይወትን ለመምሰል እንደምትፍጨረጨር ዓይነት ይሆንብናል፡፡ እኛ በዚህ ጉዳይ ላይ ማብራሪያ መስጠት ልክ በእናት ማህፀን ውስጥ ካሉት መንትዮቹ ውስጥ አንደኛው ሌላውን ከመወለዱ በፊት እና ባለሦስት ብስክሌት ከመንዳታቸው በፊት እንደማስረዳት ያክል እንደሚቆጠር ነው፡፡

    ይህ ሆኖ ሳለ ግን እግዚአብሔር ይህንን እውነት እንድንረዳ ልጁን ወደ እኛ ልኳል፡፡ ስለዚህም በዚህ ረገድ ኢየሱስ የተናገራቸውን ቃላት በልበ ሠፊነት ለመቀበል ፍቃደኛ ሆነን ከተገኘን እርሱ የሚሸልመውን ሕይወት ያለንን እንቅስቃሴ ከአሁን ጀምሮ ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲለወጥ የሚያደርገው ነው፡፡

 

 

 

 


2

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ሊቋረጥ የማይችል ግንኙነት</b>

 

“የሠው ልጅ ከመላዕክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያንጊዜም

ከሁሉም እንደ ሥራው ያስረክበዋል፡፡”

 

ኢየሱስ፤ ማቴዎስ 16፡27

  

ፅበታዊ፡፡ ይህ ነው በመጀመሪያ ደረጃ ልትገነዘበው የምትችለው፤በአጭር ቃል ምንም ዓይነት ሽግግር የለም፡፡ በጊዜያዊውና በዘላለም መካከል ምንም ዓይነት ድልድይ የለም፡፡ ወደ ሠማይ የሚወስደው ረጅም የብርሃን ኮሪደር እያዘገምን መሄድ አይደለም ( ማለትም ለምሳሌ ትክክለኛ ነው ብለህ ያሰብከው መንገድ በድጋሚ አስበህ የምትቀይረው ጉዳይ) አይደለም፡፡ እግዚአብሔር የተናገረውን ነገር መልሰን አጢነን ወደ ትክክለኛ መንገድ የምንመለስበት ምንም ዓይነት ጊዜ የለንም፡፡

    ሁልጊዜ ከቅፅበታዊ ነገር ወደ ቅፅበታዊ ነገር ትሸጋገራለህ፡፡ አንደኛው ቅፅበታዊ ነገር የሚባለው ምድር ስትሆን ቀጣዩ ደግሞ ዘላለም ……...

    በቃ ቅፅበታዊ፡፡

    ከዚያ በኃላ ምን ይከተላል?

    አንተም የብዙዎችን አስተሳሰብ የምትከተል ከሆነ ዘላለም የሚለውን ልክ በዌስት ቴክሳስ እንዳለ አውራ ጎዳና ጠፍጣፋ፣ረዥም እና አሰልቺ አድርገህ ልታስበው ትችላለህ፡፡ ከሞትክ በኃላ በሕይወትህ ያሳለፍካቸው ትላልቅ ክስተቶች በስተዋላህ እንዳለፉ አድርገህ ልትቆጥር ትችላለህ፡፡

    ነገር ግን ኢየሱስ በዚህ ረገድ በአጅጉ ተቃራኒ የሆነ ነገር ገልጿል፡፡ እርሱ ከዘላለም ከሆነው ነገር ወደ ምድር የመጣ በመሆኑ እና ተመልሶም ወደ ዘላለም ወደሆነው ነገር የተመለሰ በመሆኑ ያልተሸራረፈውን ሙሉ እውነት ያውቃል፤ ማለትም ያለፈውን፣ የአሁኑን እና ወደፊት ያለውን ከማወቁም በላይ አንድ ወጥ የሆነ አመለካከት እንዲኖርህም ያግዝሀል፡፡ ለምሳሌ አሁን ምን እየሰራህ እንደሆነ (እግዚአብሔር የሚሸልመው ሕይወት ይኸው እያነበብክ እንደሆነ) ሊቆጠር


 በማይችል እልፍ ጊዜያት በኃላ ሆነህ እንድትመለከት ከማስቻሉም በላይ ወደፊት ሊገጥምህ ስለሚገባው ነገር እንድትዘጋጅ ያስችልሀል፡፡

    ወደፊት ሊሆን ስለሚችለው ነገር ኢየሱስ ለደቀመዛሙርቱ የተናገረውን አስተውል፡-


“የሠው ልጅ ከመላዕክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያንጊዜም

ከሁሉም እንደ ሥራው ያስረክበዋል፡፡”

 

ኢየሱስ፤ ማቴዎስ 16፡27

 

ኢየሱስ  አማኙ የዘላለም ሕይወት ሊለውጥ የሚችል ወደፊት ስላለው የእያንዳንዱ ክስተት ገልፆ ነበር፤ይህም ተመልሶ እንደሚመለስ፣ ሽልማትን እንደሚያመጣ እና ሽልማቱም “እያንዳንዱ ለሠራው ሥራ” እንደሚሆን ነው፡፡ ኢየሱስ አሁንም ዳግመኛ ስላልተመለሰ ደቀ መዛሙርቱ በሰማይ ሆነው ይህንን በዚህ ጥቅስ የገባውን ተስፋ ቃል በመጠባበቅ ላይ ናቸው፡፡

    ይህ ዜና አንተን ያስገርመሃል?

    የሚያስገርምህ ከሆነ በተከታይ የሚሆነውም የሚያስደንቅህ ይሆናል፡፡ ኢየሱስ በዚህ ጉዳይ ላይ የተናገረውን ዋናውን ሀሳብ በትክክል ለመረዳት እንዲያስችልህ በመጀመሪያ ደረጃ ከትልቁ ምስል እንነሳለን፡፡ በዚህ ምዕራፍ ከቁልፍ ቀዳዳው እንጀምራለን፣ኢየሱስ በሩን እንዲከፍተው ይደረጋል እናም በመጨረሻ የእያንዳንዱ ሰው ወደፊት ጥርት ባለ ሁኔታ ለማየት የምንችልበት ሁኔታ ላይ እንደርሳለን፡፡

    እናም ወደፊት የሚኖርህ የእያንዳንዱ የሕይወት መስመር ዛሬ በምትባለዋ ነጥብ እንደምትወሰን ትገነዘባለህ፡፡

ትክክለኛው የዘላለም ሕይወት የሚጀምርበት የጊዜ ቀመር

ኢየሱስ የተናገረውን ነገር አስተውለን ከመረመርነው የእኛ የዘላለም ሕይወት የሚጀምርበት ግልፅና የሚታወቅ የጊዜ ቀመር አለው፡፡ በእርግጥ ኢየሱስ አብዛኛው የሕይወታችን ክፍል ስጋዊ አካላችን ከሞተ በኃላ ነው፡፡

    ከዚያ በኃላ ያለው ሕይወት የአንተ የዘላለም የሕይወት ጊዜ ነው፡፡ ኢየሱስ በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ጊዜ ተናግሯል፡፡ አሁንም አንተ የየትኛው ሀይማኖት ተከታይ ብትሆንም፤አሁን የየትኛው እምነት ለመከተል ብትወስን ወይም ቀጣይ ህይወትህን በምን ዓይነት ሁኔታ ለመተግበር ብትወስንም ኢየሱስ ከዘላለም ሕይወት ጋር በተያያዘ የፃፈው በአንተ ላይም ተግባራዊ ይሆናል፡፡

    ስለ ዝርዝሩ በኃላ እንመጣበታለን ነገር ግን ለአሁን ወደፊት የሚኖርህ ሕይወት የመንገድ አቅጣጫ ሊያሳይ የሚችል ካርታ ላይ እንደተመለከተው የጋራ አገናኝ መንገድ አድርገው ውሰደው፡፡

በዘላለም ሕይወትህ ያሉ ሥድስቱ ዋና ክስተቶች

1.  ሕይወት፡- በሕይወት እንድትኖር እግዚአብሔር በእርሱ አምሳያ አድርጎ ፈጥሮሃል፡፡

ከአሁን እንጀምር፡፡ ምንም እንኳን ለዘላለም ከዚህ በፊት ባትኖርም ከአሁን በኃላ ግን ለዘላለም መኖርህን ትቀጥላለህ፡፡ በውልደትና በሞት መካከል አካል፣ነፍስ እና መንፈስ እንዳለው ሆነህ ትኖራለህ፡፡ (ዮሐንስ 3፡6፤ 4፡23-24፤1 ተሰሎንቄ 5፡23)

2.  ሞት፡-  በአካል ትሞታለህ፤በመንፈስ ግን አትሞትም፡፡

ልክ ውልደት ወደዚህ ዓለም የምትገባበት አጭር መግቢያ እንደመሆኑ መጠን የአካልህ ሞት ደግሞ ከዓለም የምትወጣበት ፈጣን መውጪያ ነው፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ግን አንተ በምድር ካሉት ሌሎች ፍጡራን የምትበልጥ በመሆኑ ነፍስህ እና መንፈስህ ይቀጥላሉ፡፡ ተመልሶ እንደገና ወደምድር መምጣትም ሆነ “የነፍስ ማንቀላፋት” በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ አልተገለፀም፡፡ ኢየሱስ የገለፀው ከሞት በኃላ ነፍስህ በእግዚአብሔር ወይም በሲኦል እንደምትገኝ ነው፡፡ (ሉቃስ 23፤43፤ 2 ቆሮንጦስ 5፡8)

3.  መዳረሻ፡- መዳረሻህ ላይ የምትደርሰው ከሞት በኃላ ሆኖ የሚወሰነውም በምድር ላይ ባለህ ቆይታህ ባለህ እምነት ነው፡፡

የዘላለማዊ መዳረሻህ የሚወሰነው በሕይወት በምድር ባለህበት ጊዜ በኢየሱስ በማመንህ ወይም ባለማመንህ ነው፡፡ (ዮሐንስ 3፡16-18) ኢየሱስ እንዳስተማረው ሠው ከሞተ በኃላ ሁለት ቦታዎች የራሱ መገኛ ሊሆን እንደሚችል ገልጿል፤ ሠማይና ሲኦል (ዮሐንስ 14፡2፤ ማቴዎስ 23፡33). ሁለቱም ዘላለም የሚኖሩ፡፡

4.  ትንሳኤ፡-  የትንሳኤን አካል ታገኛለህ፡፡

ዘላለም በምንኖርበት ጊዜ የትንሳኤ አካል ሁላችንም ይኖረናል፡፡ (ዮሐንስ 5፡28-29) አዲሱ አካላቸን የማይሞት ነው፡፡ (1 ቆሮንጦስ 15) እንደገና በትንሳኤ ሕይወትን ላገኙት ኢየሱስ “ ክቡር ሥጋውን እንዲመስል የተዋረደውን ስጋችንን ይለውጠዋል፡፡” (ፊልጵስዮስ 3፡21)

5.  ዋጋ ማግኘት፡- በምድር ላይ በሰራኸው ላይ ተመርኩዞ ለዘላለም የሚሆን ሽልማት ወይም ዋጋ ትቀበላለህ፡፡

ምንም እንኳን የዘላለም መዳረሻህ የሚወሰነው በእምነትህ ላይ ተመስርቶ ቢሆንም የዘላለም ሕይወትህ እንዴት እንደምትኖር የሚወሰነው በምድር ላይ ባለህበት ጊዜ በሚኖርህ ባህሪ ተመስርቶ ነው፡፡ አማኝ የሆኑ እና ያልሆኑ የመጨረሻው የፍርድ ቀን ወይም ትልቁ ነጭ ዙፋን ሥር የሚዳኙ ይሆናል፡፡ (ዮሐንስ 5፡22፤ 2 ቆሮንጦስ 5፡10፣ ራዕይ 20፡11-15) የፍርድ ውጤቱ አንተ በሰማይ እንድትሆን ወይም በሲኦል እንድትሆን የሚወስን ነው፡፡ (ማቴዎስ 11፡21-22፤23፡14)

6.  ዘላለማዊነት፡- በምድር ላይ ባለህበት ጊዜ ያለህ እምነት እና ተግባር በእግዚአብሄር አልሆዎት ውስጥ ወይም  አልሆዎት ውጪ ለዘላለም ትኖራለህ፡፡

ኢየሱስ ሁሉም ሠዎች ዘላለማዊ የሆነ ንሮ እንደሚጠብቃቸው ተናግሯል፡፡ ያልተቀበሉት “ወደ ዘላለም ወደ ሆነ ቅጣት ውስጥ” የሚገቡ ሲሆን እርሱን የመረጡት በእግዚአብሔር አልሆዎት ውስጥ ለዘላለም ይኖራሉ፡፡ (ማቴዎስ 25፡46) ዘላለማዊነትን አስመልክቶ ኢየሱስ የገለፀው በእእምሮ ላይ ብቻ የተቀመጠ ሳይሆን በእርግጥ ትክከለኛ ሕይወት በትክክለኛ ቦታ ነው፡፡

ከላይ የተመለከተት ሁኔታዎች እንደተጠበቁ ሆነው ወደፊት በሁሉም ላይ ሊከሰቱ የማይችሉ እንደ መከራው ዘመንና የመሳሰሉት ክሰተቶች መፅሀፍ ቅዱስን ልብ ብለህ ካነበብክ ልትገነዘብ ትችላለህ፡፡ ለዚህም ነው ወደፊት ሊከሰቱ የሚችሉ ክስተቶች ሰፋ ባለመልኩ መመልከቱ አስፈላጊ የሆነው፡፡

ትሥሥርን መፍጠር

በወፍ በረር ምልከታ ወደፊት ሊሆን የሚችለውን ነገር ከተመለከትን አሁን የምናከናውናቸው ተግበራት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ ልትገነዘብ ትችላለህ፡፡ አሁን ትክክለኛውን ምርጫ ካደረክ ኢየሱስ ስለወደፊት ሰለሚገጥመን ተስፋና ሽልማት ትልቅ እንደሚሆን ያረጋግጥልናል፡፡

    ለዚህም ነው ብዙዎቹ ያለውን ትስስር በመዘንጋታቸው ሊያገኙ የሚችሉትን ክብር እንዲያጡ የሚያደርገው፡፡ ምንአልባት አንተም እንደዚሁ አሁን ተገንዝበህ ሊሆን ይችላል፡፡

    ወደፊት የሚገጥሙንን ስድስቱ ዋና ክስተቶች ከመንስኤ እና ውጤት ጋር አዛምደህ ከተመለከትከው አሁን ያለው ሕይወትህ ከሞትከ በኃላ ለሚከሰቱ ክስተቶች ቀጥተኛ ግንኙነት እንዳላቸው ልትገነዘብ ትችላለህ፡፡ አሁን በምድር በምትኖረው ሕይወትና ከዚያ በኃላ ላለው ሕይወት የማይታይ አንድ የሚያስተሳስር አገናኝ መንገድ አለ፡፡

    ይህንን ወሳኝ ግንኙነት የማይቋረጥ ግንኙነት ሕግ ብዬ ልገልፀው እችላለሁ፡-

በምድር ላይ የምትመርጣቸው ምርጫዎች በዘላለማዊ

 ሕይወትህ ላይ ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት አለው፡፡

 

የማይቋረጥ ግንኙነት ሕግ ልክ እንደ መሬት ስበት ሕግ አድርገህ ቁጠረው፤የመሬት ስብቱ ባታየውም ባታምንበትም ሁልጊዜ የሚኖር ነው፡፡ በምድር ላይ እያለህ ያደረካቸው ምርጫዎች ከሞትክ በኃላ የሚፈይዱት ምንም ዓይነት ውጤት የለም ብለህ ልትወስን አትችልም፡፡ ይልቁንም የምድር ቆይታህ ምርጫዎች ከሞትክ በኃላ የራሱ የሆነ ውጤት አለው፡፡ ውጤቱም በዘላለም ሕይወትሀ ውስጥ ቀጣይነት ያላቸው ናቸው፡፡

    ወደፊት ከሞት በኃላ የሚገጥመንን ሁኔታዎች ስናይ በዚህ መፅሀፍ ምዕራፍ አንድ ላይ የገለፅኩት ሁለት መሰረታዊ ውጤቶች እንደሚኖሩ አይተናል፡፡  እነዚህም፡-

·         በምድር ላይ ያለን እምነት የዘላለማዊ መዳረሻ ውጤት ነው፡፡

·         በምድር ላይ የምናከናውነው ተግባራት ወደፊት ዘላለማዊ የሆነ ካሳ ለምናገኘው ውጤት ነው፡፡

    በመንስኤ እና በውጤት መካከል ያለውን ግንኙነት ከፊል በሆነ ግንዛቤ ኖሮኝ ነው ያደኩት፡፡ በምድር ላይ ሆኜ የማምነው የዘላለም ሕይወቴ ወዴት እንደሚያልፍ የሚያስረግጥ እንደሆነ አውቅ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በምድር ቆይታዬ የምናከናውናቸው ተግባራት በሰማይ በሚኖረኝ የዘላለም ሕይወት እንዴት እንደማሳልፈው የራሱ ውጤት እንዳለው ግን አላውቅም ነበር፡፡ ግንኙነት የፈጠርኩት በማምነው ጉዳይ ብቻ እንጂ በማደርገው ተግባር ያለውን ግንኙነት አላስተዋልኩም ነበር፡፡

    እስቲ ልጠይቅህ በምትመርጠው ምርጫ እና ወደፊት በሚኖርህ የዘላለም ሕይወት መካከል ግንኙነት እንዳለ ታምናለህ?

    እኔ እንደአስተዋልኩት በዓለም ላይ ያሉ ሰዎች ከላይ ለተመለከተው ጥያቄ ያላቸውን አቋም በሁለት ዋንኛ ዘንጎች የተከፈለ ነው፡፡ የአንደኛው ዘንግ አሁን የእምነት ሁኔታ ወፊት ስለሚኖረን የዘላለም ሕይወት አስመልክቶ ልዩ የሆነ ትኩረት ሰጥተው አሁን ለምናከናውነው ተግባር ግን በዘላለም ሕይወት ለሚኖረን ውጤት አሳንሰው ይመለከቱታል፡፡ በሁለተኛው ዘንግ ያለው አቋም ደግሞ አሁን በምድር ላይ ሳለን ለምናከናውነው ተግባር በዘላለማዊ ሕይወታችን ላይ የሚኖረውን አስተዋፅኦ አጉልተው በሌላ በኩል ግን በምድር ሳለን የምናምነው እምነት በሰማይ ስለሚኖረው ውጤት አቀጭጨው ያዩታል፡፡

    ከላይ ያየናቸው ፅንፍ አመለካከቶች አንደኛውን አጉልተው ሌላውን በማሳነሳቸው ወደፊት ስለሚኖረው ዘላለማዊ ሕይወት ከፊል የሆነ ምስል እንድንመለከት ያስገድደናል፡፡

    በዚህ ረገድ ያስተዋልኩት የዓለም አቀፍ ሕብረተሰብ አመለካከት በአንተም እይታ ውስጥም የሚንፀባረቅ ነው?

    እስቲ አንድ ጥያቄ እስኪ ልጠይቅህ፡፡ በአንተ አመለካከት የትኛው የመንስኤና የወጤት ግንኙነት ደብዝዞ ይታያል?

    አሁን በምንመለከተው በመንስኤ እና በውጤት መካከል ያለውን ግንኙነት በማየት ያለህን አመለካከት አስፍተህ ተመልከት፡፡ አሁን በምድር ላይ ለምታከናውናቸው ተግባራት ወደፊት በዘላለማዊ ሕይወትህ ላይ የራሱ የሆነ ውጤት ለማምጣት አቅም እንዳለው ብትገነዘብ አሁን ስለ ሕይወትሀ ያለህን አመለካከት እንዲለወጥ አያደርገውም ብለህ ታስባለህ? ስለ እግዚአብሔር ያለህ ሃሳብ ምንድን ነው? ከአሁን አንድ ደቂቃ በኃላ የምትወስነው ውሳኔስ ቢሆንስ?

    በምታምነውና በምትተገብራቸው ተግባራት በዘላለማዊ ሕይወትህ ልዩ እና አስደናቂ የሆነ ውጤት እንደሚኖረውና ኢየሱስ እደንድታውቅ የሚፈልግ ሲሆን ከዚህ ውጪ የሆነ አስተሳሰብ ይዘህ ጊዜህን እንድታጠፋም አይፈልግም፡፡

    ከመጨረሻው እስትንፋስህ በኃላ ሊገጥምህ ስለሚችለው ውጤት ምን ይሆናል ብለህ መደነቅም ሆነ ማዘንም የለብህም፡፡ ኢየሱስ ባለው ታላቅ ምህረት የተነሳ አሁን ለምትተገብረውና ለምታምነው እምነት ወደፊት ለዘላለም ሕይወትህ ስለሚገጥምህ ውጤት ያለውን ግንኙነት ግልፅ ሊያደርግልህ ከዘላለማዊ ማንነቱ ወደአንተ መጥቷል፡፡

    ከዚህም ባለፈ ኢየሱስ በመምጣቱ የዘላለም እጣ ፈንታችን እንደ ሥጋት ሳይሆን እንደ ትልቅ ተስፋ አድርገን ልንወስደው ይገባናል፡፡

 

 

ነጥብና መስመር

በየዕለቱ በየምታከናውናቸው የሕይወት ተግባርህ አሁን የምታከናውነው ተግባር ወደፊት በምን ዓይነት ሁኔታ ውጤት እንደሚኖረው ሊያሳይ የሚችል ምስል ላሳይህ እወዳለሁ፡፡

    ከዚህ በታች ነጥብና መስመር ትመለከታለህ፡፡ ነጥቧ ትንሽ ናት ደግሞም በትንሽ ቦታ ላይ የምትገኝ ናት፡፡ በሌላ በኩል መስመሩ ከአንድ ነጥብ ጨምሮ ገፁን ሊያልፍ እስከሚችል ድረስ ሊሄድ እንደሚችል የሚያሳይ ነው፡፡ እስቲ መስመሩ ገፁን አልፍ ማለቂያ እስከሌለው ድረስ የሚጓዝ አድርገህ ውሰደው፡፡

 

·          


    ነጥቧ የምትወክለው አንተ በዚህች ምድር ላይ ያለህን ቆይታ ነው፡፡ ለብዙዎቻችን ግፋ ቢል ወደ ሠባ ዓመት አካባቢ፡፡

    መስመሩ በአንፃሩ የሚወክለው ከሞትክ በኃላ ለዘላለም ያለህን ሕይወት ነው፡፡ ይህም ማለት ከዘላለም እስከ ዘላለም፡፡

    ከላይ ባመላከትነው የጊዜ ቀመር መሠረት በትንሿ ነጥብ ውስጥ የተፈጠሩት ሁኔታዎች በመስመሩ ላይ በተመለከተው ማናቸውም ነገር ላይ የሚወስን ነው፡፡ ምንም ትንሽ የሆነ የሕይወት ምርጫችን በትንሻ ነጥብ ላይ ብትገለፅ ረዥም መስመር ውስጥ ላቅ ያለ አስተዋፅኦ ታበረከታለች፡፡

    ማንኛውም ይህንን ምስል በአእምሮ በአግባቡ የጨበጠ አፋጣኝ እና ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን እድል ይሰጠዋል፡፡ በዚህም መሠረት “ይህ እውነት ከሆነ የእኔን ሁሉንም ነገር ይለውጣል!” ወይም “ለልጆቼ እና አሁንም በሽምግልና ላለሁት ለእኔ ወደፊት በትክክል ሊሆን ስለሚችለው ነገር ተዘጋጅቼበታለሁ ብዬ አላስብም!” በማለት ሰዎች ያላቸውን ምላሽ ሊገልፁ ይችላሉ፡፡ አንዱ ሰው “ሁልጊዜ ነገሮችን በጥሩ ሁኔታ ለመጨረስ እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ሞት የመጀመሪያ በር መሆኑ ደግሞ ያስገርመኛል!” ብሎ ሀሳቡን አጋራኝ፡፡

    ከእንደነዚህ ዓይነቱ ምላሾች አንተም የምትጋራ ነህ? እየኖርክ ያለኸው ለመስመሩ  ነው ወይስ ለነጥቧ?

    ምላሽህ ለነጥቧ የሚል ከሆነ አስፍተህ ነገሮችን  እንድትመለከት የሚያስገነዝብ ነው፡፡ ኢየሱስ ከትንሿ ምርጫህ በመነሳት እንዴት ትልቁን የወደፊትህን ሕይወት ሊለውጥ እንደሚችል ወደአንተ መጥቷል፡፡

    በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎችንም ይህንን ጥያቄ አቅርብላቸው…..


 

3

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ስለ ሽልማት መፅሀፍ ቅዱስ ምን ይለናል</b>

ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሳዎችንም

ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤በፃድቃን ትንሳኤ

ይመለስልሃልና፡፡”

 

ኢየሱስ፤ ሉቃስ 14፡13-14

አንደኛው ሠንበት ጊዜ አንድ ክስተት ተፈጠረ፡፡ በአንድ ታዋቂ በሆነ ሰው ቤት ትላልቅ ሰዎች በሚባሉት መካከል ለኢየሱስ ግብዣ ተደረገለት፡፡ (ሉቃስ 14፡1) እንግዶቹ ወደየመቀመጫቸው በሚያመሩበት ጊዜ የተሻለ ቦታ ለመቀመጥ እርስ በራሳቸው ሲሽቀዳደሙ ኢየሱስ ተመለከተ፡፡

   ወዲያውኑ ኢየሱስ ማንም ሳይጠይቀው ከዚህ በታች የተመከተውን ምክር ለገሰ፡-

  “… ሄደህ በዝቅተኛ ስፍራ ተቀመጥ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፤ ራሱንም  

   የሚያዋርድ ከፍ ይላል፡፡”

ቁጥር 10-11

    ሁሉም ለሥልጣን እና ለቦታ የሚሻኮቱት ተደነቁ፡፡ ኢየሱስ ግን ንግግሩን አልጨረሰም ነበር፡፡ ኢየሱስ ቀጠል አደረገና ሠዎችን በሚገባ ልንቀበል እንደሚገባ በዚህ ሁኔታ አስጠነቀቀ፡-

  “ምሳ ወይም እራት ባደረግ ጊዜ እነርሱ ደግሞ በተራቸው ምናልባት እንዳይጠሩህ ብድራትም

   እንዳይመልሱልህ ወዳጆችህንና ወንድሞችህን ዘመዶችህንም ባለ ጠጎች ጎረቤቶችህንም 

   አትጥራ፡፡”

                             ቁጥር 12

    ምን ዓይነት የሚያስጨንቅ ሁኔታ! ኢየሱስ ለታዳሚዎቹ “ከዚህ በኃላ እነዚህን በዚህ ምሽት የጋበዛቹኃቸው መልሳችሁ አትጋብዙ፡፡” ያለ ይመስላል፡፡

 


 

    ኢየሱስ ምናልባት አንድ ሰው በጓደኞቹ አንዴት እንደሚታይ አሊያም ስለ ማህበራዊ በጎ ስራ ለማውራት ፍልጎ ይሆን? ከዚህ ቀጥሎ ኢየሱስ የተናገረውን ልብ በል፡-

ነገር ግን ግብዣ ባደረግህ ጊዜ ድሆችንና ጉንድሾችን አንካሳዎችንም

ዕውሮችንም ጥራ፤ የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤በፃድቃን ትንሳኤ

ይመለስልሃልና፡፡”

 

 ከቁጥር 13-14

    ኢየሱስ ለታዳሚዎቹ የተደረገውን በጎ ግብዣ ለመንቀፍ ሳይሆን ከዚህ በበለጠ የተሻለና ዘለቄታዊ የሆነ ነገረ በምትኩ እንዴት ማግኘት ስለምንችልበት ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን በይበልጥ ሊያስረዳን የሚችለው ኢየሱስ ብፁዕ የሚለው ቃል ነው፡፡

    ብፁዕ! ሁላችንም በዚህ ቃል ያለን ስሜት ልዩ እንደሆነ እናውቃለን፡፡ የእኔ ቤተሰብ ምሳ ለመብላት ወደ አንድ አውራ ጎዳና መንገድ ሄደን በደረስንበት ምግብ ቤት ደጃፍ የተቀመጠውና ቤት አልባ ለሆነው ሰው ምግብ ልንገዛለት የወሰንበት ጊዜ ነው፡፡ ሴት ልጄ ከምግብ ዝርዝር ውሰጥ የተመረጠውን ቺዝበርገር ለዚያ ሰው ስትሰጠው ያ ሰው በደስታ በፊቱ የተነበበው ፍካታ የሚረሳ አይደለም፡፡ በዚህም ምክንያት አንድ ወዳጅ አገኘን፡፡

    በአውራ ጎዳናው እንደገና ስመለስ ምን ዓይነት ልዩ ስሜት እንደተሰማኝ እኔ የማስታውሰው ነው፡፡ ሽልማት እንዳገኘው ዓይነት ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡ መላ ሠውነቴ የግለት ስሜት፡፡ አዎ ኢየሱስ ትክክል ነበር፡፡ መልሰው መክፈል ለማይችሉ ሰዎች ጥሩ መስራት በእውነት ትክክለኛ በረከት ነው፡፡

    ይህም ሆኖ ኢየሱስ እየተናገረው ያለው ይህንን ጉዳይ አይደለም፡፡

    በዚያች ምሽት ኢየሱስ ሌላ ተጨማሪ ነገር ታሳቢ አድርጓል፡፡

ኢየሱስ ቀጥሎ የተናገረው ንግግር

ከዚህ ቀጥሎ ኢየሱስ የተናገራቸው ንግግሮች ስለ ሽልማት መሰረታዊ ሃሳብ የሚያመራን ነው፡፡

“የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤በፃድቃን ትንሳኤ ይመለስልሃል፡፡”

ቁጥር 14

    በግብዣው ቦታ ላይ የታደሙት ማናቸውንም ቢሆኑ  ስለ ኢየሱስ አስገራሚ መገለጥ ማለትም እግዚአብሔር ስለ መልካም ስራችን ከሞት በኃላ ስለሚከፍለን ዋጋ በሚገባ የተገነዘቡ አይመስልም፡፡ ኢየሱስ የተናገረው ንግግር በዚህ ዘመን ያለነው ብንሆንም በወቅቱ ታደሚያን ከሚያስቡት ሃሳብ ማለትም በዚህ ምድር ላይ ለሰራነው መልካም ስራ እግዚአብሔር በምድር ዋጋ ከሚለው ጋር የሚጋጭ ነው፡፡

    ኢየሱስ የገለፀው ግን በተቃራኒ ነው፡፡ የእርሱ ንግግር እንደሚያሳየው መልሶ ወረታውን ለማይከፍል ሰው የተለየ ጥሩ ነገር ስታደርግለት፡-

1.  ዋጋህን ትቀበላለህ፣

2.  ዋጋህንም የምትገኘው ከዚህ ምድራዊ ሕይወት በኃላ ነው፣

3.  ስትቀበለው ትክክለኛ ባርኮትን ታገኛለህ፣

    በእርግጥ እግዚአብሔር እንደ ባለፅግነቱ መጠን በምድራዊ በረከትም ይባርክሀል፡፡ እግዚአብሔር ትክክለኛ ምርጫና ውሳኔ ስለወሰንን በምድራዊ በረከትም ሊባርከን ይችላል፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ ሽልማት ብሎ በዚህ ጥቅስ ውስጥ የሚያነሳው የተለየ እና ለሕይወታችን አስፈላጊ የሆነ ነው፡፡ በዚህ ምድር ላይ ለምናከናውነው ድርጊት በትክክል ለወደፊት ሕይወታችን ዋስትና እንድናገኝ የሚያደርጉን ነገሮች አሉ፡፡ ሽልማቶቹ የሚመጡት ከመጠየቅ ሳይሆን በድርጊት ላይ የተመሰረተ ሆኖ ሽልማቱም የሚመጣው ከሞት በኃላ ነው፡፡

    ይህንን የሽልማት ምንነትን በአግባቡ ሳትገነዘብ ብትቀር ራስህን ወደ አልተፈለገ አቅጣጫ እንድትሄድ ያደርግሃል፡፡ ልክ እንደነዚህ ዓይነት ጥያቄዎች ማለትም እግዚአብሔርን ባለኝ አቅም ሁሉ እና ልገነዘበው በምችለው መጠን ብዛት ሳገለግለው ቆይችላሁ፤ ታዲያ ለምን የእኔን ቤተሰብ በገንዘብ አይባርክም የሚሉትን እንድታነሳ ያደርግሃል፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር ሁሉን አድርጎትህን ያውቃል ደግሞም ይጠነቀቃል፡፡ ነገር ግን ለእርሱ ብለን አሁን ለምናከናውናቸው ማናቸውም ተግባራት ዋጋችንም ከመሞታችን በፊት እናገኛለን ማለት አይደለም፡፡

    በእርግጥ እኔ እና አንተ ኢየሱስ እንድናገኝ የሚፈልገውን ሽልማት አሁን አይመጣም፡፡ ይህንን እውነታ ኢየሱስ በመጀመሪያው ሥበከቱ ተናግሮታል፤ ከዚያም አልፎ የሀይማኖት ሥርዓትን ሁሉ እናውቃለን በሚሉት ላይም በተደረገ ግብዣም በግልፅ ገልፆታል፡፡

    የሱ ዘላለማዊ ሽልማት የሚመጣው ከዚህ ዓለም በኃላ ሲሆን ሽልማቱም ለማግኘት አሁን በምንሰራው ተግባር ላይ ተመስርቶ ነው፡፡

ኢየሱስ ሽልማት ሲል ምን ማለቱ ነው?

ኢየሱስ ሸልማት ብሎ የሚያነሳውን መፅሃፍ ቅዱስ ደስ በሚል ሁኔታ በሁለት ዓይነት ቃላቶች ነው የሚገልፀው፡፡

    በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 6 ላይ ባለው ኢየሱስ በሰጠው ትምህርት ላይ በግሪክኛው ቃል “ሚስቶስ” ይለዋል፡፡ ቃል በቃል ሲተረጎም ሚስቶሰ ማለት ዋጋ/ደመወዝ ማለት ነው፡፡ “ እነሆ ዋጋችሁ በሰማይ ታላቅ ነውና በዚያን ቀን ደስ ይበላችሁ፣ዝለሉም፤አባቶቻቸው ነበያትን እንዲህ ያድርጉባቸው ነበርና” ይላል፡፡(ሉቃስ 6፡23)

    ኢየሱስ በሌላ ስፍራም ተመሳሳይ የሆነ ቃል በመጠቀም ስለምድራዊ ዋጋም አንስቷል፡፤” …ሠራተኞቹን ጥራና ከኃለኞች ጀምረህ እስከ ፊተኞች ድረስ ደመወዝ ስጣቸው አለው፡፡” ይላል፡፡ ጳውሎስም ጢሞቴዎስን “ለሠራተኛ ደመወዙ ይገባዋል ይላልና፡፡” በማለት ይገልፀዋል፡፡ (1 ጢሞቴዎስ 5፡18)

    ኢየሱስ የተናገረውን በአግባቡ የተገነዘበው “በምድር ላይ እያለህ ደክመህ ከሆነ አሰሪህ ደመወዝህን ይሰጥሀል፡፡ ለእኔም የምትደክሙ ከሆነ ደመወዛችሁንም እሰጣችኃለሁ፡፡” በሚል ይተረጉመዋል፡፡

    ኢየሱስ ለምንሰራው መልካም ስራ ልክ እንደ ቲፕ “ይኸውልህ ተጨማሪ ክፍያ” ወይም የድጋፍ እውቅና ለመስጠት “በፋብሪካ ውስጥ ለሠላሳ ዓመት ያገለገለ የሚል ፁሁፍ/ፖስተር/” አንዲለጠፍልህ አያደርግም፡፡

    ሁለተኛው ሽልማትን ኢየሱስ የገለፀበት አሁን በዚህ ምዕራፍ ኢየሱስ ለእራት በተጋበዘበት ጊዜ በተናገረው ንግግር ውስጥ የተጠቀሰው ነው፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ኢየሱስ ጥንድ የሆነው ቃል ማለትም አፖዲዶማይ የሚለውን ቃል ተጠቅሟል፡፡ “አፖ” ማለት በምትክ ሲሆን “ዲዶማይ” ማለት ደግሞ መስጠት ማለት ነው፡፡  ሁለቱ ቃላቶቹ ሲጣመሩ በምትክ መስጠት ማለት ነው፡፡ ወይም በቀላሉ መመለስ ማለት ነው፡፡

“የሚመልሱት ብድራት የላቸውምና ብፁዕ ትሆናለህ፤በፃድቃን ትንሳኤ ይመለስልሃል፡፡”

                                                      ሉቃስ 14፡14

    ይህ ቃል ኢየሱስ ወንበዴዎች አንድን ተጓዥ ደብድበውና ዘርፈው የጣሉትን ሰው ለመርዳት ወደ ኃላ ያላለውን የሳምራዊ ድንቅ ታሪክ ውስጥ ተጠቅሷል፡፡ ሳምራዊው ተጎጂውን በአቅራቢያ ለሚገኘው ጠባቂ ሲወስደው ለጠባቂው “በማግስቱም ሁለት ዲናር አውጥቶ ለባለቤቱ ሰጠና ጠብቀው ከዚህም በላይ የምትከስረውን ሁሉ እኔ ስመለስ እከፍልሀለሁ አለው፡፡” (ሉቃስ 10፡35)

    አፖዲዶማይ የሚለው ቃል በተለየ አኳሀን በዚህ ክፍል ውስጥ ተገልጿል፡፡ ኢየሱስ ዋጋህን/ደመወዝህን እጥፍ ድርብ አድርጎ ሲሰጥ በእርሱ ምትክ ሆነህ ለሰራው ስራ እንደሚሆን ይገልፃል፡፡ ሁልጊዜ ዋጋዬን በተናጥል በራሴ ማንነት ለሰራሁት ስራ ነው ብለህ ካሰብክ ኢየሱስ የተናገረውን ይህንን “… በስሜ ፅዋ ውሃ የሚያጠጣችሁን ሁሉ ዋጋው እንዳይጠፋበት እውነት እላችኃለሁ፡፡” (ማርቆስ 9፡41) ልናስታውስ ይገባናል፡፡

    ኢየሱስ የገባውን ድንቅ ቃል ኪዳን አስተውለህዋልን፤ ተማምነህበታልንስ? እያንዳንዱ ድርጊት በእግዚአብሔር ፊት ለሽልማት የምትተው ወይም የምትዘነጋ አይደለችም፡፡ አንድ ኩባያ ውሃ ሆነ በአንድ ምሽት ሌሊት የተፀለየው ፀሎት፡፡

የሕይወት ምስል

በቅርብ ሰሞን የአልጋ ቁራኛ የሆነችና በአድሜያዋም የገፋች ስሟ ቬራ የተባለች ቤት ሄድኩኝ፡፡ “ቀኑን ሙሉ አልጋ ላይ መሆኔ ቅስሜን ሰበረው ዶ/ር ዊልኪሰን” አለችኝ፡፡ “ለእግዚአብሔር ከመፀለይ የተለየ ነገር እዚህ ምንም አላደርግም፡፡” ብላ ሐሳቧን ገለጸችልኝ፡፡

    “ብዙ ጊዜ ትፀልያለሽ” ብዬ ጠየኳት፡፡

    ቬራ ምላሿን ከመስጠቷ በፊት ትንሽ አሰብ አደረገችና “የቀንኑ ግማሽና አልፎ አልፎም በምሽት ጭምር እፀልያለሁ” ብላ መለሰችልኝ፡፡

    “አንተ ግን ስትጸልይ፤ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤በስውር የሚያይህ አባትህ በግልጥ ይከፍልሀል፡፡” (ማቴዎስ 6፡6) ላይ የተመለከተውን ኢየሱስ የተናገረውን ቃል በመጥቀስ ቬራን አፅናናኋት፡፡

    ልከ እንደ ቬራ አንተም ሳትገነዘበው ዘላለማዊ አሴት ሊያስጨብጥ የሚችል ተግባር እያከናወንክ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ምን ዓይነት የሆነ የሕይወት ምስል እግዚአብሔር ይሽልማል ብለህ ታስባለህ?

    በየትኛውም የመጽሀፍ ቅዱስ ክፍል ኢየሱስ ሊያሸልሙ የሚችሉትን ተግባራት አንድ በአንድ እስከመጨረሻው ዘርዝሮ አላስቀመጠም፡፡ ይህ ሆኖ ሳለ ግን በአለም አጥናፍ ዙሪያ ባስተዋልኳቸው ማናቸውም ዓይነት ባሕል ውስጥ ጥሩ መስራት ምን ማለት እንደሆነ በደመ ነፍስ ጭምር ያውቁታል፡፡ የወይኑ ሚስጢር በተሰኘው መጽሃፌ ውስጥ እግዚአብሔር ሕይወታችን ፍሬያማ እንዲሆን የቱን ያክል እንደሚጥር ማብራሪያ ሰጥቼበታለሁ፡፡ ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ “ ብዙ ፍሬ ብታፈሩና ደቀ መዛሙርቴ ብትሆኑ በዚህ አባቴ ይከብራል፡፡” (ዮሐንስ 15፤8) ብሏቸዋል፡፡

    ኢየሱስ የሚፈልገው ሕይወት ምን እንደሚመስል ኢየሱስ ራሱ ካስተማራቸው ትምህርቶችና በተቀሩት የብሉይ ኪዳን የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ መገንዘብ እንችላለን፡፡ በተቻለ አቅም እግዚአብሔር የሚሸልመውን ሕይወት ምን መምሰል እንዳለበት ሊያግዝ የሚችሉትን ከእህት ቬራ አንስቶ የተወሰኑትን ለማየት እንሞክራለን፡፤

1.  እግዚአብሔርን በፆምና በፀሎት እርሱን ለማግኘት የምናደርገውን ጥረት ይሸልመዋል፣ (ማቴዎስ 6፡6፤ ዕብራዊያን 11፡6)

2.  እግዚአብሔር ለአለቃህ በፍፁም በመገዛት ለምታደርገው ታማኝነት ይሸልመሃል፡ (ማቴዎስ 24፡45-47፤ ኤፌሶን 6፤8፤ ቆላስያስ 3፡22-24)

3.  እግዚአብሔር እርሱን ለማገልገል ስትል ራስህን በመካድህ ይሸልመሃል፤ (ማቴዎስ 16፡ 24-27)

4.  በእርሱ ስም እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች ላደረከው አገልግሎት እግዚአብሔር ይሸልምሃል (ማርቆስ 9፡41)

5.  እግዚአብሔር ለእርሱ ስምና ክብር ስትል ስለደረሰብህ መከራ ይሸልመሃል (ሉቃስ 6፡22-23)

6.  እግዚአብሔር ለእርሱ ስትል ስለከፈልካቸው መስዕዋቶች ይሸልመሃል (ሉቃስ 6፤35) በትክክልም ኢየሱስ እርሱን ለመከተል በሚል መስዋዕት መክፈላችን መቶ እጥፍ እንደሚሸልመን ተናግሯል፡፡ (ማቴዎስ 19፤29)

7.  እግዚአብሔር መንግስቱ እንዲስፋፋ ጊዜህን፣ እውቀትህንና ክህሎትን እንዲሁም ሀብትህን ጥቅም ላይ እንዲውል በማድረግህ ይሸልመሃል (ማቴዎስ 6፡3-4፤ 1 ጢሞቲዎስ 6፡18-19)

    ከላይ የተዘረዘሩትን እግዚአብሔር የሚሸልማቸውን ተግባራትን በምትመለከትበት ጊዜ አንተ የትኛውን ቅድሚያ ሰጥተህ እያለህ ልታውቅ ትችላለህ፡፡ ወይም ይህንን ዝርዝሮች ስታይ የተስፋ ቢስ ስሜት ሊሰማህ ይችላል፡፡ ምክንያቱም እነዚህ ተግባራትን የሚያደርጉት ፍፁም ፃድቅ ተብሎ የሚወሰዱትን እንደ ቢል ግራሀም ወይም ማዘር ትሬዛ ካልሆንኩኝ ላደርግ አልችልም ትል ይሆናል፡፡

    እስቲ እኔው ላፅናናህ፡፡ ከዚህ በኃላ በምታነበው ፁሁፍ ውስጥ ሁሉም ሰው ምንም እንኳን የተለያየ አቅምና የተለያየ ሁኔታ ውስጥም ቢሆንም እግዚአብሔርን ለማስደሰት እድል እንዳለውና “መልካም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ፤ በጥቂቱ ታምነሀል፤በብዙ እሾምሃለሁ” (ማቴዎሰ 25:21) ለመባል እንደሚችል ትረዳለህ፡፡

የእግዚአብሔር ብጎ ስራ

እግዚአብሔር ለሁላችንም በእኩል ሁኔታ በማየት ሽልማት ሊሰጠን የሚችልበትን ሁኔታ በምንረዳበት ጊዜ የተለያየ ስሜት በውስጣችን ውስጥ ይፈጠራል፡፡ አንዳዶቹ ውስጣቸው ልዩ በሆነ ምስጋና ሊሞላ ይችላል፤ሌሎቹ ደግሞ ይህንን የመጨረሻውን ጊዜ ለማየት በጉጉት ላይ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቹም እንደነገሩኝ ለዚህ ጉዳይ ብዙም ግድ ላይላቸው ይችላል፡፡ እንዲዚህም ይላሉ “ እኔ ለሽልማት የምበቃ ሰው አይደለሁም!” ወይም “እኔ ከኢየሱስ ጋር ለዘላለም እንደምሆን ካረጋገጥኩኝ ሌላው ተጨማሪ ነገር ለምን ያስፈልገኛል” የሚሉም አሉ፡፡

    ለመጀመሪያ ጊዜ ከዚህ ርዕሰ ጉዳይ ጋር ራሴን ሳገናኝ ተመሳሳይ የሆነ ስሜት እንደተሰማኝ ስለማስታውስ በእንደነዚህ ዓይነት ስሜት ውስጥ ያሉትንም ሰዎች ሁኔታ እረዳለሁ፡፡ በእርግጥም እግዚአብሔር ባስቀመጠው እቅድ ውስጥ አልተስማማውም ነበር! ለዓመታት ያህል ለእግዚአብሔር ብዬ ብዙ ሥራዎችን ሳከናውን ቆይቻለሁ! ይሁን እንጂ የምሰራቸው እነዚያ መልካም ሥራዎች ሁሉ እኔ ለሽልማት ያበቁኛል በሚል ስሜት ሳከናውናቸው አልነበረም፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ነገር ብዬ የምወስደው ኢየሱስ ለእኔ ሲል ሞቶልኛል፡፡ እርሱን የቱንም ያህል ባገለግለውም ያደረኳቸው ተግባራት እንደ ኢምንት አድርጌ ነበር የምወስደው!

    ሁለት የወንጌል ክፍል ውስጥ የሚገኙት ጥቅሶች ያለኝን አመለካከት እንዲለወጡ አደረጋቸው፡-

·         በሉቃስ 17፡10 ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ፤ “እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁበትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ የማንጠቅም ባሪያዎች ነን፤ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል በሉ” አላቸው

    ይህ የመጽሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ከሁሉም በላይ የሚያስገነዝበው እግዚአብሔርን እንድናገለግለው የእኛ ሃላፊነት እንደሆነ ነው፡፡ ኢየሱስ እኔን ቢያመሰግነኝ እርሱ ባለፀጋ እና ቸር ስለሆነ ነው እንጂ እኔ ስለሚገባኝ ሆኖ አይደለም፡፡

·         በማቴዎስ 20፡1-6 ላይ ኢየሱስ የተለያዩ የጊዜ ርዝማኔ የሠሩ ሠራተኞች የተከፈላቸው ደመወዝ ግን አንድ ስለሆነበት ምሳሌ ነግሯቸዋል፡፡ ቀኑን ሙሉ ሲሰሩ የነበሩ ሠራተኞች ፍትሀዊነቱን አስመልክቶ ለመሬት ባለቤቱ ሲጠይቁ “… በገንዘቤ የወደድኩትን አደርግ ዘንድ መብት የለኝምን? ወይስ እኔ መልካም ስለ ሆንሁ ዓይነህ ምቀኛ ናትን?” ቁጥር 14-15

    ይህ የመፅሀፍ ቅዱስ ክፍል እግዚአብሔር እስከሚፈልገው መጠን ድረስ ቸር መሆን እንደሚችል ያስታውሰኛል፡፡ ስለ እርሱ ጥሩነት የምከራከርበት ነጥብ ባነሳ ከመጀመሪያውም አንስቶ በእኔ ውስጥ የሚፈለገውን ጥሩነት በልቤ ውስጥ ባለመኖሩ ነው፡፡

    አንድ ቀን ብዙዎቻችን የምናውቀውን ጥቅስ ተመልክቼ ሳጠናው በዚህ ጉዳይ ላይ ያለኝ አመለካከት እንዲቀየር ልዩ መሠረት ጥሎልኛል፡፡

ሸላሚውን አግኝ

ስለ እምነት አባቶች አስመልክቶ የዕብራዊያን መልዕክት ሰፋ ባለ መልኩ በእምነታቸው እግዚአብሔር የተደሰተባቸውን ሠዎች በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ “ ያለ እምነት እግዚአብሔርን ማስደስት አይቻልም” ይልና ፀሀፊው “ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና” ይላል፡፡ (ዕብ 11፡6)

    ሸላሚ የሚለውን ቃል በ"ግሪክ ምን እንደሚል ስትመለከተው በጣም ትደነቃለህ፡፡ በዚህ ክፍል ውስጥ ሸላሚ የሚለው ቃል “ሚስቶስ” ወይም “አፖዲዶማይ” የሚለውን ቃል ሳይሆን ሁለቱንም ቃላትን በአንድነት የያዘ ነው፡፡ በእርግጥ ከዕብራቢያን 11፡6 በስተቀር በሌሎች የመፅሃፍ ቅዱስ ስለዋጋ ሰለሚሰጠው የተገለፀበት ክፍል የለም፡፡ በዚህ ጥቅስ አግዚአብሔርን ዋጋን የሚመልስ ሸላሚ አድርጎ ገልፆታል፡፡

    እግዚአብሔር ቸር የሆነ ባህሪያ ያለው በመሆኑ ይህንኑ ባህሪውን የሚገልጽ ሽልማትም ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ከመቆጠብ ይልቅ ለመሸለም ያለው እቅድ እርሱ ድንቅ የሆነ ፀጋ ያለው እንደሆነ የሚያመላክት ነው፡፡

    ከዚህ ውጪ ስለ እርሱ ባህሪይ ልንገልፅ የምንችልበት ሁኔታ የለም፡፡ እግዚአብሔርን ለማስደሰት የምትፈልግ ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ እርሱ አምላክ እንሆነ ልታምን ይገባል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በሌላ ነገርም ልታምን ይገባል፡፡ እርሱም እግዚአብሔር “የሚሸልም አምላክ” እንደሆነ ነው፡፡

    በአሁን ጊዜ ወደ ሽልማት እንድንደርስ የሚያደርገን እምነት ነው፡፡ በሚቀጥለው ምዕራፍ ግን ኢየሱስ ፊት ለፊት ሆኖ ያለንን እምነት የሚያሳይበትን የወደፊት ሁኔታ እንመለከታል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


4

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">የዚያች ቀን</b>

ሰዎች ሁሉ አብን እንደሚያከብሩት ወልድን ያከብሩት ዘንድ

ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ

አይፈርድም፡፡

 ኢየሱስ ፣ በዮሐንስ 5፡22-23

ኩር ብለህ ወደ ቴሌቪዥን እየተመለከትክ በኦሎምፒክ ውድድር አሸናፊ የሆኑ ሰዎች ሜዳሊያ ሲሸለሙ ስሜቱህ ተነክቶ እንባህ በጉንጭህ ፈሶ ያውቃል? እኔ ግን አጋጥሞኛል፡፡ በትዕይንቱ የሰውን ልብ ልዩ ስሜት እንዲሰማው የሚያደርግ ነገር አለ፡፡

    አንተ የምታደንቀው አትሌት የመሸለሚያውን ጠረጴዛ ላይ ሲወጣ፣ ብሔራዊ መዝሙሩ እስታዲየሙን በሞሉት ሰዎች ፊት ሲደመጥ እንዲሁም የሀገሩ ባንዲራ ሲውለበለብ ልዩ ስሜት ያመጣል፡፡ ላቡን አንጠብጥቦ ለሠራበት ሥራ ዋጋውን ሲቀበል ላቅ ያለ ስሜት እንዲጎናፀፍ ያደርገዋል፡፡ ሩጫውን ጨርሷል፡፡ ደግሞም አሸናፊም ሆኗል፡፡

    አሸናፊም ስለሆነ ሺዎች እያጨበጨበለት ሽልማቱን የሚሸልመወ የክብር እንግዳው ሜዳሊያውን በአሸናፊው አንገት ውስጥ ያጠልቃል፡፡

    አንድ ቀን እኔ እና አንተ ለዘላለም ሽልማታችንን የምንቀበልበት ጊዜ ይመጣል፡፡ በሰማይ ያሉ ታዳሚያን ምስጋናቸውንና ደስታቸውን የሚገልፁበት ጊዜ ይመጣል፡፡ ከተለያዩ ሀገራትና ከትውልድ እስከ ትውልድ ያሉ ምስክሮች አንተ ሽልማትህን ለመውሰድ ባለህበት ጊዜ በልዩ ጉጉት  እየተመለከቱ ይጠብቁታል፡፡ መልእክትም ቢሆኑ…

    ለዚህም ምክንያቱ የእምነት ሩጫችን ስለተገባደደ ነው፡፡ ሽልማታችንን በመሸለሚያ ጠረጴዛ ላይ ወጥተን ሽልማታችንን የምንቀበልበት ጊዜ በመምጣቱ የተነሳ፡፡

    በዚያን ቀን የሚዳኘንና ሽልማቱን የሚሰጣን ማን ይሆናል ብለህ ታስባለህ? ትከክለኛ ሸላሚ ሊሆን የሚገባው ከሠማያዊ ምልከታ አንፃር ፍትሃዊነትን በውል የሚረዳና በምድራዊ ኑሮ የሚስተዋለው መከራ ጭንቅ በእርግጥ ሊረዳ የሚችል ሰው መሆን አለበት፡፡

    ይህን ሊረዳ የሚችለው ብቸኛው ደግሞ ኢየሱስ ነው፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ እንደሚነግረን “ከሐጢያት በቀር በነገር ሁሉ እንደ እኛ የተፈተነ ነው እንጂ፤ በድካማችን ሊራራልን የማይችል ሊቀ ካህናት የለንም፡፡” ይላል (ዕብራዊያን 4፡15) በእርግጥም ኢየሱስ የእኛ ዳኛ እንደሆነ መፅሃፍ


ቅዱስ ይገልጥልናል፡፡ ኢየሱስ ራሱ ለደቀ መዛሙርቱ የመፍረድ እና የዳኝነት ሥልጣን ከአባቱ ከእግዚአብሔር እንደተሰጠው እንደነገራቸው መፅሃፍ ቅዱስ ሲገልፅ፡-

     “ፍርድን ሁሉ ለወልድ ሰጠው እንጂ አብ በአንድ ሰው ስንኳ አይፈርድም፡፡” ዮሐንስ 5፡22

    ጳውሎስ ወደፊት የሚገጥመውን ሽልማት እያሰበ እንደዚህ ብሎ ተናገረ፡- “ወደ ፊት የፅድቅ አክሊል ተዘጋጅቶልኛል፤ ይህንም ፃድቅ ፈራጅ የሆነው ጌታ ያን ቀን ለእኔ ያስረክባል፤ደግሞም መገለጡን ለሚወዱት ሁሉ እንጂ ለእኔ ብቻ አይደለም፡፡” (2 ጢሞቲዎስ 4፡8)

    አዳኝህን ፊት ለፊት ለማየት ትናፍቃለህን? ይህ ከሆነ የዚህ ምዕራፍ ክፍል ለአንተ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ወደፊት ይከሰታሉ በሚል ከተዘረዘሩት ክስተቶች ውስጥ ቁጥር 5 ላይ የተመለከተውን ማለትም መካስ የሚለውን እንመለከታለን፡፡

    በምድር ላይ በነበርክበት ጊዜ ለሠራሃቸው ሥራዎች ኢየሱስ ዋጋህ ሊከፍልህ አንተ በእርሱ በፊት ስትሆን ምን ሊሆን እንደሚችል በመጀመሪያ ደረጃ እንመለከታለን፡፡ ሁሉም ሰው ያደረጋቸውን ተግባራት ይናገራል፤ ለሠራቸውን ሥራዎችም ዋጋውን ከእግዚአብሔር እንደሚቀበሉ ልብ ልትል ይገባል፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ ለአብያተ ክርስቲያነት መልዕክቱን ሲፅፍ ሁላችንም በኢየሱስ ወንበር ፊት እንደምንቆም ገልፆላቸዋል፡፡

    ከዚህ በኃላ በሚኖረን ጥቂት ደቂቃ ምንባብ ውስጥ በዚያ የፍርድ ወንበር ጊዜ ኢየሱስ ለእርሱ የሰራነውን እንዴት እንደሚገመግም አስመልክቶ ለሚነሳ ጥያቄ መልስ የምንመልስበት ይሆናል፡፡ ምን እንደምናጣ እና ምን እንደምናገኝ? እናም ለዚያም እንዴት ምላሻችንን እንሰጣለን?

    እንደ ሐዋሪያው ጳውሎስ በዚያ የፍርድ ቀን ስለሚከሰተው ነገር በዝርዝር የዘረዘረው የለም፤ ምናልባትም ሐዋሪያው በግሪክ ባለችው የቆሮንጦስ ከተማ በዚህ ጉዳይ ላይ በዝርዝር መመልከቱ ጠቃሚ እንደሆነ ተገንዝቦት ሊሆን ይችላል፡፡

ጳውሎስ ስለ መጨረሻው ፍርድ ቀን የሰጠው ሃሳብ

ሐዋሪያው ጳውሎስ በቆሮንጦስ ከተማ ለበርካታ ወራት በችግር ውስጥ ሆኖ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ወንጌልን ያሰራጭ ነበር፡፡ የአርሱ ጠላት የሆኑ ሰዎች ወደ ፍርድ ወንበር ወስደውት “ይህ ሕግን ተቃውሞ እግዚአብሔርን ያመልኩት ዘንድ ሰዎችን ያባብላል” በማለት ከሰሱት፡፡ (ሐዋሪያት 18፡13)

    ሊቃውንት በቆሮንጦስ ከተማ ውስጥ በእምነበረድ የተሰራ አሁንም በፍርስራሽ ውስጥ የሚታይ ከፍ ያለ መቀመጫ የግዛቱ አስተዳዳሪ ክርክሮችን የሚያደምጡበት ቦታ እንደሆነ ይስማማሉ፡፡ የመቀመጫው ሥፍራ በግሪክ ቃል “ቤማ” የሚባል ሲሆን ትርጓሜውም የፍርድ መቀመጫ ወንበር ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይ ይህ ቃል በአትሌቲክ ውድድር ጊዜ ሀላፊዎች የሚቀመጡበት ወንበርም ለጥቀስ ይውላል፡፡ “ቤማ” የሚለው ቃል ሥልጣን፣ ፍትህና ሽልማትን የሚወክል ነው፡፡ (ዮሐንስ 19፡13፤ ሐዋሪያ ሥራ 25፡10-12)

    የጳውሎስ ክርክር በሚሰማበት ጊዜ ጠላቶቹ እንዲቀጣ በሚሞግቱበት ጊዜ ክርክሩን ሲሰማ የነበረው ጋሊዮ የሚባለው አስተዳዳሪ ነበር፡፡ ጳውሎስ ለተከሰሰበት ክስ የሚከላከልበት ጊዜ ሲደርስ ጋሊዮ የክስ መሰማቱ ሂደት እንዲቋረጥ አደረገ፡፡ ከመከላከሉ በፊት ሊያስቀጣ የሚችል ወንጀል እንዳልፈፀመ ከወዲሁ ተገንዝቦ ነበርና፡፡ አሁን ጳውሎስ በነፃ ሊለቀቅ ይችላል፡፡

    ጳውሎስ ካሳለፋቸው አስቸጋሪ ጊዜያት አንፃር በቆሮንጦስ ከተማ የነበረው የፍርድ ሂደት ለእርሱ ቀላል ሊሆን የሚችል ነው፡፡

    ወይስ በተለየ ሁኔታ ሊታይ የሚችል ነው?

    ከሦስት ዓመታት በኃላ ሐዋሪያው ጳውሎስ መልሶ ለቆሮንጦስ ሰዎች መልዕክት ፅፎላቸዋል፡፡ በመልዕክቱ ውስጥም ስለ ሌላ ቤማ ማለትም ስለ ሰማያዊ የፍርድ ወንበር፡፡ እያንዳንዱ አማኝ በፍርድ ወንበር ፊት አንድ ቀን እንደሚቆሙ፤ ጊዜም እንደተቀጠራላቸው ይነግራቸዋል፡፡ በመልዕክቱ እንዲህ ስል ይገልፅላቸዋል፡-

      መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፤ እያንዳንዱ በሥጋው የተሰራውን

     በብድራት ይቀበል  ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ

     ይገባናልና፡፡

                              2ቆሮንጦስ 5፡10

 

    ጳውሎስ በፃፈበት መልዕክት ውስጥ ሁለት መሠረታዊ ሐረጋትን እንመልከት፡ “እያንዳንዱ …በብድራት ይቀበል ዘንድ” የሚለው በግልፅ ሊቀበል ስላለው ሽልማት ወይም ዋጋ ነው፡፡ እንደገናም “… በስጋው የተሰራውን” ሲል ደግሞ ሽልማቱ በምድር ላይ በነበርንበት ጊዜ ባከናወነው ላይ ብቻ እንደሚገደብ ነው፡፡ እንደምትገነዘበው ሽልማቱ ተግባራዊ የሚሆነው ከሞትን በኃላ በሰማይ ነው፡፡

    በቆሮንጦስ ከተማ ጳውሎስ ያጋጠመው የፍርድ ወንበር የቆሮንጦስ ቤተ ክርስቲያን እንድታስተውልና እንድታስታውስ የሚፈልገውን ሃሳብ እንዲያጣ ያነሳሳዋል፤ ይህም የፍርድ ወንበር እንደሚኖር፣ እያንዳንዳችንም በፍርድ ወንበር ፊት እንደምንዳኝ፣ ዳኛ ደግሞ የሚሆነው ራሱ ኢየሱስ እንደሚሆን ነው፡፡

የፍርድ ወንበር ምንነት የሚታወቅበት ሌላው አጋጣሚ

ከሁለት ዓመት በኃላ ጳውሎስ በሮም ላሉት ክርስቲያኖች የማጽናኛ መልዕክትን በሚፅፍበት ጊዜ በግሪክኛ ቃል ቤማ ስለሚለው ጉዳይ ዳግመኛ አንስቶላቸዋል፡-

        ሁላችን በክርስቶስ ፍርድ ወንበር ፊት እንቆማለንና፡፡…እንግዲያስ

        እያንዳንዳችን ስለ ራሳችን ለእግዘአብሔር መልስ እንሰጣለን፡፡ ሮሜ 14፡ 10፣12

 

    ጳውሎስ “ስለ ራሳችን …መልስ እንሰጣለን” ሲል ምን ማለቱ ነው፡፡ በ 1 ቆሮንጦስ 3 ላይ ስለ ፍርድ ከተገለፀው በተለየ ሁኔታ ስለ ፍርድ ያለን አመለካከት የተለየ ተጨማሪ ሀሳብ እንድናገኝ ያስችለናል፡፡ በዚህ ምዕራፍ ውስጥ ስለ ፍርድ ሂደት ያለውን ሃሳብ ሲያስቀመጥ እንደመሸለሚያ መድረክ ሳይሆን ስራችን በእሳት እንደሚፈተን ሕንፃ አድርጎ ነው ያቀረበው፡፡

          ማንም ግን በዚህ መሰረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም

          በእንጨትም በሳርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ የእያንዳንዱ ስራ ይገለጣል፡፡

          በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፤ የእያንዳንዱም ስራ እንዴት መሆኑን

          እሳቱ ይፈትነዋል፡፡ 

                                                ከቁጥር 12-13

    ከላይ ከተመለከተው ጥቅስ  በፊት ጳውሎስ “መሠረት” ብሎ የጠቀሰው ኢየሱስን ነው፡፡ ይህንን ከአሁን ከተመለከተው ጥቅስ ጋር ስናገናኘው የፍርድ ወንበር ዋና አላማ የሰውን ሥራ ለመግለጥ ነው፡፡ “ይገለጣል”፣ “ያሳያል” እና “ይፈትነዋል” የሚሉትን ቃላትን ልብ ልትላቸው ይገባል፡፡ ሠዎች ስለሚሰሩት ስራ መልስ የሚሰጡበት እና የሰራናቸውን ስራዎች ግልጥ የሚሆንበት ጊዜ ጳውሎስ ኢየሱስ እንደገለፀው “ያ ቀን” ተብሎ የሚጠቀሰው ነው፡፡

    ሁለተኛው በፍርድ ወንበር የምንሆንብት ምክንያት ሥራችን ለመፈተን ነው፡፡

   በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፤ የእያንዳንዱም ስራ እንዴት መሆኑን እሳቱ     

      ይፈትነዋል፡፡ ማንም በእርሱ ላይ ያነፀው ሥራ ቢፀናለት ደመወዙን ይቀበላል፡፡ የማንም   

   ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፤እርሱ ራሱ ግን ይድናል፤ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል

                                               ቁጥር 13-15

 

    አሁን ስራ እንዳልተፈተነ ልብ ልትል ይገባል፡፡ እምነትህ አልተፈተነም፡፡ የዘለለም መኖሪያ የት እንደሆነ አልታወቀም፡፡

    ይህ ከሆነ ዘንድ በፍርድ ወንበር ቀን የሚፈተነው ነገር ምንድን ነው? ሥራህ፡፡ በሕይወትህ የሠራሃቸው ስራዎች ልክ ወርቅ፣ ብር እና ውደ ድንጋዮች በእሳት ውስጥ እንደሚያልፉት ይቆያል፡፡ አሊያም በምድር ላይ በምትኖርበት ጊዜ የቱም ያሀል አስደሳች፣ ትርጉም ያለው ሥራዎችን አከናውኛለው ብትልም ገለባ እንደሚቃጠል ሁሉ የሠራሃቸው ሥራዎች ምንም ዓይነት ቅሪት ሳይኖረው ሊቃጠል የሚችል ነው፡፡

    በመጨረሻው የፍርድ ወንበር ጊዜ የምንሰራው ሥራ እንዴት ግልጥ ሆኖ “እንደሚታይና እንደሚፈተን” በይበልጥ ለመረዳት እንዲቻል ሁለቱ የኢየሱስ ተከታዮች በፍርድ ወንበር ጊዜ ሊሆን የሚችለው ሁኔታ እንመልከት፡፡ አንደኛው የቤተ ክርስቲያ ታላቅ መሪ ነው፡፡ ሁለተኛው ደግሞ በበረንዳ የሚኖር ነው፡፡ በመጀመሪያ ታላቁ መሪ ቀጥሎም በበረንዳ ያለው ሰው በፍርድ ወንበር ስር ቀረቡ፡፡ እያንዳንዱ በሕይወት ዘመናቸው የሰሯቸው ሥራዎች በግልፅ ፊት ለፊታቸው ታየ፡፡ የተሰማቸው ሥራቸው በእሳት እንዲፈተን ተደረገ፡፡

    ከእነዚህ ሁለቱ የትኛው ወደ ዘላለም ሕይወት ከፍ ያለ ሽልማት በማግኘት ይገባል?

    መልሱ የሠሩት ሥራዎች በፍርድ ጊዜ ስራዎቻቸውን በእሳት ካልተፈተነ የትኛው የተሻለ ሽልማት እንዳገኘ አይታወቅም የሚል ነው፡፡ በእሳቱ አስኪፈተን ድረስ የየትኛው ስራ ለሽልማት ብቁ እንደሆነ የሚያውቀው እግዚአብሔር ብቻ ነው፡፡ ለዚህም ነው ጳውሎስ “ስለዚህ በጨለማ የተሰወረውን ደግሞ ወደ ብርሃን የሚያወጣ የልብንም ምክር የሚገልጥ ጌታ እስኪመጣ ድረስ ጊዜው ሳይደርስ አንዳች አትፍረዱ፤በዚያን ጊዜም ለእያንዳንዱ ምስጋው ከእግዚአብሔር ዘንድ ይሆናል፡፡” (1 ቆሮንጦስ 4፡5) በማለት ክርስቲያኖች ለመፍረድ መቾኮል እንደሌለባቸው ያስገነዝባል፡፡

    ሰው የሠራቸው ስራዎች በእሳት ሲፈተን ብቻ ለዘላለም ሕይወቱ የሚያበቃውን ሽልማት እንዳከማቸ ሊታወቅ የሚቻለው፡፡ እሳቱ እውነተኛ የሆነው ነገር እንዲገለጥ ያደርገዋል፡፡ የተከማቸውን ስራ በእሳቱ ሲፈተን ስንመለከት ለሽልማት ብቁ የሆነውንና ያልሆነውን ከመለየት አንፃር ኢየሱስ በሚፈርደው ፍርድ እኛም ሙሉ በሙሉ እንድንስማማ መንገድ ይከፍትልናል፡፡

    በባለፈው ምዕራፍ እግዚአብሔር የሚወደው ሕይወት ምን ሊመስል እንደሚችል ሥዕሉን ለማስቀመጥ ሞክረን ነበር፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ እንደገለፀው ትክክለኛ ባሀሪ የሚገኘው ከልብ ነው፡፡ (ሉቃስ 6፡43-45)

    ከኢየሱስ ትምህርት የተገኘውን ሦስቱ መለኪያዎችን እንደ ዋና መመዘኛ መስፈርት አድርጎ በመውሰድ ለእግዚአብሔር የሰራሃቸው ሥራዎች ቋሚዎች አንደሆኑ እና እንዳልሆኑ የሚያስችሉህን ሁኔታዎች ሰፋ ባለ ሁኔታ እስቲ እንያቸው፡-

1.  የግንኙነት መስፈርት፡- ከኢየሱስ ጋር ካለህ ግንኙነት ውጪ የምታከናውናቸው ሥራዎች እግዚአብሔር ለሚሸልመው ሕይወት አላስፈላጊ ሆኖ እንድትቆጥር ያስችልህ ይሆናል፡፡ ይህን እንጂ በተቃራኒው ትክክለኛ እውነታው ነው፡፡ ኢየሱስ ከእርሱ ጋር ጥብቅ ግንኙነት ከሌለንና እርሱ ያዘዘንን ነገር መፈፀም ካልቻለን በቀር ፍሬ ልናፈራ እንደማንችል “”ያለ እኔ ምንም ልታደርጉ” አትችሉም በማለት እንተናገረው ነው፡፡ (ዮሐንስ 15፡5)

    በራዕይ መጽሃፍ ላይ ኢየሱስ ለኢፌሶን ቤተ ከርስቲያን በላከው መልዕክት ለሠራቻቸው መልካም ስራዎቿ አመስግኗት ለእርሱ ብላ ግን ፍቅሯን ባለመጠበቋ እንደኮነናት እናያለን፡፡ ኢየሱስ ሲናገር “ስራህንና ድካምህን ትዕግስትህንም አውቃለሁ፤ … ዳሩ ግን የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤የቀደመውን ፍቅርህን ትተሃልና፡፡ (ራዕይ 2፡2፣4)

2.  የውስጥ ሃሳብ መስፈርት፡-  ኢየሱስ “ለሰዎች ትታዩ ዘንድ ምፅዋታችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ ያለዚያ በሰማያት ባለው አባታችሁ ዘንድ ዋጋ የላችሁም፡፡” አለ፡፡  የውስጥ ተነሳሽነት በምን ዓይነት መንፈስ ሊቀረፅ ይገባዋል? እግዚአብሔርን ለማገልገልና ለእርሱ ክብር እንዲሆን፡፡ ትናንሽ ተግባራት የምንላቸው እንደ መብላትና መጠጣት እንኳን ለእግዚአብሔር ክብር ሊሆኑ ይገባል፡፡ (1 ቆሮንጦስ 10፡31) በተቃራኒው ትልቅ ስፍራ ሰጥተነው ለምናከናውነው “ሃይማኖታዊ” ተግባር ለራሳችን ክብር እና ዝና ማግኛ ከሆነ ርባና ቢስ ነው፡፡

3.  የፍቅር መሰፈርት፡- ትክክለኛ ፍቅር የወዳጁን መልካም ሁኔታ ይበልጥ እንዲሻሻል ልዩ ትኩረት ይሰጣል፡፡ ኢየሱስ ሲናገር “ነገር ግን ጠላቶቻችሁን ወደዱ፤መልካም አድርጉ፤ምንም ተስፋ ሳታደርጉ አበድሩ፤ዋጋችሁም ታላቅ ይሆናል፤የልዑልም ልጆች ትባላላችሁ፤እርሱ ለማያመሰግኑ  ለክፉዎች ቸር ነውና” አለ፡፡ ጳውሎስ ስለ ፍቅር በፃፈው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ውስጥ ያለ ፍቅር የምናደርገው መልካም ስራ ለባለቤቱ እንደማይጠቀመው ሲናገር፡-“ድሆችንም ልመግብ ያለኝን ሁሉ ባካፍል፤ሥጋዬን ለእሳት መቃጠል አሳልፌ ብሰጥ ፍቅር ግነ ከሌለኝ ምንም አይጠቅመኝም፡፡” አለ፡፡ (1 ቆሮንጦስ 13፡3)

    በፍርድ ወንበር ጊዜ እያንዳንዱ ለእግዚአብሔር የሰራናቸው ሥራዎች እንደሚዳኝ ልብ ልንል እንደሚገባ ተረድተን ነገር ግን ባልሰማነው ጉዳይ የሠራናው ስራ ውድቅ ቢሆን ራሳችንን ለስጋት አሳልፈን ልንሰጥ አይገባንም፡፡ ኢየሱስ በቃሉ ላይ የተመለከተውን ነገር ሳናውቅ ቀርተን በቃሉ መመዘኛ መስፈርት አንፃር እንድናሟላ አንደረግም፡፡ (2 ጴጥሮስ 1፡2-4)

    ጳውሎስ “ይጎዳበታል” ሲል ምን ማለቱ ነው?

“በሰማይ እንዴት ሊጎዳ ይችልብኛል?”

በእሳት መፈተንን አስመልክቶ በ 1ቆሮንጦስ 3 ላይ የተመለከተው የሚዘጋው ለየት ባለ አገላለፅ ነው የሚዘጋው፡፡ እንዲህ ሲል፡-“የማንም ስራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፤ እርሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል፡፡” ይላል፡፡ (ቁጥር 15)

    ይህኛው የመጽሃፍ ቅዱስ ክፍል ማለትም በመጨረሻው የፍርድ ወንበር በምንሆንበት ጊዜ የሰራነው ስራ ሊጎዳብን እንደሚችል ነው፡፡

    ምን ዓይነት የሚገርም አስተሳሰብ! አንድ ሰው የዘላለም ሕይወት እንደሚያገኝ አውቆ ነገር ግን በምድር ላይ በሚኖርበት ጊዜ የሰራቸው ሥራዎች ግን ጥቂት እንደሚሆኑበት?

    አዎ፡፡ በዚህ ጥቅስ ላይ እንደሚነበበው ይህ በትክክል ሊሆን እንደሚችል ነው፡፡

    በምድር ላይ መሰራት ያለበትን ስራ ልትሰራ ትችል ይሆናል ነገር ግን ሥራህ ለሽልማት የማያበቃ ሆኖ ሊገኝ ይችላል፡፡ ሐዋሪያው ዮሐንስ “ሙሉ ደመወዝን እንድትቀበሉ እንጂ የሠራችሁትን እንዳታጠፉ ለራሳችሁ ተጠንቀቁ” በማለት የገለፀው የሚያስደንቅ አይደለም፡፤ (2 ዮሐንስ 1፡8)

    እርሱ በድጋሚ “አሁንም ልጆቼ ሆይ በሚገለጥበት ጊዜ እምነት እንዲሆንልን በመምጣቱም በእርሱ ፊት እንዳናፍር በእርሱ ኑሩ፡፡” በማለት የገለፀበት ያለ ምክንያት አይደለም፡፡ (ዮሐንስ 2፡28)

    አሁንም ቢሆን የመጨረሻው የፍርድ ወንበር ዓላማ የሠራነው ሥራ እንዲጎዳብን አይደለም፤ እንድናገኝ፡፡ ምንም እንኳን ልንሰራው የሚገባውን ባለማድረጋችን በዘላለም ሕይወት ጊዜ ልናገኝ የምንችለውን ሽልማት የምናጣ ቢሆንም የምንፀፀትበትና የምናፍርበት ጉዳይ ግን አይኖርም፡፡ በዚህ ጉዳይ ግን እንዴት እርግጠኛ ልሆን እችላለሁ? ምክንያቱም መፅሃፍ ቅዱስ “እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፤” በማለት ቃል ስለሚገባልን ነው፡፤ (ራዕይ 21፡4)

    የሚያስገርመው እውነት ግን ኢየሱስ አንተን ከመውደዱ የተነሳ ደሙን አፍስሶ ሕይወትህን ከመዋጀት ወይም አሁን በምታነብበት ጊዜ ከሚኖረው ፍቅር በፍርድ ወንበር ፊት በምትቀርብበት ጊዜ የሚያንስም አሊያም የሚበልጥም አይደለም፡፡

    ወዳጄ በፍርድ ወንበር ጊዜ በዚህ ረገድ ያለንን ተስፋ በመረዳት ከማዘን ይልቅ ከሙሉ ልብ የመነጨ ደስታ በዚያች ቀን ከእኔ ጋር ተጋራ፡፡ በምድር የምናገኘው ሽልማት ኢየሱስ የሰራናቸውን ስራ አይቶ እኛን ሊያበረታን የሚፈልገውን ሽልማት በአዳኛችን ፊት ሆነን ከምናገኛው ያልደበዘዘ ደስታ ጋር በፍፁም ሊወዳደር የሚችል አይደለም፡፡

ሽልማቱን ለመጠበቅ

      

ኢየሱስ ለሕይወታችን ሽልማት በሚሰጥበት ጊዜ፣በመጨረሻ እግዚአብሔር ሙሉ በሙሉ ለእኛ፣ በእኛና በእኛው ውስጥ ሆኖ የሰራውን ስናይና ስንገነዘብ፤ ያለ እርሱ እርዳታ አንድ እንኳ የሚያስመሰግን ሥራ ለመስራት እንደማንችል በተገቢው ሁኔታ በተረዳን ጊዜ የእኛ ሁለንተናዊ ምላሽ የሚሆነው እርሱን ለማመስገንና ለማከብር መጮህ ብቻ ነው፡፡

    በዚያን ጊዜ ከልዩ ደስታና ምስጋና የመነጨ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እግር ስር ወድቀን እንድናመሰግናው ከወውደዳችንም አልፎ የሰጠንን ሁሉ መልስን ለመስጠት እንፈልጋለን፡፡

    ኢየሱስ እነዚህን ሁሉ እንድንጠብቀው ይፈልጋል፡፡

    በሚቀጥለው ምዕራፍ በምንመለከትበት ጊዜ የእርሱ እቅድ አንተ እንድትደሰትና በምታገኘው ሽልማት ዘላለም እንድትኖር እንደሆነ ትረዳዋለህ፡፡ ያለንን አክሊል በኢየሱስ ፊት እንጥለዋለን የሚለው አመለካከት ሊመጣ የቻለው በራዕይ 4፡10-11 ላይ የተመከተውን የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ በተገቢው ሁኔታ አውዱን ባለመቀመጡ የተነሳ ነው፡፡ በዚህ የመፅሃፍ ቅዱስ ጥቅስ ውስጥ የተወሰኑ ሽማግሌዎች ያላቸውን አክሊል በኢየሱስ ዙፋን ስር እንደሚያደርጉት እናነባለን፡፡ በዚህ አውድ ውስጥ የተጠቀሱት ሽማግሌዎች ግን ሁሉን አማኞችን የሚወክሉ አይደሉም፡፡ በዚህ ጥቅስ ውስጥ አውዱን በምንመለከትበት ጊዜ እነዚህ ሽማግሌዎች አከሊላቸውን በመጣል የሚያመልኩበት የአምልኮ ስርዓት ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚያመልኩበት ተግባር እንደሆነ መረዳት ያስፈልገናል፡፡

    የእርሱን አስደናቂ ሃይል ስትመለከት ልክ እንደነዚህ ሽማግሌዎች ያለህን አክሊል በዙፋኑ አግር ስር በመጣል ልታመልከው ትወዳለህን? በእርግጥም መረዳትህ በዚህ የአምልኮ ስርዓት ውስጥ እንድትገባ ያደርግሃል፡፡

    ኢየሱስ የሚሰጠው ሽልማት ለአንድ ጊዜ የሚበቃ ሳይሆን ከዘላለም እስከ ዘላለም የሚሆን ነው፤ በጥቂት የምድር ቆይታህ ለምታከናውናት ተግባር ለአንተ ያለውን ያልተገደበ ፍቅር የሚገልፅበት መንገድ ነው፡፡ አንደኛው ልዩ እና ዘላለማዊ ሽልማት ተደርጎ የተጠቀሰው በዳንኤል 12፡3 ላይ ሲሆን ጥቅሱም “ጥበበኞቹም እንደ ሰማይ ፀዳል፤ብዙ ሰዎችንም ወደ ፅድቅ የሚመልሱ እንደ ክዋክብት ለዘላለም ይደምቃሉ፡፡” ይላል፡፡

    እናም የአንተ ሽልማት ለዘላለም ከአንተ ጋር አብሮ የሚዘልቅ ነው፡፡

    በሰማይ የሚገጥምህ ሽልማት ልክ እንደዚህ ልዩ ዓይነት መሆኑን ስትረዳ ከዚህ ውጪ ሌላ ሽልማት ለማግኘት የምትጓጓ ከመሆኑም በላይ በዚህም ሁልጊዜ የምትደነቅ ትሆናለሀ! በሚቀጥሉት ሁለት ምዕራፎች ኢየሱስ ከተናገረው ቃል በመነሳት እዚህ ላይ ሆነህ የምትከናውናቸው ተግባራት በሰማይ ለሚጠብቅህ ሽልማት ወሳኝ እንደሆነ አሳይሃለሁ፡፡

    እናም በሰማይ ሆነህ ለመሰራት የምትፈልገው ከሁሉም በላይ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡


5

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">የሕይወትህ ጥያቄ</b>

“በእናንተስ እንዲህ አይደለም፤ነገር ግን ማንም ከእናንተ ታላቅ ሊሆን የሚወድ የእናንተ አገልጋይ ይሁን፤ ከእናንተም ማንም ፊተኛ ሊሆን የሚወድ የሁሉ ባሪያ ይሁን፡፡”

ኢየሱስ፣ በማርቆስ 10፡43-45

ሰማይ ስተደርስ የአንተ ትልቁ መሻትህ በሰማይ ምን እንዲሆን ነው? በዚህ ረገድ ፍንጭ እንዳገኝ ሰማንያ ሺ ሰዎችን ለማግኘት ግድ ሆኖብኝ ነበር፡፡ በዴትሮይት ኬቨርነስ ሲልቨርዶም እስታዲዮም ውስጥ ከነበሩት አቅምን ሊፈጥሩ ከሚችሉተ የክርስቲያን ስብስብ ውስጥ አኔ አንዱ ነበርኩኝ፡፡ ተናጋሪው ከጨረሰ በኃላ የአምልኮ በድኖች “ቅዱሰ ቅዱስ ቅዱስ” የሚለውን ዝማሬ ለመምራት ወደ መድረኩ ወጡ፡፡

    ዝማሬው እየቀጠለ ባለበት ሂደት ውስጥ ዝማሬው ጉልበት እያገኘ በመምጣቱ ፀጥታው እየጠፋ መጣ፡፡ ዝማሬው ካለቀ በኃላ እንደገና የድምፃችን መጠን ጨምረን ዝማሬውን መዘመር ቀጠልን፡፡ በመጨረሻ ከእግር ኳስ መጫወቻው አንስቶ በሁሉም የእስታዲየሙ ቦታዎች ሁሉ በአምልኮ ዝማሬ ተሞላ፡፡

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ! ሃያልና ታላቅ አምላክ እግዚአብሔር!

በጠዋት በማለዳ ዝማሪያችን ወደ አንተ ከፍ ይላል፤

ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ!

  

    ተንበርክከን ዝማሬውን ዘመርን፡፡ እጃችንን ወደላይ ዘርግተን ዘመርን፡፡ ራሶቻችንን ወደ ላይ አሻቅበን ከውጣችን ዘመርን፡፡ ያለንበትን ሁኔታ ትተን የእጆቻችን ጫፍ ሰማዩን የነኩ እስኪመስለን ድረስ ዝማሬውን በመዘመር ቀጠልን፤ ቀጠልን፡፡ የዝማሬውን ድምፅ ጩኸት የእስታዲየሙን ጣሪያ አልፎ የወጣ እስኪመስለኝ ድረስ ዝማሬው እየተዘመረ የእስታዲየሙ ያሉት ሁሉ ለእግዚአብሔር ልዩ የሆነ ጭብጨባ አጨበጨቡ፡፡

    ይህ ደስ የሚል የዝማሬ ድምጽ በሰማይም እንዳለው ዓይነት ዝማሬ እንደሆነ አስብኩኝ፡፡

    ነፍሴ ውስጥ ድረስ ዘልቆ እስኪገባ ድረስ እንደዚህ ዓይነት ለጌታ የሚደረግ አምልኮ አላጋጠመኝም፡፡ አምልኮዬን ከልብ በሆነ ሁኔታ በቀጠልኩበት ቁጥር ከዚህም በጨመረ ሁኔታ


አምልኮ ውስጥ ለመግባት ጥረት አደረኩኝ፡፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለሁ አንዴ ወደ ወዳጄ ዞር አልኩኝና “ከዚህ በበለጠ አምልኮ ውስጥ መግባት እፈልጋለሁ፡፡ ነገር ግን ከዚህ የበለጠ አምልኮ ውስጥ ለመግባት ግን ክፈተት አላገኘሁም!” አልኩት፡፡

    ከዓመታት በኃላ የእነዚያ የአምልኮ ዝማሬ የሰዎች ድምፆች በውስጥ ትውስታዬ ውስጥ እያስታባ ዝማሬን አሁንም እንድቀጥል ያደርገኛል፡፡ በዚያን ቀን በውስጥ ልቤ ውስጥ የተከሰተውን ነገር አሁንም አስታውሳለሁ፡፡ በእግዚአብሔር ፊተ ሆኜ ከእልፍ እና ከአላፋት ጋር ሆኜ እግዚአብሔርን ሳመልከው አሁን ከተሰማኝ መቶ እጥፍ ይልቅ እንደሚጨምር አስባለሁ፡፡ ለዚህም ነው እራሴን እስከማላውቅ ድረስ ስሜቴ ልዩ እንደሚሆን የማስበው፡፡

    እራሴን እከማላውቅ የሚለው አገላለፄ ያስገርምሃል?

    እኔ እና እንተ በእግዚአብሔር ፊት መሆናችን ስንረዳና በታላቅ ሃይሉ አማካኝነት ከውልደታቸን ድረስ እስከ “ያች ቀን” ጊዜ ድረስ እንድንደርስ ያደረገን መሆኑን ስንገነዘብ ያለንን ውስጣዊ ምስጋችንን እናጎርፋለን፤ የሰማይ ጫፍ እስኪደርስ ድረስ ከምስጋና የመነጨ ድምፃችንን አናወጣለን፡፡

   ነገር ግን ከዚህ በላይ የተለየ ተጨማሪ ነገር በሰማይ እንደሚሆን አምናለሁ፡፡

    የዚህ ምዕራፍ ትኩረት የሚያደርገውን በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ ነው፡፡

የምትሻው ነገር

ኢየሱስ ከተናገራቸው ቃላትና ምሳሌዎች እንዲሁም በሲልቨርዶም ካጋጠመኝ ክስተት ጋር አያይዤው በሰማይ ፍፁማዊ በሆነ መሰጠት እርሱን እንደምናገለግል አምናለሁ፡፡

    አዳኛችንን በምናይበት ጊዜ ዘላለማዊ በሆነና ሙሉ በሙሉ በተሰጠ ፍላጎት ለኢየሱስ ያለንን ፍቅር እንገልፃለን፤ዝማሬ እና አምልኮ ለእኛ በቂ አይሆንም፡፡ ከዚህም የበለጠ ነገር ለእርሱ ለማድረግ እንፈልጋለን፡፡

    እስቲ አስብበት፤እኔ እና እንተ አንድን ሰው ከልባችን ስንወደው ፍቅራችንን የምንገልጽበት ሁኔታ ልዩ እና ጣፋጭ ይሆናሉ ነገር ግን ከምንናገረውም በላይ መውደዳችንን ከቃላትም አልፎ በተግባር እንድንገልፀው እንፈልጋለን፡፡ ለመስጠት፣ለመርዳት፣ ለመንከባከብ እንዲሁም ለማገልገል እንዳዳለን፡፡

    ለእግዚአብሔርም ያለን ፍቅር ለመግለጽ ቃላቶች ብቻ በቂ አይደሉም፡፡ በእርሱ ዓለም ውስጥ ያሉትን እያንዳንዱን ሰው ከመውደዱ የተነሳ ልዩ ነገር አድርጓል፤ እኛን ለማደን ሲል ልጁን ሰጥቷል፡፡ (ዮሐንስ 3፡16) እናም ኢየሱስ እንደተናገረው ትልቁ የፍቅር መግለጫ መንገድ አንድ ነገር ማድረግ ነው፤ “ለወዳጆቹ ሕይወቱን አሳልፎ መስጠት” (ዮሐንስ 15፡13)

    በዚህ ምዕራፍ ውስጥ በዚህ ምድር ላይ ለእግዚአብሔር ሃሳብ ሕይወታችን እንዲመች በማድረጋችንና እግዚአብሔርን በሰማይ በልዩ ሁኔታ እንድናገለግለው የሚያደርግበትን ሁኔታ መካከል ያለውን ግንኙነት እንመለከታለን፡፡

የሕይወትህ ጥያቄ

 

ኢየሱስ ደጋግሞ የባለቤቱን ሀብት (ለምሳሌ ገንዘብ፣መሬት ወይም የወይን አትክልት ቦታ) እንዲከባከቡለት የላካቸውን ሠራተኞችን አስመልክቶ ብዙ ታሪኮችን ተናግሯል፡፡ ይህንን የመሳሰለውን ተግባር የሚያከናውነውን ለመግለፅ በመጽሃፍ ቅዱስ ላይ እንደተገለፀው “ባለአደራ ተንከባካቢ” ልንለው እንችላለን፡፡

ባለአደራ ተንከባካቢ ከአገልጋይ የሚለይበት በምንድን ነው? ባለአደራ ተንከባካቢም ሆነ አገልጋይ አንድን ሰው የሚያገለግሉ ናቸው፤ ሁለቱም ኃላፊነቶች አሉዋቸው፤ ሁለቱም ዋጋ ለማግኘት ነው የሚሰሩት፡፡ በመካከላቸው ያለው ልዩነት ባለአደራ ተንከባካቢ የባለቤቱን ሀብት በአግባቡ እንዲያስተዳድር ሃላፊነት የተሰጠው በመሆኑ ነው፡፡ ኢየሱስ በተናገራቸው ታሪኮች ውስጥ እንደነዚህ ዓይነት እንመለከታለን፤ባለቤቱ ላልተወሰነ ጊዜ ወደ ሌላ ቦታ በመሄዱ የተነሳ የባለቤቱን ንብረት በአግባቡ እንዲያስተዳድሩለት ለአገልጋይ/ለባለአደራ ተንከባካቢ ሃላፊነት ሲሰጥ፡፡

    በጊዜ ርዝማኔ ውስጥ አንድ ባለአደራ ተንከባካቢ የሚያከናውናቸውን ዋና ዋና ተግባራት ምን እንደሆኑ ለማየት እንሞክር፡፡

መጀመሪያ ……………………………………………………………………………መጨረሻ

 

ባለአደራ ተንከባካቢው ሃላፊነት ተሰጠው 

 

የንብረቱ ባለቤት ለቆ ወደ ሌላ ቦታ ሄደ

 

የንብረት ተንከባካቢው እድል ፈንታ

 

የንብረት ባለቤቱ ተመለሰ

 

ለንብረቱ ባለቤት ሽልማት ተሰጠው

 

    ከላይ በሠንጠረዥ ውስጥ ከተመለከቱት ደረጃዎች ውስጥ የባለአደራው ተንከባካቢ ሃላፊነት ሊሳካ ወይም ላይሳካ የሚችልበትና የወፊቱን እድል የሚወስንበት አለ፤ ይኸውም “እድል ፈንታ” በሚለው ደረጃ ውስጥ ነው፡፡

    ኢየሱስ ስለ ባለአደራ ተንከባካቢ ታሪኮች የተናገረበት ለአስፈላጊና ለተወሰነ ምክንያት ነው፤እርሱ በኃላ ጥሏቸው ስለሚሄድ ነው፡፡ እርሱ በሌለበት ጊዜ በምድር እንዲሰሩለት የሚፈልጋቸው ተግባራት ሊከናወኑ የሚችሉት እርሱ በወከላቸው ተከታዮቹ አማካኝነት ነው፡፡ መንግስቱ በምድር እንዲስፋፋ በሕይወታቸው ዘመን ሁሉ መስራት ያለባቸው በመሆኑ ነው፡፡ በኃላም ተመልሶ ይመጣል፤የተሰራው ስራ እንዲጣራለት ይጠይቃል፤ በስተመጨረሻ ለሁሉም እንደየስራው መጠን ሽልማት ይሰጣል፡፡ (ማቴዎስ 16፡27)

    አንተ ክርስቲያን ከሆንክ  እንደ ጥንቱ  የኢየሱስ ተከታዮች ሁሉ አንተም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ ነው ያለኸው፡፡

    ባለቤቱ በእኔ እጄ ውስጥ ያስቀመጣቸውን ሃብቱን እንዴት አድርጌ ልንከባከብለት እችላለሁ?

    በእርግጥ በየለቱ ይህንን ጥያቄ እየመለስክ ትመጣለህ፡፡ ከዚህ ቀጥሎም በምናየው ምሳሌም ይህ እውነታ ቀስ እያለ ነገር ግን በግልፅ አውን እንደሚሆን ያሳየናል፡፡ እግዚአብሔር ለአንተ የሰጠህን ሃላፊነት አውቀህ  እየተገበርከው ይሁን አይሁን በምታከናውነው ተግባር እና በሚኖርህ አቋም በአደራ እንድትንከባከበው የተሰጠህን እድል ፈንታ ወስነህ እየመረጥክ ነው፡፡

    የእኛ ባለአደራ ሰጪ በአካል በእኛ ውስጥ ስለሌለ ታማኝ ባለአደራ ተንከባካቢ ሁልጊዜ እምነት ያስፈልገዋል፤ የእኛ ባለአደራ እርሱ እንደተናገረው ነው ብሎ የሚቀበል እምነት፣አሁን እንድንሰራው የጠየቀን ጉዳዮች እርሱ ሲመለስ ውሳኝ መሆኑን የማመን እና እርሱም እንደሚመለስ ማመን፡፡

    መፅሃፍ ቅዱስ “ታማኝ” የሚለው ቃል ከመቼውም በበለጠ ሁኔታ ትክክለኛ ባለአደራ ተንከባካቢ ለሆነ ሰው መጠቀሙ የሚገርም ጉዳይ አይደለም፡፡ ጳውሎስም ይህንን ጉዳይ በተመሳሳይ ሁኔታ ሲገልፅ “እንደዚህም ሲሆን በመጋቢዎች ዘንድ የታመነ ሆኖ መገኘት ይፈለጋል፡፡” በማለት ገልጿል፡፡ (1 ቆሮንጦስ 4፡2)

 

“እኔ እስከምመጣ ድረስ ሥራህን አከናውን”

ኢየሱስ በምናን እና በመክሊት ዙሪያ የተናገራቸው ምሳሌዎች በመጀመሪያ እኩል ከሆኑ ሠዎች ይጀምርና በኃላ ግን ወደሚደንቅ ደረጃ ውስጥ ይገባል፡፡

    በሉቃስ 19 በሚገኘው ምናን በሚለው ምሳሌ ውስጥ አንድ መኮንን ሰው ከተማውን ጥሎ መሄድ እንዳለበት ይገልፃል፡፡ አስር አገልጋዮችን ይጠራና አንድ አንድ ምና (ለሦስት ዓመት የሚሆን ደመወዝ) ይሰጣቸዋል፡፡ የባለአደራው ተንከባካቢ ሃላፊነት ምንድን ነው? “እስኪመጣ ድረስ እንዲነግዱ” (ቁጥር 13)

    መኮንኑ በሚመለስበት ጊዜ ምን ያህል በሰጣቸው ምናህ እንዳተረፉ ጠየቃቸው፡፡ የመጀመሪያው አገልጋይ በተሰጠው ምናን ነግዶ አስር አጥፍ ምናን እንዳተረፈ ተናገረ፡፡ ባለቤቱም “መልካም አንተ በጎ ባሪያ፤ በጥቂት የታምንክ ስለሆንክ በአስር ከተማዎች ላይ ሥልጣን ይሁንልህ አለው” (ቁጥር 17)

    ሁለተኛውም አገልጋይ አምስት እጥፍ እንዳተረፈ ተናገረ፤ ባለቤቱም ልከኛ የሆነ ተመጣጣኝ ሽልማት ሰጠው፡፡ እንዲህም ሲል “አንተም በአምስት ከተማዎች ላይ ሁን አለው” (ቁጥር 19) በዚህ ረገድ ልብ ልንል የሚገባው ነገር ባልተናገረው ጉዳይ ላይ ነው፡፡ “መልካም አደረክ” ወይም “ በጎ ታማኝ ባሪያ” ወይም “በጥቂት ታማኝ ስለሆንክ” እንኳን አላለም፡፡ አነስተኛ የሆነ ምስጋና ባለቤቱ ማቅረቡ የሚያሳየው ባለቤቱ ከዚያ የበለጠ ነገር መስራት እንደሚችል ያገኘውን ምናን ሊያበዛ እንደሚችል ስለተረዳ ነው፡፡

    ሦስተኛው ባለአደራ ተንከባካቢ በቤቱ ምቹ የሆነ ሰፍራ በመደበቅ እንደጠበቃት ጠቅሶ የተሰጠውን አንድ ምናን መልሶ ሰጠ፡፡

    “አንተ ክፉ ባሪያ” ሲል ባለቤቱ ሲናገር በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚሸማቀቅና የሰጠውን አንዱን ምናን ነጥቆ አስር ምናን ላለው ሲሰጥ የሚኖረው ስሜት መገመቱ ቀላል ነው፡፡ መኮንኑ ያከናወነውን ተግባር ሲገልፅ “እላችኃለሁ፤ ላለው ሁሉ ይሰጠዋል፤ከሌለው ግን ያው ያለው ስንኳ ይወሰድበታል፡፡” በማለት አስገራሚ ንግግር ተናገረ፡፡ (ቁጥር 26)

    ይህንን ምሳሌ በማስተምርበት ጊዜ ትምርህቱን የሚከታተሉት ሦስተኛውን ሰው ለመደገፍ ወዲያውኑ ተጣደፉ፡፡ “አስፈላጊውን ጥንቃቄ እያደረገ አይደለምን?” ብለው ጠየቁ፡፡”በዚያላይም ይህ ሰው ምንም ነገር ያጎደለው ነገር የለም፡፡” ነገር ግን እንደ ወላጆች፣ አስተዳዳሪዎች ወይም እንደ ባለቤቶች ሆነን ውሳኔ በምንወስንበት ጊዜ በዚህ ሃሳብ ፀንተን እንድንቆይ አያደርገንም፤ አሁን ባገኘው እድል ፈንታ በተቻለ አቅም ብዛት ውጤታማ እንዲሆን የምንፈልግ በመሆናችን የተነሳ፡፡

    ለእኛ እንዲጠቅመን በሚል ኢየሱስ በምሳሌው ውስጥ የሦስቱ ባለአደራ ተንከባካቢዎች የመለሱት ምላሾች ሕይወትን ሊለውጥ የሚችል ሃሳብ ለእያንዳንዳችን እንድናገኝ የሚያስችለን ነው፡፡

የሚጠበቁ ታላቅ ተስፋዎች

እስቲ ባለአደራ ተንከባካቢን አስመልክቶ በክርስቲያኖች ዘንድ የሚስተዋሉ የጋራ የሆኑ ሦስት ትክክለኛ ያልሆኑ እምነቶችና በእነዚህ ጉዳይ ላይ ኢየሱስ እንድንመለከታቸው የሚፈልጋቸውን እውነታ እንይ፡፡

·         እግዚአብሔር የሰጠን ስጦታና መክሊት የሰጠን ቢሆንም በሚገባ መጠን ባንጠቀምበት እርሱ ግድ አይለውም ብለን እናስባለን፡፡

    ነገር ግን ከመጀመሪያው የባለአደራ ተንከባካቢ የሥራ ውጤት ላይ የተሰጠው ምላሽ መረዳት የሚቻለው እግዚአብሔር በሕይወታችን የምናገኛቸውን ሀብቶችን ተጠቅመንበት ለእርሱ መንግስት ይበልጡን እንድናስፋፋው እንደሚፈልግ ነው፡፡

·         በምድር ቆይታችን እግዚአብሔርን ላገለገልነው በምላሹ ሽልማት እንደምናገኝ ካመንን የእርሱ ሽልማት ለሁሉም በጠቅላላው በሚሰጠው ተመሳሳይ ምላሽ እንደሚሆንና በመንግስቱ ውስጥ በእኩልነት ተፈፃሚ ስለሚሆን የወዲፊት አድል ፈንታችንን የሚቀይረው አይደለም፡፡

    ከሁለተኛው ባለአደራ ተንከባካቢ እውነታ ልንጨብጥ የምንችለው ነገር እግዚአብሔር የሚሰጠን ሽልማት ሕይወታችን ለእርሱ ብለን ምን ያህል ካበዛነው ጋር ቀጥተኛ የሆነ ግንኙነት እንዳለው ነው፡፡ ለዚህኛው የሰጠው ምላሽ በሕወታችን ለዘላለም በሚኖረው ውጤት ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያለው ነው፡፡

·         እግዚአብሔር በሰጠን መክሊት ባናገለግለው የመጨረሻው ከባድ ነገር በእኛ ላይ የሚደረሰው ሽልማት አናገኝም የሚል አስተሳሰብ መኖር፡፡

    ከሦስተኛው ባለአደራ ተንከባከቢ ከተሰጠው ምላሽ መረዳት የሚቻለው እግዚአብሔርን ለማገልገል በተሰጠን ጊዜ ውስጥ መክሊታችንን ባንጠቀም ያለንን መክሊት መወሰድ ብቻ ሳይሆን በዘላለም ሕይወታችን በሙሉ ደረጃ እንዳናገለግለው የሚያግድን በመሆኑ ነው፡፡     

የባለ አስሩ ምናን ሰው

የዚህ ወሳኝ የሆነ እውነታ የሚኖረውን እድምታ በልቤ ውስጥ ሲገባ አስታውሳለሁ፡፡ ምንም እንኳን የዚህን ምሳሌ ለእኔ አዲስ ባይሆንም ራሴን እንደዚህ ብዬ ጠይቄው አላውቅም፡- እና ባለ አስሩ ምናን ባለአደራ ተንከባካቢ ነኝ?

    ይህ ጥያቄ በጥልቀት ራሴን እንድመለከትና በሕይወቴ ላይ ከፍተኛ ለውጥ እንዲመጣ ያደረገ ነው፡፡ በመጨረሻ ልዩ የሆነ ሃሳብ ወደ እኔ መጣልኝ፡፡ እግዚአብሔር በእኔ ሕይወት ውስጥ የሚፈልገው እንደ ባለአስሩ ምናን እስከሆነ ድረስ በሕይወቴም እንደ ትከክል መስፈሪያ አድርጌ ልጠቀምበት እንደሚገባ ወሰንኩኝ፡፡ ለራሴ በእርሱ ፀጋ አማካኝነት እንደ ባለ አስሩ ምናን ለመሆን ራሴን ለማስገዛት ወሰንኩኝ፡፡

    በዚህ ቅጽበት ምናልባት እንዚህ ብለህ ልታስብ ትችላህ፤ እኔ ብዙ መክሊትና እርሱን ለማስደስት የሚያስቸለኝ እድል ፈንታዎች እስከሌለኝ ደረስ እንዴት ብዬ ባለ አስር ምናን ልሆን እችላሁ?

    ለዚህ ጥያቄ ፅናትን የሚሰጥ መልስ ኢየሱስ ስለ መክሊት በተናገረው ምሳሌ ውስጥ ይገኛል፡፡ (ማቴዎስ 25፡14-30) የዚህም ታሪክ ልክ እንደ ምናን እንደተገለፀው ታሪክ ተመሳሳይ ይዘት ያለው ነው፡፡ በዚህ ምሳሌ ታሪክ ግን ኢየሱስ ለባለመክሊቶች የሰጠው የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ ነው፤”ለእያንዳንዱ እንደ አቅሙ” (ቁጥር 15)

    በዚህ ምሳሌ ውስጥ ሁለቱ ባሪያዎች በተሰጣቸው መክሊት አድርገው አተረፉበት፡፡ ባለቤቱ ሲመጣ ግን ለእያንዳንዱ የሰጠው የምስጋና ምላሽ እና ሽልማት ተመሳሳይ ነው፡፡ ለምንድን ነው? ምክንያቱም የባሪያው ሽልማቱ በተሰጠው አቅም መሠረት ባስገኘው አጠቃላይ ውጤት ላይ የሚመዘን በመሆኑ የተነሳ ነው፡፡ ባለቤቱም ለሁለቱም ያለው ቃል ተመሳሳይ ነው፡-

    “ጌታም መልካም አንተ በጎ ታማኝም ባሪያ በጥቂቱ ታምነሃል፤ በብዙ እሾምሃለሁ፤

      ወደ  ጌታህ ደስታ ግባ አለው፡፡ ሁለት መክሊትም የተቀበለው ደግሞ ቀርቦ ጌታ ሆይ    

     ሁለት መክሊት ሰጥተኸኝ ነበር፤ እነሆ ሌላ ሁለት መክሊት አተረፍኩበት አለ፡፡ ጌታውም 

    መልካም አንተ በጎ ታማኝም በሪያ በጥቂቱ ታምነሃል ብዙ እሾምሃለሁ፤ ወደ ጌታህ ደስታ 

   ግብ አለው፡፡” ከቁጥር 21-23

    በተመሳሳይ መንገድ አንተ እና እኔ ኢየሱስ የሚሸልመን በሰጠን ነገር ላይ ምን ያህል እንደ ሰራን በመመዘን ነው፡፡

    አንተ ልብስ ሰፊ ነህ ወይስ የሀገር መሪ ነህ? የፋብሪካ ሰራተኛ ወይስ ወጣት እናት? የአካባቢ ቤተ ክርስቲያን መጋቢ ወይስ ግንበኛ? እያንዳንዱ ደቀ መዝሙር በተሰጠው እድል እኩል ውጤታማ ሊሆን ይችላል፤ እናም ተመሳሳይ የሆነ ትልቅ ሽልማት ወፊት ለማግኘት፡፡ በእርግጥ በታሪክ ከፍተኛ ተሰጥኦ ካለው ሰው ጋር በተመሳሰለ ሁኔታ የአንተም የመጨረሻ እድል ፈንታ ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፡፡

    የልጆች እናት ለሆነችው ለሸይላ የእርሷ አስር ምናን ሊሆን የሚችለው በተቀናጀ እቅድ በጎረቤቶቿ ላሉ እናቶች በሚገጥማቸው ችግሮች ጠንካራ ሆነው እንዲወጡ ማገዝ ሊሆን ይችላል፡፡

    በአሪዞና ላለው አንቀሳቃሽ አስር ምናን ማለት “የሚሰሩ ቢዝነሶች” የሚኖራቸውን እድምታ ማሳየት ሊሆን ይችላል፡፡ በሚያስገረም ሁኔታ በመካከለኛው አሜሪካ ላለው ፕሮጀክት ያለውን ጊዜ በማብቃቃት የግንባታ ስራ አገልግሎት መስጠት ሊሆን ይችላል፡፡

    ከአስራ አምስት አመቷ ጀምሮ እውር ለሆነችው ጄነፈር ለእርሷ አስር ምናን ሊሆን የሚችለው ያለባትን ገደብ ማለፍ መቻል ሊሆን ይችላል፡፡ እርሷ አሁን አይነ ሥውርነቷን “እንደ አስቸጋሪ ስጦታ” ትቆጥረዋለች፤ በንግግሯና በሙዚቃዋ ብዙ ሺ ሰዎችን እየደረሰች ነው፡፡

    አሁን እግዚአብሔርን በታማኝነት ማገልገል ማለት ብዙ ሐጢያትን አለማድረግ ብቻ ሳይሆን “የተለመደውን ንግዳችንን ማከናወን” ወይም እስከ መጨረሻው ሳናቋርጥ መጓዝን ሊሆን ይችላል፡፡ እውነተኛ ታማኝነት ልክ ባለአደራው ተንከባካቢ ከመደበኛ በላይ ልዩ የሆነ ኢንተርፕሩንሪያል ሥራ ከመስራት ጋር በጣም የቀረበ ነው፡፡

የባለአደራው ተንከባካቢ ሽልማት

በዚህ ምዕራፍ መጀመሪያ ላይ እንደገልፅኩት ሁላችንም  በሰማይ እግዚአብሔርን ማገልገል እንደምንሻ ገልጬ ነበር፡፡ ተግባራዊ ለመሆን አንድ አገልጋይ ያለውን መሰጠትን የሚያሳይበት መንገድ ነው፡፡ የእግዚብሔርን ፍቃድ ለማከናወን የምንችልበት ልዩ አጋጣሚ ቢኖር የፍቅር የሆነ አገልግሎት ለእግዚብሔር ለዘላለም በመስጠታችን የምናገኘው ትልቁ ሽልማታችን ነው፡፡

    በትክክል ምን ያህል እድል እግዚአብሔርን በሰማይ ለማገልገል ባለአደራ ተንከባካበዎች ይኖራቸዋል? ከምድር ተቃራኒ በሆነው በሰማይ መንግስት ማገልገል ማለት መግዛት ማለት ነው፡፡ ይህንን እውነታ አዳምና ሔዋን ከሚኖሩበት ኤደን ገነት ማግነት እንችላለን፡፡ በዘፍጥረት ጊዜ እግዚአብሔር ሠውን ወንድና ሴት አድርጎ ሲፈጥራቸው በምድር ላይ ለተወሰነ ስራ ነው፤ በምድር ያሉትን ፍጥረታትን በባለአደራነት በማስተዳደር እርሱን ማገልገል ነው፡፡ ኢየሱን ይህንን ነገር ለደቀ መዛሙርቶቹ ሲያረጋግጥላቸው በምድር ለሠራችኃቸው ሥራዎች በአስራ ሁሉቱ ላይ ተቀምጣችሁ በእስራኤል ነገድ ላይ ፈራጆች እንደምትሆኑ ነው፡፡ (ማቴዎስ 19፡28)

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


6

 

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">ዋጋን መልሶ የሚሰጥ እግዚአብሔር</b>

“ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፡፡ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፡፡”

ኢየሱስ በማቴዎስ 6፡19-20

ከንተኪ በነበረው የቤተሰብ ውይይት ጊዜ የሻይ ቡና እረፍት ሰዓት ላይ በነበርኩበት ጊዜ ዊል ከተቀመጥኩበት ወንበር አጠገብ ቆመ፡፡ እድሜው ወደ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ ነው፡፡ ለአንድ ተልዕኮ ለሚሆን ፕሮጀክት ገንዘብ እንድለግስ ጠየቀኝ፡፡

“ገንዘቤን ለምን አገልግሎት ታውለዋለህ?” ብዬ ጠየኩት፡፡

    ዊል ራዲዮ አወጣ፡፡ “ይህ ራዲዮ በፀሃይ ጉልበት ነው የሚሰራው” በማለት በኩራት ሆኖ ነገረኝ፡፡ “ የሚያገለግለውም በደን ውስጥ ላሉ ሠዎች ነው፡፡ በዚህ ራዲዮ አማካኝነት ሰዎች መረጃን ሊያዳምጡ ይችላሉ፤ስለ ኢየሱስ ማድመጥም ይችላሉ፡፡” በማለት ቀጠለ፡፡

    በዚህ ሂደት ቅጽበት ለዊል አንድ ነገር ላበረክትለት ወሰንኩኝ፡፡ “ምን እንድነግር ፈለክ” ብዬ ነገርኩት፡፡ ቀጠዬ “አንተ ላሰብከው ፕሮጀክት ገንዘብ ልሰጥህ እችላለሁ ነገር ግን በመጀመሪያ ገንዘብ አንተ መስጠት አለብህ የሚል ሕግ አለኝ፡፡” በአንደኛው በለገሰው ካርድ ላይ የእኔን ሀሳብ ፃፍኩን፡-

                ዊል፡-

ለአንድ ሰው አምስት ዶላር የምትሰጥ ከሆነ

አንተ በሰጠው መጠን እጥፍ እሰጥሃለሁ፡፡

ለስድስት ሰው ስድስት ዶላር የምትሰጥ ከሆነ

አንተ የሰጠኸውን ሦስት እጥፍ እሰጣለሁ፡፡

ለአሰራ አንድ ሰው ሃያ ዶላር የምትሰጥ ከሆነ

አንተ የሰጠኸውን አራት እጥፍ እሰጣለሁ፡፡


    በስሜ ረድፍ ፊርማዬን አኖርኩት ዊልም በካርዱ ላይ የተፃፈውን አነበበው፡፡ አንብቦ እንደጨረሰው አይኑ ልክ እንደ ስኒ ማስቀመጫ ትልቅ ሆነው አገኘኃቸው፡፡ በኃላ ግን ከመቅፅበት ፊቱ ወደቀ በማስከተልም በወለሉ ላይ ማተኮር ጀመር፡፡

    “ሃሳቤን አልወደድከውም ብዬ?” ብዬ ጠየኩት፡፡

     “አዎ” አለኝ እግሮቹን በመሬት ላይ እያንሸራተተ፡፡

      “ጥሩ ምን ልታደርግ ነው ያሰብከው?”

      “ምንም”

      “ምንም?”

      “አልችልም” አለ፡፡ “እኔ ያለኝን ሁሉ ሰጥቻለሁ፡፡”

    ውስጤ ልዩ ስሜት ተሰማኝ፡፡ “ላሰብከው ለገንዘብ ማሰባሰቢያ ፈንድ ሁሉንም ገንዘቤን አውዬዋለሁ ማለት ነው?” ብዬ ጠየኩት፡፡

    ራሱን ነቀነቀ፡፡

    “ከዚህ በኃላ ላለው ኮንፍረንስ ምንም ዓይነት ምግብ መግዛት አትችልም ማለት ነው?”

    አሁንም ራሱን ነቅንቆ መለሰ፡፡

    በዚህ ጊዜ ምን ማድረግ እንዳለብኝ ተረዳሁ፡፡

    “በእርግት ዊል” ብዬ ቀጠልኩኝ “ያለህን የሰጠህ ከሆነ እኔም ያለኝን እሰጣለሁ የሚልም ሕግ አለኝ” አልኩት፡፡

    ይህ ሁሉ ሲሆን ለመጓጓዢያ የሚሆን በሚል ብዙ ገንዘብ ያወጣሁት ካሽ ነበረኝ፡፡ ቦርሳዬን ለማግኘት ከጠረጴዛው በታች ሆንኩኝ፤ከባንክ የተሰጠኝን ገንዘብ ሁሉ ለዊል ሰጠሁት፡፡

    በዚህ ነገር ማንም እንደሚገረም እርግጠኛ አይደለሁም፤ ዊል ወይስ እኔ፡፡ አሁን የሁለታችንም አይን እንደ ስኒ ማስቀመጫ ተልቋል ነገር ግን ሁለታችንን ደስተኞች ነበርን፡፡

    ከቢል ጋር በነበረኝ ቆይታ ከመስጠት ጋር በተያያዘ አንድ ትልቅ ቁም ነገር እንድጨብጥ አስችሎኛል፤ ለእግዚአብሔር በምድር ቆይታዬ ለምሰጠው ማናቸውም ነገር በሰማይ ዋጋዬን ከፍ አድርጎ እንደሚሰጠኝ፡

    በዚህ ምዕራፍ ያለን ገንዘብና ሀብት በሰማይ ትልቅ ነገር እንድናገኝበት ምን ማድረግ እንዳለብን ኢየሱስ በተናገረው ላይ በዝርዝር እንመለከታለን፡፡

የቸር ተመሳሳይ እቅድ

ኢየሱስ ስለ ገንዘብና ሀብት በእርግጥ ምን ዓይነት ትምህርት አስተማረ?

ኢየሱስ ባለፀጋውን ያለውን ሀብትና ገንዘብ ትቶ ሊከተለው እንደሚገባ ሲነግረው በመስማቱ   ጴጥሮስ ምንአልባት ለመጀመሪያ ጊዜ በዚህ ረገድ የሰማ እርሱ ነው ብለን ልንገምት እንችላለን፤”ኢየሱስም፤ ፍፁም ልትሆን ብትወድ ሂድና ያለህን ሽጠህ ለድሆች ስጥ፤መዝገብም በሰማያት ታገኛለህ፤መጥተህም ተከተለኝ አለው፡፡” (ማቴዎስ 19፡21)

    ባለፀጋው በኢየሱስ ለቀረበለት ጥያቄ ወደ ጎን ትቶ ሲሄድ ጴጥሮስ ጠጋ አለና ግልፅ የሆነ ጥያቄ ጠየቀው፡

     “በዚያን ጊዜ ጴጥሮስ መልሶ እነሆ እኛ ሁሉን ትተን ተከተልንህ፤እንኪያስ ምን እናገኝ ይሆን? አለው፡፡” ቁጥር 27      

    ኢየሱስ ጴጥሮስ ባሳየው ግላዊ አመለካከት ባለማዘኑ ደስ ብሎኛል፡፡ ወይም ፈገግ ብሎ “በሰማይ ባለው መዝገብ እኔ ብዙ ትኩረት አልሰጥም” ብሎም አልመለሰለትም፡፡ ይልቁንም ትልቅ የሆነ ሚስጥር ገለጠለት፡፡ ኢየሱስ ለጴጥሮስና ለደቀ መዛሙርቱ መንግስቱን በሚያቋቁምበት ጊዜ በእስራኤል ሕዝብ ላይ ገዢ እንደሚሆኑ ነገራቸው፡፡ ከዚያም በማስከተል ማንም ያለውን ትቶ የተከተለኝ በሰማይ መቶ እጥፍ እንደሚከፍለው ተናገራቸው፡፡(ማቴዎስ 19፡29)

    መቶ እጥፍ ማለት 10,000 ፐርሰንት ዋጋን መልሶ ከማግኘት ጋር የሚመጣጠን ነው!

    የዊል የነበረው ሁኔታ ኢየሱስን ለመከተል ያለንን ነገር ብንተው እግዚአብሔር ለእያንዳንችን ለከፈልነው መሥዕዋት ምን ያህል ሽልማት ሊሰጠን የሚችል ሰለመሆኑ ፍንጭ ሊሰጠን የሚችል ነው፡፡ ለዊል ላደረገው በጎ ተግባር ያደረጉት “ቸርነት” እግዚአብሔር ካስቀመጠልን ላቅ ያለ ተሰፋ ጋር ሲመዘን በጣም ኢምንት ነች፡፡

ኢየሱስ መዝገባችሁን ተጠቀሙበት ሲል ምን ማለቱ ነው

ምንአልባት ኢየሱስ ስለመዝገብ የተናገረው የምናገኘው በተራራው ስብከቱ ውስጥ ነው፡-

     “ብልና ዝገት በሚያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በሚሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በምድር ላይ መዝገብ አትሰብስቡ፡፡ ነገር ግን ብልም ዝገትም በማያጠፉት ሌቦችም ቆፍረው በማይሰርቁት ዘንድ ለእናንተ በሰማይ መዝገብ ሰብስቡ፡፡”

                                                      ማቴዎስ 6፡19-20

    ልክ እንደ እኔ ከልጅነትህ አንስቶ በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ ካደክ ከላይ የተመለከተው ጥቅስ መንፈሳዊውን ከስጋዊው ነገር መፈለግ አስፈላጊ እንደሆነ አድርገህ ልትተረጉመው ትችላለህ፡፡ ነገር ግን ኢየሱስ በዚህ ጥቅስ ውስጥ እየተናገረ ያለው በእጃችን ያለውን መዝገብ እንዴት መጠበቅ እንዳለብን ነው፡፡ በሠማይና በምድር ላይ ለሚገኘው መዝገቦች ተመሳሳይ የሆነ ቃል ነው የተናገረው (በግሪክኛ ሲተረጎም ቴዛሮስ)  በሰማይ ያለው መዝገብ ምን እንደሚመስል አሊያም እንዴት ሊለካ እንደሚችል አልተናገረም፡፡ ይልቁንም በሰማይ ያለው መዝገብ በጣም ውድ እንደሆነ ነው፡፡

    የአንተ የሒሳብ ሹም “ያለህን መዝገብ በባንክ ሀ ብታስቀምጥ ትከስራለህ ነገር ግን በባንክ ለ ብትታስቀምጥ ትርፋማህ ትሆናለህ” ብሎ ተናገረከ ብለን እናስብ፡፡

    ከላይ በተመለከተው አባባል በባንክ ሀ ስለሚቀመጠው ገንዘብ ጥሬ የገንዘብ ብሮች መሆናቸውን ከተረዳህ በባንክ ለ ውስጥ ማስቀመጥ አለብህ ብላ ስትመክረው የማይጨበጠውን መንፈሳዊ መዝገብ ነው ብላ አታስብም! በመሆኑም የዘላለም መዝገብ ከምንፈልገውና ከምንጓጓለት መዝገብ አሳንሰን የምንመለከተው ለምንድን ነው?

    በዚች አንድ ጥቅስ (ማቴዎስ 6፡20) ስለ መዝገብ ያለንን ሦስት የጋራ የተሳሳቱ አመለካከቶችን አፈረሳቸው፡-

1.  ባለህ መዝገብ ልታደርግ ስለሚገባው ነገር፤ “ማከማቸት”፡፡ “ማከማቸት” የሚለው ግስ በግሪክኛ አቻው ግስ ኢየሱስ የተናገረው በትዕዛዛዊ መልክ እንደተናገረ እንረዳለን፡፡ ስለሆነም ማከማቸት እንዳለብን የሚገልፀው እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን እቅድ የምንረዳበትና ልክ እንደ መመሪያ ታዘን ልንተገብረው የሚገባ ነው፡፡

2.  ለማን ማከማቸት እንዳለብን፤ “ለራሳችን”፤ እያንዳንዳችን መዝገቦቻችንን ልናከማች ይገባናል፡፡ ኢየሱስ እንደተናገረው በሰማይ ራሳችን መዝገቦቻችንን ካላከማችንን ማንም በሰማይ መዝገቦቻችንን ሊያከማችልን አይችልም፡፡ ለዚህም ነው ኢየሱስ በሰማይ መዝገቡን ሳያከማች የቀረውን “ሞኝ” ያለው፡፡(ሉቃስ 12፡13-21) እግዚአብሔር ራስ ወዳድነትን ሳይሆን ራስ ወዳድነትን የማይወደውን ነው፡፡ ከዚህ በኃላ እንደምንመለከተው በሰማይ መዝገባችንን እንድናከማች በምድር ሳለን ያለንን መዝገብ ለሌሎች ልንሰጥ ይገባናል፡፡

3.  የት መዝገባችንን ማከማቸት እንዳለብን ፤”በሰማይ” የምናከማችበት ቦታ ወሳኝነት አለው፡፡ ያለንን መዝገብ በምድር ብናከማች ለመዛግና ለመጥፋት እንደሚጋለጥ ኢየሱስ አስታውቋል፡፡ እውነታው መዝገብህን በደህንነት ሊኖር የሚችለው በሰማይ ስታኖር ብቻ ነው፡፡

    አሁን ይህንን ልትጠይቅ ትችላለህ፡-“በሠማይ መዝገብ እንዲኖረኝ ለምን ያስፈልጋል?”

    ጥያቄውንም እረዳዋለሁ፡፡ ኢየሱስ በተለያዩ ስፍራዎች ስለ መዝገብ በተናገራቸው ንግግሮች በመነሳት መዝገባችንን በሰማይ ማከማቸት ለዘላለም ሕይወታችን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ልንደመድም እንችላለን!

    በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ ስግብግቦች፣ ቀናተኞችና መሰሪዎች የሌሉበት በመሆኑ ባገኘነው መዝገብ በትክክል የምንደሰትበት ከመሆኑም በላይ ለንፁህና ትክክለኛ ዓላማ ልናውልበት እንችላለን፡፡ ከዚህ በኃላ እንደምንመለከተው በመዝገባችን ለእርሱ እንድናውለውለውና እንድናገለግልበት ያግዘናል፡፡

መዝገባችንን እዚህና እዚያ ማግኘት

ከአንድ አመት በፊት ዳርሊን እና እኔ ረዥም መንገድ ስንጓዝ አስታውሳለሁ፡፡ በመንገድ ስንጓዝ ባለንበት ጊዜ ከፊታችን ያለው ተሽከርካሪ አስፈላጊ ካልሆኑ ዕቃዎች በተጨማሪ የግላችን አስፈላጊ የሆኑ መዝገቦችን የያዘ መሆኑን ተመለከትን፡፡ ተሸከርካሪውን በመኪና በኃላ ለመከተል  ስለወሰንን በተሽከርካሪው ውስጥ ያሉት ግላዊ ሃብቶቻችንን ለማግኘት የምንችለው ከሣምንት በኃላ ወደ አዲሱ ቤታችን ስንደርስ ነው፡፡

    በተመሳሳይ መልኩ በሰማይ ያለንን መዝገብ ለማግኘት አሁን በሕይወታችን ያለውን መዝገብ እንጥለዋለን፡፡ አሁን የሚያስፈልገንን ነገር አጥተናል፡፡ ነገር ግን ትክክለኛው ሃብታችንን በአግባቡ ከያዝን ከፊታችን መምጣቱ የማይቀር ነው፡፡

    ይህንን እየተንቀሳቀሰ እንደለ የእግዚአብሔር እቅድ አድርገህ ውሰድ፤ መዝገብህን በሰማይ ለማኖር ቀድመህ መላክ እንዳለብህ፡፡   

    ይህንን እንዴት አድርገን ልንፈፅመው እንችላለን? አንድን ቀን ኢየሱስ የሚንቀሳቀሰውን እቅዱን ለደቀ መዛሙርቱ ገለፀላቸው፡

       “ያላችሁን ሽጡ ምፅዋትም ስጡ፤ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማይጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ” ሉቃስ 12፡33

    ይህ ጥቅስ በግልፅ በምድር በምናደርገው መዝገበ እና በሰማይ የሚኖረውን የድርጊቱን ውጤት ያለውን ትስስር የሚያሳይ ነው፡፡ አሁን ያለንን “ለድሆዎች ብንሰጥ” ወድ የሆነ ነገር “ለረሳቸው እንደሚያስገኙ” ለወዳዶቹ ነግሯቸዋል፤ “በሠማይ ስለሚገኝ መዝገብ”

    ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ ከተናገራቸው ንግግር መዝገብ አስፈላጊ እንዳልሆነ ወይም ሌላ የሆነ መዝገብ እንዲያገኙ እንዳልተናገራቸው መረዳት እንደሚቻል ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በትክክል ተቃራኒውን የሆነው ነገር ነው የነገራቸው! ለራሳቸው የዘላለም የሆነ መዝገብ ማከማቸት እንደሚያሰፈልጋቸው እና ለዚህም በሰማይ ብዙ እንዲያከማቹ ነግሯቸዋል፡፡

    ጳውሎስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ አቅም ላላቸው አባላት “እውነተኛውን ሕይወት ይይዙ ዘንድ ለሚመጣው ዘመን ለራሳቸው መልካም መሠረት የሚሆንላቸውን መዝገብ እየሰበሰቡ፤መልካምንም እንዲያደርጉ በበጎም ስራም ባለ ጠጎች እንዲሆኑ፤ ሊረዱና ሊያካፍሉም የተዘጋጁ እንዲሆኑ ምከራቸው፡፡” እንዲያደርጉ ጢዎቴዎስን አዞት ነበር፡፡ (1 ጢሞቴዎስ 6፡18-19)

    የአስተምህሮቱ ሂደት ላይ እስኪ ልብ በል፤የኢየሱስ ተከታዮች “ለራሳቸው” ማከማቸት እንዳለባቸው፤ለዚህም ምክንያቱ የማይቋረጥ ግንኙነት በመኖሩ ነው፡- የሚተገብሩት ተግባር “ሊመጣ ላለው ጊዜ ወሳኝ የሆነ ሚና ሊጫወት መቻሉ ነው፡፡”

    “ሊጠፋ በማይችል መዝገብህን በሰማይ” ማከማቸት ትፈልጋለህን? አሁን ለእግዚአብሔር ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገባቸው ላይ ያለህን ነገር አውል፡፡

ማናቸውም ያለህ ነገር እንደ ብድር ነው

አሁን እንደምትገምተው ስለ ባለአደራ ተንከባካቢ የተጠቀሱት መርሆዎች (ሃላፊነት፣ማሳደግ እና አቅም) በሚኖረን መዝገብ ላይ ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡

    ገንዘብ እና ሃብት በሰማይ ስለሚኖራቸው ስፍራ አስመልክቶ ኢየሱስ ባስተማረው አንደኛው ትምህርት ውስጥ ኢየሱስ እንዲህ አለ:-

    “ከሁሉ በሚያንስ የታመነ በብዙ ደግሞ የታመነ ነው፤ ከሁሉ በሚያንስም የሚያምፅ በብዙ ደግሞ አመፀኛ ነው፡፡ እንግዲያስ በዓመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኃል? በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ የእናንተን ማን ይሰጣችኃል?” ሉቃስ 16፡10-12

    እዚህ ላይ አንድ ባለአደራ ተንከባካቢ የእርሱ ባልሆነው ገንዘብ ሳቢያ እንዴት ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ ነው፡፡ ሳንደነቅበት “ታማኝ” የሚለውን ቃል አራት ጊዜ ተጠቅሞበታል!

    የሚያስደንቀው ነገር ቢኖር ታማኝ ለሆነ ባለአደራ ተንከባካቢ የተሰጠውን መዝገብ በአግባቡ ቢጠብቅ ሊያገኝ የሚችለውን ተስፋ ነው፡፡ አንተ ልትገምት እንደምትችለው በሰማይ ሌላ ተጨማሪ መዝገብ በባለአደራነት እንዲከባከብ አይደለም ነገር ግን “ባለቤትም” ጭምር እንደምትሆን ነው፡፡ “ጽድቅ የሌለበትን ገንዘብ” በምድር ከማግኘት ይልቅ “ትክክለኛ ሃብት” የሆነውን በሰማይ ታገኛለህ፤ “የሌላው የሆነው ሀብት ከማስተዳደር” ይልቅ “የራስህ የሆነውን ሃብት” ይኖራሃል፡፡

    በሌላ አገላለፅ አሁን የእኔ ነው ብለህ በምታስበው መዝገብ ተገቢውን ነገር ካደረክ በኃላ ባለቤት የምትሆንበትን ነገር ታገኛለህ፡፡

የእድል ፈንታዎችን ድምር ውጤት

የምታውቃቸውን ሠዎች ዙሪያ ልትመለከት ትችላለህ እናም በምድር ያለውን መዝገብህን እንዴት መስጠት እንደምትችል ምሳሌዎችን ልታገኝ ትችላለህ፡፡ ከዚህ በታች የተመለከቱት ጥቂት የራሴ የምላቸው ናቸው፡-

·         ቤት አልባ ለሆኑት ሰዎች ማርሴለስ ያሉትን ትላልቅ የልብስ ማስቀመጫዎቹን ሰጠ (እናም ማርኤለስ በልብስ ሽያጭ ውስጥ ከፍተኛ አድናቆትን ያገኘ ሰው ነው)

·         ኢራና ፍራንሲስ ለመድኃኒት ቅመማ ሂደት ፕሮግራም ለሚያከናውኑት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ራሳቸውን ለመደጎም እንዲያስችላቸው ከጡረታቸው የሚያገኙትን ገንዘብ አዋሉበት፣

·         በካንሰር ሕመም ምክንያት ፀጉሩን ላጣው ወዳጃቸውን ለማገዝ በሚል ሠባቱ ሠዎች የራሳቸውን ፀጉር ተላጩ፣

·         በተስፋ መቁረጥ ውስጥ ለነበረው ወዳጅዋ በጣም የምትወደውን የሳለችውን ሥዕል ማሪባ ሠጠች፣

·         ናታንና አና ትልቅ የሆነ ቤታቸውን በመሸጥና አነስተኛ የሆነ ቤት በመግዛት ቀሪውን ገንዘብ ለእግዚአብሔር ስራ አዋሉት፡፡

    የምትሰጠው ስጦታ ምንም ትንሽ ይሁን ትልቅ ለሁለት ቀላል ጥያቄዎች መልስ በመስጠትህ ሕይወትህን በእንቅስቃሴው ውስጥ እያስገባህ ነው፡፡

1.  “ምን ዓይነት መዝገብ እግዚአብሔር ለእኔ ሰጠኝ?” ሁላችንም ተመሳሳይ አቅምን እንዳለን በመጨረሻው ምዕራፍ ያየነው መርህ በባለአደራነት ለምንከባከው ንብረትም ተፈፃሚ ሊሆን የሚችል ነው፡፡ እግዚአብሔር ለእርሱ ታማኝነት ያለን ሁኔታ የሚመዝነው ባለን አቅም ላይ ተመስርቶ ነው፤ በእጃችን ከሚገኝ ውስጥ ምን ያህሉን ሰጥተናል በሚል ምዘና መሰረት፡፡ ኢየሱስ ያቺ መበሊቲቱ የሰጠችውን ሁለት ዲናር ሳንቲም ሀብታሞች ከሰጡት ይልቅ ሲመዛዘን የላቀ በሆኑ በከፍተኛ ሁኔታ አመስግኗቷል፡፡ (ሉቃስ 21፡4)

2.  “እግዚአብሔር በሰጠኝ መዝገብ ምን እንዳደርግበት ነው የሚፈልገው?” ለቤተ ክርስቲያን ከሰጠኸም በኃላ ተጨማሪ እንዴት መስጠት እንደምትችል መሪትን እንድታገኝ እግዚአብሔርን ጠይቅ፡፡ በአንድ ጉዳይ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ከሌላው ኢንቨስት ከምታደርገው ጉዳይ ጋር እኩል አይደለም፡፡ እግዚአብሔርን ከሁሉ በላይ ግድ የሚሰጠውን እንድታውቅ ጠይቀው፡፡ ለምሳሌ ለአንድ ታዋቂ ለሆነ ሲቪክ አካል የምትሰጠው ገንዘብ ልክ የቤተ ክርስቲያን ተልዕኮ እንዲሳካ እንደምትሰጠው ገንዘብ ያስደስተዋል ወይ?

    እኔ የማውቃቸው ጓደኞቼ በገንዘብ አጠቃቀማቸው ታማኝ ሆነው ስለተገኙ በሚኖራቸው ማህበራዊ ግንኙነት ነፃ ናቸው፡፡ እነዚህን ሰዎች አደንቃችኃለው ምክንያቱም ባለህ ገንዘብ እግዚአብሔርን ማገልገል ካልቻልክ የምታገለገልለው ገንዘብን እንደሆነ ጠንቅቀው የሚያውቁ በመሆኑ የተነሳ ነው፡፡

ተቀናቃኝ ባለቤት

እግዚአብሔርን እንድታገለግለው የሚፈልገው መዝገብ በሕይወትህ ውስጥ ለባለቤቱ ታማኝ እንዳትሆን ሊፈትን የሚችል ከፍተኛ አቅም ያለው እንደሆነ ኢየሱስ ተናግሯል፡፡ እንዲህ ሲል፡-

“ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቸለው ማንም ባሪያ የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላልና ሁለተኛውንም ይወዳል፤ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፡፡ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም፡፡”

ሉቃስ 16፡13

    እግዚአብሔርን በምታገለግልበት ጊዜ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለእርሱ ፍቃድ ማከናወኛ እያደረከው ነው፡፡ ገንዘብን እያገለገልክ ከሆነ በእግዚአብሔር ገንዘብ የራስን ፍላጎትህን እያገለገልክበት ነው፡፡ ይህንን በምታደርግበት ጊዜ በውስጥህ ያለውን ደመ ነፍስ እየተከተልክ ከሆነ ገንዘብህን “በዚህ ላይ”  ታውላለህ፡፡

    ኢየሱስ ግን እንዲህ አለ “መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና፡፡” (ማቴዎስ 6፡21)

    እናም እስቲ ልጠይቅህ፤ ልብህ አሁን ያለው የት ነው? በዓላማና በቸርነት ያለህን ገንዘብ በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ እያዋልክ ካልሆነ ይህ የሆነው ልብህ በዚያ አንዳልሆነ ላረጋግጥልህ እውዳለሁ፡፡

    መፍትሔውም ቀላል ነው፤ምናልባትም አስቸጋሪ ግን ያለምንም ጥርጣሬ ሕይወትን ሊቀይር የሚችል ነው፡፡ ልብህ ባዘመመው እንድሄድ አትፍቀድለት ወዳጄ ምክንያቱም እድሉን ዳግመኛ ልታገኛው የማትችል በመሆኑ፡፡ ይልቁንም ኢየሱስ የተናገረውን መሰረት አድርገው የሕወትህን አቅጣጫ ምራ፡፡ ያለህን መዝገብ ለሰማይ ፋይዳ ሊኖረው በሚችል ጉዳይ ላይ አኑረው…. እናም ልብህም በትክክለኛው አቅጣጫ ትጓዛለች፡፡

 

 

 

 

 

 


7

<b style="mso-bidi-font-weight:normal">የመጀመሪያው ቁልፍ</b>

                                

   “ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር

     ወደ ዓለም አልላከውና፡፡”

                           ኢየሱስ፤ በዮሐንስ 3፡17

 

ዲ ለየት ያለ አመለካከት ነበረው፡፡ በቤተ ክርስቲያኑ ፊት ለፊት ባለቤቱ አስተዋወቀችኝ፤ከዚያም “ባልጠበኩት ሁኔታ” ሌላ ጉዳይ ለማከናወን ወደ ሌላ ቦታ ሄደ፡፡ ሩዲ ጥሩ መንፈስ ባልተሰማው ሁኔታ እዚያው ቆመ፤እጆቹን በኪሶቹ ውስጥ ከቶ፡፡ በሕይወቱ ጉዞ ውስጥ መፍትሔ የሚያስፈልገው ነገር እንዳለ ከሚያስተላልፈው አካላዊ እንቅስቃሴና ከእኔም በዚያ ቦታ ከመገኘቴ አኳያ ላረጋግጥ ቻልኩኝ፡፡

    ፈገግ ብዬ በምን ሁኔታ ልረዳው እንደምችል ጠየኩት፡፡

    “ባለቤቴ በሐይማኖት ጉዳይ እንዳዘነብል ትፈልጋለች” የቤተ ክርስቲያኑን ምንጣፍ በእግሩ እያሻሸ አለኝ፡፡

    ለምን ይህ እንደሆነ ጠየኩት፡፡

    ፊቱን ጨምደድ አደረገ፡፡ “ወደ ሲኦል መሄደ ስለማልፈልግ” አለኝ፡፡

    “ወደ ሲኦል በቅርብ ጊዜ ለመሄድ እቅድ አለህ?” ብዬ ጠየኩት፡፡

    ወደ እኔ ተመለከተ፤ ከዚያም ሳቁን ለቀቀው፡፡ የመጽሃፍ ቅዱስ አስተማሪ እንደእነዚህ ዓይነት ቀልድ ንግግሮችን የሚናገር መሆኑን ሲረዳ ቀለል አለው፡፡

    “እናም” ብዬ ቀጠልኩኝ “ከእግዚአብሔር ፊት ስትቆም ከሲኦል ሊያድንህ የሚችለው ነገር ምንድን ነው?”

    ትንሽ ዝምታ ከተፈጠረ በኃላ ሩዲ ሳቅ አለና “ በእርግጥ እንደዚህ አድርጌ አስቤው አላቅም” ትንሽ ካንገራገረ በኃላ “ታውቃለህ እኔ መጥፎ ሰው አይደለሁም፡፡ ልክ እንደ ጓደኞቼ ከባለቤቴ ላይ ሌላ ሴትን የምደርብ አይደለሁም፡፡ በሁሉም ጊዜ ጥሩ ሰው ለመሆን ጥረት አደርጋለሁ….”


 

    ካለበት ጥያቄ ነፃ እንዲሆን ልረዳው ወንኩኝ፡፡ “እናም እግዚአብሔር ትልቅ መስፈሪያ ይኖረው ይሆናል፤አንተስ ይሄ ይኖረዋል ብለህ አታሳብም?” በአንደኛው ጎን በኩል የአንተ ሐጢያቶች፤ ሃጢያት እንደምትሰራ ታውቃህ አይደል ሩዲ?”

    ራሱን ነቀነቀ፡፡

    ቀጠልኩኝ፡፡ “በሌላይኛው በኩል ደግሞ ለባለቤትህ፣ ለልጆችህ እና ለሕብረተሰቡ ወዘተ…  ያደረከውን መልካም ስራዎች፡፡ በትክክለኛው መንገድ እየሄድኩኝ ነው አይደል?”

    በልዩ አትኩሮት ሩዲ ራሱን ነቀነቀልኝ፡፡

    “እግዚአብሔር ሕይወትህን በዚህ ትልቅ መስፊያ ውስጥ ሲያስቀምጠው ከመጥፎ ይልቅ ጥሩ የሆኑት ይኖሩሃል፤ እናም ሁሉም ነገር መልካም ይሆናል፤ አይደል?”

    ፈገግታ ፊቱን ሸፈነው፡፡ መልሱን ራሴው ሰጥቼ ወደ ተፈለገው ጉዳይ ለመግባት ያለኝን እንቅስቃሴ ወደደው፡፡ እኔም በዚህ መንገድ መሄዴ ትክክል እንደሆነ ነገርኩት ግን ጥያቄ እንዳለኝ አሳወቁት፡፡ እስክሪፒቶዬን አወጣሁና ልክ እንደዚህ መስመር አሰመርኩኝ፡-

 

 ሙሉ በሙሉ ክፉ                                           ሙሉ በሙሉ ጥሩ

(0 ፐርሰንት ጥሩ)                                            (100 ፐርሰንት ጥሩ)

 

    “በግልፅ” ቀጠልኩና “ምን ያህል ጥሩ እንደሆንክ ወስነህ ሚዛኑ ወደ ከክፉ ወደ ጥሩ እንዲያዘነብል ማድረግ አለብህ” አልኩት፡፡ ለሩዲ እስክሪፒቶዬን ሰጠሁትና በወረቀቱ ላይ የ x በማድረግ ምን ያህል ወደ ሰማይ ለመግባት የሚያበቃ ወደ “ሙሉጥሩ” የተጠጋ ምልክት እንዲያደርግ ጠየኩት፡፡

    ሩዲ ወረቀቱ ላይ ያለውን ማጥናት ጀመረ፤ከዚያ በኃላ 60 ፐርሰንት ላይ የሚደርስ ላይ የx ምልክት አደረገ፡፡ ከዚያ በኃላ መልሶ ካጤነው በኃላ ምልክቱን 75 ፐርሰንት ላይ አደረገ፤ትንሽ ቆይቶ ማሰብ ጀመር፡፡ በመጨረሻ ራሱን አወዛወዘ፤ ከዚያም አነስተኛ የሆነች x ምልክት 70 ፐርሰንት ላይ አደረገ፡፡

    ምንም ነገር መልሶ ሳይመለከት እስክሪፒቶውን መለሰለኝ፡፡

    ምልክት ያደረገበትን ተመለከትኩኝ፡፡ “እስቲ ምልክቱን አፍንጫ ጫፍ ላይ እንደሆነ አድርገን እንውሰድ ምክንያቱም አንተ ያን ያክል መጥፎ ሰው አይደለህም፡፡ ፈጣሪህ ፊት ብትቀርብና ምልክቱ ትንሽ ወደ ቀኝ ለምሳሌ 71 ፐርሰንት ነው ቢልስ፡፡ ጥሩ ለመባል መመዘኛው 71 ፐርሰንት ቢሆንና የአንተ 70 ፐርሰንት በመሆኑ መስፈርቱን ባታሟላ ወዴት የምትሄድ ይመስልሀል?”

    አጆቹን አጣመረ፤አሁንም ወደ እኔ ሳይመለከት “ሲኦል ይሆናል ብዬ እገምታለሁ፡፡”

    “ስለዚህም የ x ምልክቷ በየትኛው ቦታ ላይ እንደምትውል ማወቅህ የሕይወትህ ዋና ጥያቄ አይሆንም ወይ?” ብዬ ጠየኩደት፡፡

    ሩዲ በሃሳቡ እያጉተመተመ ተስማማ፡፡ “ትክክል የት ቦታ ላይ እንደሚሆን እርግጠኛ አይደለሁም፡፡”

    ኖትፓዴን ዘግቼ ወደ ሀሳቤ ገባሁ ነገር ግን ፉዲ እየተንቀሳቀሰ አልነበረም፡፡ “የ x ምልክቱ የት ላይ እንደሚውል ላውቅ አልችልም?” ብሎ ጠየቀ፡፡ “ምክንያቱም ማወቅ ስለምፈልግ ነው አሁን፡፡ምንአልባት የተወሰኑ ደቂቃዎችን ወስደህ ልታሳየኝ ትችላለህ?”

    እንደዚህ ዓይነት ስሜት ከመጀመሪያውም እንደሚሰማው ጠብቄ ነበር፡፡ ወደ ጥግ የሚገኝ መቀመጫ አገኘን፤ እናም ስለ x መፅሃፍ ቅዱስ ምን እንደሚል ገለፅኩለት፡፡ ተረዳ እኔም መለስኩለት….. እናም እግዚአብሔር ለእርሱ ያስቀመጠውን ቦታ ያን ቀን በትክክል ሊረዳ ቻለ፡፡

የችግሩ ሥያሜ

የመጀመሪያዎቹ ስድስት ምዕራፎች ትኩረት ያደረጉት ለዘላለም ሕይወትህ ወሳኝ የሆነውን  የሁለተኛው ቁልፍ ላይ ነበር፤ አሁን የምትሰራው ሥራ በሰማይ ለምታገኘው ዋጋ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ፡፡ አሁን ስለመጀመሪያ ቁልፍ ማውራቱ አስፈላጊ ነው፡፡ እንደምታስታውሰው የመጀመሪያው ቁልፍ እምነት ነው፤ የምታምነው ነገር ለዘላለም የት እንደምታሳልፍ ወሳኝ የሆነ እንደሆነ፡፡

    ከሕይወትህ ጥሩ የሆነ ነገር እንድታገኝ ምን ማድረግ እንዳለበህ በሰፊው በሚያወሳ መፅሃፍ ወስጥ ስለ መጀመሪያው ቁልፍ ያወከው ትምህርት እንድትወደው ያደርግሃል፡፡ የኢየሱስ አስተምርሆ የምናምነው ነገር የሚሰራው በእኛ የምንሰራው ስራ ሲያቆም እንደሆነ ነው፤ ይህም ለአንድ ወሳኝ ምክንያት ነው፡-

              አንድ ሠው የአንተን ሥራ ሠርቷል!

    አንድ ሰው ወይም የሆነ ነገር በሩዲ አእምሮ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው ወደ ሠማይ ለመግባት እርሱ በሚሰራው ጥሩ ስራ መሆኑን አምኖ ለዚህም ይህንን ችግር ለመፍታት ከባድ ስለሆነበት ነው፡፡ አዋቂ ናቸው የሚባሉ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሠዎችም ተመሳሳይ የሆነ አስተሳሰብ አላቸው፡፡ ኢየሱስ እንደተናገረው ከሆነ ግን ሩዲ እና በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ሠዎች መፈታት ያለበትን ችግር ትክክለኛ ቁልፍ ባለሆነ ቁለፍ ለመፍታት የሚሞክሩ ናቸው፡፡

    ምን ለማለት እንደፈለኩኝ ላስረዳህ፡፡

    በእግዚአብሔር ፊት ለመቆም ሩዲ ያልተማመነ እንደሆነ ተገንዘብ፤ምክንያቱም እርሱ ራሱ ብቁ እንዳልሆነ ስለሚያውቅ ነው፡፡ ችግር አለበት፤እናም የእርሱ ችግር የሆነው ይህንን ችግር ለመፍታት በራሱ ጥሩ የሆነ ስራ ለመፍታት በመሞከሩ ነው፡፡ የችግሩ ስያሜ ሐጢያት ይባላል፡፡ እያንዳንዱ በራሱ ተደጋጋሚ ሐጢያት የፈጸሙ መሆናቸውን ያውቃሉ፡፡

   ጳውሎስ ይህንን ግንዛቤ በውስጣችን እንዲኖር የሚያደርገው አግዚአብሔር እንደሆነ ፅፏል፡፡

     “እውነትን በዓመፃ በሚከለክሉ ሰዎች በኃጢአተኝነታቸውና በዓመፃቸው

     ሁሉ ላይ የእግዚአብሔር ቁጣ ከሰማይ ይገለጣልና፡፡ እግዚአብሔር

    ስለ ገለጣቸው ስለ እግዚአብሔር ሊታወቅ የሚቻለው በእነርሱ ዘንድ ግልጥ ነውና፡፡”         

                                                      ሮሜ 1፡18-19

 

    ከዚህም በላይ እግዚአብሔር አልሆዎቱን የገለፀ በመሆኑና ጳውሎስ እንደገለፀው እኛ ሐጢያት እንዳለብን ያሳወቀን በመሆኑ ምንም ማምለጫ እንዳይኖረን አስቀርቶናል፡-

           “የማይታየው ባህሪ እርሱም የዘላለም ሃይሉ ደግሞም አምላክነቱ

           ከዓለም ፍጥረት ጀምሮ ከተሰሩት ታውቆ ግልጥ ሆኖ ይታያልና፤

           ስለዚህም እግዚአብሔርን እያወቀ እንደ እግዚአብሔርነቱ መጠን

           ስላላከበሩትና ስላላመሰገኑት የሚያመካኙት አጡ፤”

                                                      ቁጥር 20-21

   ይህ ጥቅስ  በዓለም ያሉ ሐይማኖቶች ለመፍታት ጥረት የሚያድጉትን የሰው ልጅ ትክክለኛ የሆነውን ችግር ጠቅልሎ የያዘ ነው፤ የእግዚአብሔር ፍርድ የሚጠብቀን እንደሆነ የምናውቅ ከሆነ ከእርሱ ጋር ለመታረቅ እንድንድችል ታዲያ ምን ልናደርግ ይገባናል፤ ከሐጢያት መዘዝ ለመዳንስ ምን ማድረግ ይኖርብናል?

    አንዳንድ ሐይማኖቶች በመንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ያለውን ነገር ለሞሙላት በማሰብ የእንስሳ መስዋት ወይም ለጠንቋይ ገንዘብ መክፈል እና የመሳሰሉትን ተግባራትን ያከናውናሉ፡፡ እንዳንድ ሐይማኖቶች አሁን መከራን በመታገስ ሐጢያትን ሰው ራሱ ሊዋጅ እንደሚችል ያስተምራሉ፤ ለምሳሌ በጉልበታቸው ብዙ ርቀቶችን መሄዳቸው ወይም ራሳቻውን ይመታሉ፤ለዚህም ምክንያቱም በኃላ ስቃይ አይገጥማቸውም ብለው ስለሚያምኑ፡፡ አንዳንድ ሐይማኖቶች ደግሞ አንድ ሰው ለሰራው ጥፋት ብዙ መልካም ነገሮችን በመስራት ሊያካክሰው ይችላል ብለው ያስተምራሉ፡፡ ይህኛው የሩዲ ሃይማኖት ነው፡፡

    የዓለም ችግር ለሆነው ለሐጢያት መፍትሔ ለመስጠት እነዚህ ሁሉም አስተምርሆዎች መፍትሔ አይሆኑም፡፡ ለምን? ለዚህ ምክንያቱ እነዚህ አስተምርሆዎች በእኛ መልካም ስራ ላይ ስለሚመረኮዙ እና ከደቂቃ በኃላ እንደምንመለከተው የእኛ ሐጢያት የሚያስከትለው መዘዝ በጣም ከፍተኛ በመሆኑ ምንም ያክል ጥሩ ስራ ብንስራ ሊያድነን የሚችል አይደለም፡፡

     ኢየሱስ በመጀመሪያ በሐጢያት በኩል ያለው ችግር ከተወገደ በኃላ እና የእኛ መዳረሻ ሰማይ መሆኑን ካወቅን ለእግዚአብሔር ብለን በምድር የምንሰራው ስራ በዘላለም ሕይወታችን የሚጠቅመን እንደሆነ አስተምሯል፡፡ ይህ ሁኔታ ደግሞ አንገብጋቢ የሆነ ጥያቄ እንድናነሳ ይጋብዘናል፤ወደ ሰማይ የማትገባ እንደሆነ ካወክና የአንተ መጨረሻ ሲኦል ከሆነ አሁን በምድር ላይ የምንሰራው መልካም ነገር ምን ዓይነት ርባና ይኖረዋል?

    ምንም እንኳን መልካም የሆኑ ሥራዎችን መስራት ወደ ሰማይ ለመግባት የማያበቃን ቢሆንም በዚህ ሁኔታዎችም ውስጥ ጠቀሜታ አላቸው፡፡

ሲኦል በደረጃ ሲታይ

 

በጎረቤት ያለው ካለምንም እምነት ዝም ብሎ በደመነፍስ መልካም የሚሰራ ነገር ግን በኢየሱስ የማያምን እንደ ሂትለር ካሉ ክፉ ሠዎች ተመሳሳይ የሆነ የሲኦል ቅጣት ይገጥማቸዋል ብለህ ታምናለህ? በውስጠኛው ያለው መንፈስህ ይህ ፍትሃዊ እንዳልሆነ ይመሰክርልሃል፡፡

    ለዚህም ምክንያቱ ይህ መሆን ስለሌለበት ነው፡፡

    የማይቋረጥ ግንኑነት ማለትም በምድር የምትሰራው ማናቸውም ሥራዎች በዘላለም ሕይወትህ ላይ የሚያበረክት ከሆነና ይህም በሁሉም ሠዎች ላይ በእኩልነት ተፈፃሚ የሚሆን ከሆነ ይህ ሁኔታ መዳረሻህ ሰማይም ቢሆን ሲኦል ተፈፃሚነት ይኖረዋል፡፡

    በእርግጥ ኢየሱስ በሰማይ የተለያዩ ደረጃ ያላቸው ሽልማት መኖራቸውን ካራጋገጠ ፍትሃዊ የሆነው እግዚአብሔር አማኝ ያልሆኑ ሠዎችን በተመሳሳይ ሁኔታ መዳኘቱ ወይም ተመሳሳይ መስጠቱ ትርጉም የሚሰጠው ይመስልሃል?

    ኢየሱስም ይህንን ጉዳይ ነው የተናገረው፡፡ በልዩ ሁኔታ ኢየሱስ በምድር ላይ በምን ሁኔታ ላይ እንደኖረ ተመዝኖ በሲኦል የሚኖረው የሲቃይ መጠን የሚጨምርበት ሁኔታ እንደሚኖር ገልጿል፡፡ ይህንን እውነታ ልናገኝ የምንችለው ኢየሱስ ካወገዘው ነገር ላይ በመነሳት ነው፡-

    “አንቺም ቅፍርናሆም እስከ ሰማይ ከፍ አልሽን? ወደ ሲኦል ትወርጂያለሽ፤

    በአንቺ የተደረገው ታምራት በሰዶም ተደርጎ ቢሆን እሰከ ዛሬ በኖረች ነበርና፡፡

    ነገር ግን እላችኃለሁ፤በፍርድ ቀን ከአንቺ ይልቅ በሰዶም አገር ይቀልላታል፡፡ “

                                                      ማቴዎስ 11፡23-24

 

    “ይቀልላታል” የሚለው ቃል ላይ ትኩረት ስጥበት፡፡ የዚህ ቃል በሲኦል የሚኖረው ፍርድና ቅጣት የተለያዩ ደረጃዎች እንዳሉዋቸው የሚያመለክት ነው፡፡

    በሌላ ሁኔታ ደግሞ ኢየሱስ ፈሪሳዊያን ያላቸውን ሥልጣን መበለቶችን በመጉዳታቸውና ሐሰት የሆነ ረዥም ጸሎት ማድረጋቸው “ትልቅ የሆነ ኩነኔ እንደሚገጥማቸው” ተናግሯል፡፡(ማቴዎስ 23፡14)  ሐዋሪያው ጳውሎስም በተመሳሳይ አንዳንዶቹ “በቁጣ ቀን ቁጣን /በራሳቸው/ ላይ እንደሚያከማቹ፡፡” ጽፏል፡፡ ሐዋሪያው ዮሐንስ አማኝ ያልሆኑ ፍርድ እንደሚጠብቃቸው ሲናገር “እያንዳንዱም እንደ ሥራቸው መጠን ተከፈላቸው፡፡”  ብሏል፡፡ (ዮሐንስ ራዕይ 20፡13)

    ግራ አንጋባ፤ልክ የምትሰራው የክፋት ስራ (ሐጢያት) በሰማይ ያለህን ደስታ እንደማይቀንሰው ሁሉ የምትሰራው ጥሩ ሥራ በሲኦል የሚኖርህን የቁጣ መጠን አይቀንሰውም፡፡ ይህንን ጉዳይ በደንብ እንድትረዳውና እውነታውን በውል እንድትገነዘብ የሚያስችል ስለ ካሳ መጠን እንደሚከተለው ነው፡-

         ሠማይ ወደአልተሻለ ደረጃ አትዘልቅም፣ ወደ ተሻለ ነገር ብቻ እንጂ፤

         ሲኦል ወደተሻለ ደረጃ አትዘልቅም፤ወደ አልተሻለ ነገር ብቻ እንጂ

   

    ትክክለኛውን ቁልፍ አንስተህ ወደ ሰማይ ሊያመራህ የሚችለውን በር መክፈት ትክክለኛ ጊዜ እንደሆነ አታስብም? አሁን ለሩዲ የነገርኩትን ለአንተ የምነግርበት ጊዜ ነው፡፡

 

የምንሰራቸው ሥራዎች ለምን አይሰሩም

 

ሩዲ X የትኛው ሥፍራ ላይ ልትሆን እንደሚገባት ለመማር ዝግጁ ነበር፡፡ ወደ “100 ፐርሰንት ጥሩ ሥራ” ቦታ ላይ ማረፍ እንዳለበት ካሳየሁት በኃላ ቀጥዬ “መፅሃፍ ቅዱስ X የትኛው ቦታ ላይ ማረፍ እንዳለበት በዚህ ሁኔታ ነው የሚገልፀው” አልኩት፡፡

    “ይህ ግን የማይቻል ነው!” ሩዲ መለሰልኝ፡፡ “ማንም ሰው ወደ ሰማይ ሊገባ አይችልም፡፡” በማለት፡፡

    “ስለዚህም ማንም ሰው 100 ፐርሰንት ሊሆን እንደማይችልና የሐጢያትን ችግር በራሱ ሊፈታው እንደማይችል ተስማምተሀል ማለት ነው?”

    “አዎ፤ ይመስለኛል፡፡”

    “አንድም ብትሆንም ለሐጢያት የሚኖረው ቅጣት ሞት ነው ብልህ ምን ትላለህ?”

    “መልካም፤ እንዲህ ከሆነማ ፍትሃዊ አይሆንም” ብሎ ነገረኝ፡፡ “ማንም ሰው ፍፁም አይደለም፡፡ ሁሉም ሐጢያትን አድርገዋል፤ ግን ቅጣቱ አሁንም ሞት ነው?”

    ሩዲ አመንክኖአዊ የሆነ ነገር እየተናገረ እንሆነ አረጋገጥኩለት፡፡ ከዚያም መፅሃፍ ቅዱሴን ከፍትኩኝ፤ አዳምና ሔዋን በገነት ውስጥ ሐጢያት ከሰሩ አንስቶ አካላዊ እና መንፈሳዊ ሞት የሚያስከትለው ውጤት እንደሆነ ገለጽኩለት፡፡ በኦሪት ዘፍጥረት ላይ እንዲህ እናነባለን፤”ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ከእርሰ በበላህ ቀን ሞተን ትሞታለህና፡፡” (ኦሪት ዘፍጥረት 2፡17) እናም በአዲሱ ኪዳንም ይህ ችግር አሁንም ዘልቆ እንዳለ ተገነዘበ፤”የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነውና፤”

    “በዚህ ሁኔታ አስብ፤” ብዬ ቀጠልኩኝ፤ “በዳኛ ፊት  ሆኜ ብዙ የሕብረተሰብ አገልግሎት እንደምሰጥ ቃል ገባሁኝ ልበል” “ይህ አግባብነት ያለው ይመስልሃል?”

    “በእርግጥ ትክክል አይደለም” ብሎ ሩዲ መለሰልኝ፡፡ ከደቂቃ በኃላ ቆየና “ስለዚህ ምንም ዓይነት መፍትሔ የለም ማለት ነው? ተስፋም የለም ማለት ነው”

    “በትክክል” አልኩት “ምንም ዓይነት ተስፋ የለም፡፡” ከመቀጠሌ በፊት ትንሽ ቆየሁና “አንተን የሚተካ ነገር ከሌለ በስተቀር፡፡ አንተን የሚተካ ቢገኝስ፤እግዚአብሔር በአንተ ላይ ሊፈርድ ሲል በአንተ ምትክ ሆኖ ሊቆም የሚችል ሰው ቢገኝሳ?”

    “ያ ሊኖር የሚችል ቢኖርማ በጣም ጥሩ ነበር” ብሎ መለሰልኝ፡፡ “ነገር ግን 100 ፐርሰንት ጥሩ የሆነ ሰው ሊሆን ይገባል፤ እደዚህ ሊሆን የሚችል ሰው ደግሞ የለም፤ አይደል?”

    “በትክክል ከኢየሱስ በቀር ማንም የለም፤”፡፡ ከዚያም ለሩዲ ቀጠል አደረኩኝና ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ እና እርሱ ብቻ በምድር ላይ ሐጢያት እንዳልሰራ መፅሃፍ ቅዱስ እንደሚናገር ገለፅኩለት፡፡ በእርግጥ አግዚአብሔር ልጁን ወደ ምድር ሲልከው በሩዲ ፋንታ ሆኖ እንዲሞትና የሐጢያቱን ቅጣት ለመክፈል ነው፤ ለአንዴና ለመጨረሻ የዓለምን ሐጢያትንም ጨምሮ፡፡

    ከዚያ በኃላ የማስታወሻ ኖት ፓዴን እንደገና አወጣሁኝ፡፡ ሩዲ ያስቀመጠውን X ምልክት አመላከትኩት፡፡”አሁን ምርጫ ልትመርጥ ትችላለህ ሩዲ”

     “እሺ” አለ፡፡

    እርሱ ወዳሳረፈው X ምልክት ጠቀስኩኝ፡፡”አንተ በምትሰራው ጥሩ ሥራ ልትተማመን ትችላለህ፤ እናም X ባደረከው ምልክት ትክክል እንደሆንክ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ አሊያም በኢየሱስ ክርስቶስ ልታምን ትችላለህ፤ በአንተም ምትክም እንደሞተልህ፡፡”

    መፅሃፍ ቅዱሴን ከፈትኩኝና በፊታችን ላለው ምርጫ ኢየሱስ እንዴት እንደአብራራው አነበብኩለት፡

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ

እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና፡፡

ዓለም በልጁ እንዲድን ነው እንጂ በዓለም እንዲፈርድ እግዚአብሔር

ወደ ዓለም አልላከውምና፡፡”

            ዮሐንስ 3፡16-17

 

    ወዳጄ ይህም ለአንተ ምርጫ ነው፡፡ ይሀን የመፅሃፍ ቅዱስ ክፍል አንብበህ ከሆነና ሰማይ የአንተ መዳረሻህ እንደሆነ እርግጠኛ ካልሆንክ ኢየሱስ በተናገረው ነገር ላይ ተመስርቼ በእርሱ ላይ እምነትህን እንድትጥል አበረታታሃለሁ፡፡ በእርሱ ላይ ያለህን ሙሉ እምነት መጣል ከፈለክ ሩዲ እንደፀለየው ለምን አሁን አትፀልይም፡-

 

የተከበርከው አምላኬ ሆይ ለሰራሁት ሐጢያት ይቅርታ እጠይቃለሁ፤እና የሐጢያቴን ችግር እኔው ልፈታው እንደማልችል ተረድቻለሁ፡፡ እናም የአንተን ሞት ለሐጢያቴ ሙሉ ክፍያ እንደተከፈለ አድርጌ እቀበላለሁ፤ ኢየሱስንም እንደ አዳኜ አድርጌ እቀበላለሁ፡፡ ኢየሱስ ሆይ፤አንተን ለማገልገል ከአሁን በኃላ ወስኛለሁ! በአንተ ስም አሜን

 

    ይህ ፀሎት እግዚአብሔር ሁልጊዜ የሚመልሰው ፀሎት ነው፤ለመስማትም የሚፈልገው ነው፡፡

መዳረሻ ሠማይ

ለደህንነትህ እምነትህን በኢየሱስ ላይ ሙሉ በሙሉ ካደረክ የአንተ ዘላለማዊ መዳረሻህ ተቀይሯል፤ ከሲኦል ወደ ሰማይ!

    አሁን በኢየሱስ አዲስ ፍጥረት ነህ፡፡ (2 ቆሮንጦስ 5፡17) አሁን ዘላለማዊ ሕይወት አለህ፡፡ (የሐንስ 3፡16-17) አሁን የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤በደህንነትህ የተነሳ ወራሹም ነህ፡፡ (ገላቲያ 4፡7)

    ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አንተ በምትሰራው መልካም ስራ የደህንነትህን ስራ ከቶ ሊለውጥ እንደማይችል ተስፋ የለህም፡፡ ምክንያቱም ልክ እንደ ሌሎች የኢየሱስ ተከታዮች ከዚህ በታች የተመለከተውን ጥቅስ እንደሚረዱት አሁን የምትረዳ በመሆኑ፡-

 

      “ጸጋው በእምነት አድኖአችኃልና፤ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ

      ከእናንተ አይደለም፡፡ ማንም እንዳይመካ ከስራ አይደለም፡፡”

                                                      ኤፌሶን 2፡8-9

 

    በዚህ ፀጋ ምክንያት ሐጢያት የሚያስከትለው አሉታዊ ወጤት ለዘላለም አያገኝህም፤ ምክንያቱም ኢየሱስ በራሱ የወሰዳቸው በመሆኑ፡፡

    ከዚህ ይልቅ በሠፊህ ልቦናህ ሆነህ ለእግዚአብሔር ያለህን ፍቅርህን ልተገልፅ ይገባል፤ለእርሱም ለምትሰራቸውም ሥራዎች ለዘላለም ሽልማትም እንደሚሰጥህ ግንዛቤ እየወሰድክ፡፡

    ይህንን ጥቅስ እስኪ ተመልከት፡-

    እኛ ፍጥረቱ ነንና፤ እንመላለስበት ዘንድ እግዚአብሔር አስቀድሞ ያዘጋጀውን

    መልካሙን ስራ ለማድረግ በክርስቶስ ኢየሱስ ተፈጠርን፡፡

                                                      ቁጥር 10

 

    ወዳጄ ሆይ፤ መልካሙን እንድትሰራ ተፈጥረሃል፤ድነሃልም!

    እናም እምነትህን በኢየሱስ ላይ ካደረክ ለመጀመሪያ ጊዜ በሕይወትህ እግዚአብሔርን የሚሸልመውን ሕይወት ትኖራለህ፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 


8

                  <b style="mso-bidi-font-weight:normal">ለዘላለም ወደ ሆነው ነገር መመልከት</b>

 

         “እነሆ፤ በቶሎ እመጣለሁ፡፡ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው

         መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ፡፡”

                                           ኢየሱስ በራዕይ 22፡12

 

ላርምህ በነገው ጠዋቱ ሲጮህ ለዘላለም የሚገጥምህ ነገር ምን እንደሆነ አትመለከትም፡፡ የአይን መነፅርህን ታጠልቃለህ፤ በችኮላ መንፈስ ኮሌታህን ታስተካክላለህ፡፡ ቤተሰብህን አዳራቸውን ትጠይቃለህ፤ጥሩ የሆነ ቡና ወይም ሻይ ትጠጣለህ፤በቀን ለምታሳልፈው ስራ ትወጣለህ…. እናም በሕይወትህ የመጀመሪያውን ምርጫ ታደርጋለህ፡፡

    ለማየው ነገር መኖር አለብኝ፤ወዲያውኑ የሚጠፋ መሆኑን እያወኩኝ? ወይስ ለዘላለም ሕይወት ብዬ መኖር አለብኝ?

    ይህ መፅሃፍ ከጥርጣሬ በሆነ ሁኔታ ኢየሱስ እንድታውቀው የሚፈልገውን ነገር አሳይቶ ትክክለኛ ምርጫ እንዲኖርህ ጥረት አድርጓል፡፡

    ምንም ዓይነት ከፍተኛ የሆነ ጥረት አድርገህ አሳልፈህ ለመመልከት ብትሞክር ወደፊት በሰማይ ሊኖር ስለሚችለው እውነታ ከዚህ በላይ የሆነ ማረጋገጫ አታገኝም፡፡ ለምን? “የማይታየውን እንጂ የሚታየውን ብንመለከት፤ ቀላል የሆነ የጊዜው መከራችን የክብርን የዘላለም ብዛት ከሁሉ መጠን ይልቅ ያደርግልናልና” ብሎ ጳውሎስ ጽፏል፡፡ (2 ቆሮንጦስ 4፡18)

    ምድራችን ጊዜያዊ ልትሆን ትችላለች ግን በእርግጥ እንደሆነች አሳማኝ አይደለም ወይ? ያለ እምነት ትክክለኛ የሆነ መዳረሻችን መመልከትም ብቻ ሳይሆን ማሰብም አንችልም፡፡

    የሚሲኦናሪ ተመራቂ የሆኑት ብሪታናዊ ጥንዶች ሕይወታቸውን ሙሉ ከህይወት ጥግ ላይ ሆነው ያገለገሉት ያላቸውን የሕይወት ታሪክ የምረሳው አይደለም፡፡ ምዕተ ዓመቱ ተቀየረ፡፡ ከአርባ ዓመታት በኃላ ለደጋፊዎቻቸው ወደ ቤታቸው ለመመለስ እንደተዘጋጁና ጉዞዋቸውንም ወደ ኢንግላንድ ያደረጉ መሆናውን ገለፁላቸው፡፡

    ከብዙ አስርተ ዓመታት በኃላ አይኖቻቸውን ዳርቻውን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲመለከቱ ሰውየውን ባለቤቱን እንደዚህ ብሎ ተናገራት “እዚህ እንኴን ደህና መጣችሁ ብሎ የሚቀበለን ሰው የምናገኝ ከሆነ እድነቃለሁ፡፡” አላት፡፡


 

    መርከቢቱ ወደ ፕላይማውዝ ዳርቻ እየተጓዘች ባለበት ጊዜ ጥንዶቹ በመርከቢቱ የውጪያኛው ክፍል ላይ እጃቸውን ተያይዘው ቆሙ፡፡ ከዚያ በኃላ ለራሳቸው ትንግርት እስከሚሆንባቸውና እስከሚደሰቱ ድረስ በርከት ያሉ ሰዎች በዳርቻው ጫፍ ላይ ወደ እነርሱ እየተመለከተ ይደሰቱ ነበር፡፡ ሁሉም ፈንጠዙ፡፡ ሠዎች እንደዚህ ተብሎ የሚነበብ ሠነደቅ ሰቀሉ “እንኳን ወደ ቤታችሁ በሠላም ተመለሳችሁ! በእናንተ እንኮራባችኃለን!”

    ባልየው ልዩ የሆነ ስሜት ተሰማው፡፡ “ይህ የሚያስደንቅ አይደለም!” ባለቤቱ በደስታ እየሳቀች፤ ከዚያ በኃላ ሻንጣዎቻቸውን ይዘው መውጣት እንዳለባቸው ወሰኑ፡፡

    ነገር ግን ከጀልባው ወደ መሬት ወደሚያስወስው መንገድ እንደደረሱ ልባቸው በድንጋጤ መምታት ጀመር፤እነርሱን ወደዚያ አደረጓቸው፡፡ የተሰበሰበው ሰው መበታተን ጀመር፡፡ ወዲያውኑ እየሆነ ያለው ነገር ምን እንደሆነ ግልፅ ሆነላቸው፡፡ እነዚህ ብዙ ሠዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ያሉት ለእነርሱ አልነበረም ነገር ግን አንድ የፖለቲካ ሰው በውጪ ባስገኘው ስኬት የተነሳ አቀባበል ለማድረግ ነው፡፡

    ባልየው የተሰማውን ቅሬታ ሊደብቅ አልቻለም፡፡ ”ሕይወትን ሙሉ እስከመስጠት ድረስ የተደረገ አገልግሎት በኃላ እቤት እንኳን ደህና መጣችሁ ብሎ ሊቀበለን የሚችል ማንም አላገኘንም፡፡”

    ባለቤቱ እጁን ያዘችና “የኔ ውድ ና እንሂድ” በለሰለሰ ድምጽ አለችው፡፡ “ይህ ኢንግላንድ ነው፡፡ እስካሁን ድረስ እቤት አይደለንም፡፡” አለችው፡፡

 

የመታሰቢያ መጽሃፍ

 አብዛኛዎቹ የኢየሱስ ተከታዮች ልባቸውን በመስጠት ለእግዚአብሔር አገልግሎታቸውን እንዳያውሉ የሚያግዳቸው ለሚያገለግሉት አገልግሎት በሚታይ ነገር ላይ አገኛለሁ ብለው ስለሚያስቡ ነው ብለህ አታስብም? እኛ ላናምን አንችላለን ነገር ግን ጥሩ የሆነ ምርጫ በመምረጣችን አፋጣኝ የሆነ ውጤት ያስገኝልናል ብለን እናስባለን፤ አንድም የሆነ ነገር የማናገኝ ከሆነ በዘላለማዊ ሕይወታችን ምንም ዓይነት ነገር እንደማይከሰት አድርገን እንደመድማለን፡፡

    በሚድዌስት  ለብዙ ጊዜ ከሕብረተሰቡ ተለይተው የፀሎት ጊዜ ያላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ የክርስቲያን ሠራተኞች በጊዜያዊ ጉዳይ ላይ ለተወሰነ ጊዜ የታወሩትን አስታውሳለሁ፡፡ በነበረን የሁለተኛው ቀን የአብሮ ጊዜ የነበራቸው የተስፋ መቁረጥ ሰሜት በግልፅ ይነበብባቸው ነበር፡፡ “ስንቶቻችሁ ናችሁ ምንም እንኳን እግዚአብሔርን የምትወዱ ብትሆኑም አሁን አገልግሎታችሁን ለማቆም የምትፈልጉ? ለአገልግሎታችሁ ለምታውሉት ነገር ዋጋ አያስፈልገውም ብላችሁ አታስቡም?”

    ከግማሽ በላይ የሆኑት እጃቸውን አወጡ፡፡

    ሁላችንም የመጨረሻውን የብሉይ ኪዳን መፅሃፍ ቅዱስ ገፅ ከፈትን፡፡ በዚያ ቦታ ለእግዚአብሔር መኖር የሚፈልጉ ነገር ግን ጥቅማቸውን ያልተመለከቱ ሌላ የእግዚአብሔር አገልጋዮች አገኘን፡፡ በእርግጥ እነርሱም በሚያዩት የተነሳ እግዚአብሔርን ለማገልገል የወሰኑ ቢሆንም ያዩት ግን እነዚያ ካዩት የተለየ ነበር (ሚልክያ 3፡15) እነርሱም የተናገሩት እንደዚህ ነው፡-

     “እናንተም፤ እግዚአብሔርን ማገልገል ክንቱ ነው፤ትእዛዙንስ በመጠበቅ በሠራዊት ጌታ    

     በእግዚአብሔር ፊት ኀዘንተኞች ሆነን በመሄድ ምን ይረባናል?”    

                                                      ቁጥር 14

   

    እግዚአብሔር ለእንደዚህ ዓይነት እውነተኛ ለሆነ ጥያቄ እግዚአብሔር በምን ዓይነት ሁኔታ እንደሚመልስ ለማወቅ ፈለግ? የሚከተለው በመፅሃፍ ቅዱስ ውስጥ ልብን የሚነካ ነገር ነው፡፡ እግዚአብሔር ይሰማል፡፡ባለው ሁኔታ ውስጥ የተያዙ ወንድና ሴቶች እንደሆኑ ይረዳል፤በቀላሉ የማየት አቅማቸውን ያጡት፤እግዚአብሔር ይመለከታል ብለው ተስፋ የቆረጡት፡፡ መፅሃፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፡-

 

“የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን የሚፈሩ እርስ በርሳቸው ተነጋገሩ፤እግዚአብሔርም አደመጠ፤ሰማም፤እግዚአብሔርን ለሚፈሩ ስሙንም ለሚያስቡ የመታሰቢያ መፅሃፍ በፊቱ ተፃፈ፡፡”

ቁጥር 16

 

    እግዚአብሔር የመታሰቢያ መፅሀፍ የሚፅፈው ለምንድን ነው? እንደሚያይ እና እንደሚጠነቀቅ ለሕዝቡ ለማስረገጥ የሚፈልግ በመሆኑ ነው፡፡ የእያንዳንዱን ዝርዝር ሁኔታ በተመለከተ ወደፊት ባለ ቀን የሚገልፀው ይሆናል፡፡ ይህንን አንብብ፡-

       “እኔ በምሰራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ…….

          ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ፡፡”

                                                      ከቁጥር 17-18

    የእግዚአብሔር ፍቅር ፤ፍትሀዊነቱ ምን ዓይነት ትልቅ ነው! አሁን ማናቸውም ዓይነት ነገር ቢኖሩም ወደፊት አንድ ቀን ግን የመታሰቢያ መፅሃፉን ይከፍታል፤ የቸር አድርጊነቱ፣ የታማኝነቱና ፍትሃዊነቱ ስለመሆኑ እውነቱ ይታወቃል፡፡ በአርሱ ስም የተከናወነ የአገልግሎት ሥራዎች አትዘነጋም፤ከሸልማትም አታልፍም፡፡

    ለምሽግ ፀሎት የነበሩ ሠዎች እውነቱን ሲረዱ ተስፋ ቢስነታቸው ከውስጣቸው ተወገደ፡፡ አንዳንዶቹ ንጉሳቸውን እንዴት ዝቅ አድርገው እንዳዩ ሲረዱ እንባቸውን አፈሰሱ፡፡ አብዛኛዎቹ እርሱን ለማገልገል ራሳቸውን አነሳሱ፡፡ አንድ ቀን ራሱ ነገሮችን ሁሉ በታምራት ትክክል እንደሚያደርግ እስተከተናገረ ድረስ እንዴት ራሳቸውን ለእግዚአብሔር አገልግሎት አናነሳሳም?

    ይህንን ክፍል ከማጠናቀቃችን በፊት ከመፅሃፍ ቅዱስ በዚያች ቀን ምን ሊሆን እንደሚችል አካፈልኳቸው፡፡ አሁን ደግሞ ለአንተ ላሳይ ነው፡፡

በመጨረሻው ገፅ ያለው ኢየሱስ

አንተ ወላጅ ከሆንክ ልጅህ አንድ ነገር ፈልጎ ፊቱ ሲጡቁር ነገር ግን ይህንን ፍላጎቱን ለማምጣት የምትችልበት አቅም እንዳለህ ስትረዳ በቀጣይ ምን ማድረግ አለብኝ የሚለውን ስትረዳ  ምን ዓይነት ስሜት እንደሚሰማ ልታውቅ ትችላለህ!

   ኢየሱስም አሁንም የሚሰማው ስሜት ልክ እንደዚህ ነው፡፡

    በብሉይ ኪዳን መጨረሻ ላይ ያለው በአዲስ ኪዳን መጨረሻ ላይ እንደተደገመ ልትገነዘብ ይገባል፡፡ የራዕይ የመጨረሻ መጽሃፍ ገልጠህ ከተመለከትክ ልታነበው ትችላለህ፡፡ የመጨረሻው ኢየሱስ የገባው ቃል ኪዳን እንደሆነ ልትገነዘብ ትችላለህ፡-

    “እነሆ በቶሎ እመጣለሁ፤ ለእያንዳንዱም እንደየስራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ  

    ጋር አለ”

                                            ራዕይ 22፡12

 

    ኢየሱስ “ በቶሎ መጥቼ መንግስቴን እመሰርታለሁ” ብሎ ባለመናገሩ ይገርመኛል፡፡ እርሱ በመንግስቱ ውስጥ ያሉ ሠዎች ከመቼም በላይ እንደሚጠነቀቅላቸው ልትረዳ ይገባል፤ምክንያቱም  እርሱን አምነውታል፤ እርሱን ለማስደሰት የቆሙ ናቸው፤ለእርሱ ደግሞ ታማኞች ናቸው፡፡

    አምላክህን በአዲስ ብርሃን ውስጥ ተመልክተኸዋልን? እርሱ የአንተን ጥረት የሚጠነቀቅ እና የሚረዳ ነው አምላክ ነው፤ምንም እንኳን እርሱን ከማገልገል አንፃር ትንሽ የምትመስል ብትሆንም፡፡ ወደ ላይ አሻቅቦ የሚመለከተውን ፊትህን ይመለከተዋል፤ልብህን ያውቀዋል፤እና ስለታማኝነትህ ግድ የለዋል፡፡

    ሊሸልምህ ቃል ገብቶልሃል…..ይህንንም ለማድረግም አይጠብቅም!

 

“በጎ አደረክ” ወደ ሚል ሕይወት ማምራት

ዳርሊን ማሬ እና እኔ እግዚአብሔር የዘላለም ሽልማት እንደሚሰጥና ለዚያች ቀን መኖር እንዳለብን የወሰንበት ቀን አስታውሳለሁ፡፡ ወዲያውኑ የምናከናውነው ድርጊቶች ቅድሚያ መስጠት ያለብን ጉዳዮች ተቀየረ፡፡ ቤተሰቦቻችን በቅደም ተከተል እንዴት ገንዘቦቻቸውን፣ ጊዜዎቻቸውን እና አቅማቸውን መጠቀም እንዳለባቸው ወሰንን፡፡ ያልጨረስናቸው ሥራዎችን እንዴት መስራት እንደሚኖርብን አዲስ የሆነ የውስጥ መነሳሳት ፈጠረብን፡፡ በእግዚአብሔር ምህረትና ቸርነት ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ መላ ውስጣችንን ሞላው፡፡

    “በጎ አደረክ” የሚል ቃል ከሸላሚው እንድናገኘ እለት እለት መኖር ጀመርን፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ስለ ዘላለማዊ ሕይወትና አሽቀንጥረው የሚመለከቱና እግዚአብሔርን ለማስደሰት በትልቅ ተልዕኮ ውስጥ ያሉ በመቶዎቹ የሚቆጠሩ ሌሎች ወንድ እና ሴቶችን አገኘን፡፡

    እነርሱ ስራውን የሚሰሩ ነገር ግን እንደነገሩን በምንም ነገር “ሀብት” የሌላቸው፤ ለጫማቸው እንኳን የሚበቃ ጥሪት የሌላቸው ናቸው፡፡ በአዲስ ፊት ለእግዚአብሔር ብለው ጉዞዋቸውን የሚመለከቱ ተማሪዎች ናቸው፤ የእያንዳንዱን የሕይወት ችግሮችንና ቀላል የሚመስሉ ሥራዎችን ለመጋፈጥ፡፡ ትልቁን ንጉሱን በመሰጠት የሚያገለግሉ ውጣች እናቶች ናቸው፤ትንንሽ የሆኑትን በትምህርት ማቋያ ማስተኛትና ከእነርሱ ጋር መሆን የህይወታቸው አገልግሎት መሆኑን እየተገነዘቡ፡፡

    የተቀደሰውን ጉዞ የሚያደርጉት በአንድ ቦታ ላይ ያሉ ሌሎች ሰዎች ይመስላሉ፤ነገር ግን በየቀኑ የሚሠሩ ሥራዎችን በተለየ አመለካከት የሚያዩ ናቸው፡፡ ሠው በመሆናችን በመደበኛው በምናከናውናቸው ተግባራት ውስጥ እያንዳንዱ ቀን ዘላለማዊ ሥራ ምን እንደሆነ ለማግኘት የሚያስችል እድል ተደርጎ የሚወሰድ ነው፡፡ በእርግጥ እነርሱ በነጥብ ላይ ሆነው ነው የሚኖሩ ቢሆኑም ኑሮዋቸው ግን ለመስመሩ ነው፡፡ በኒው ደሊሂ፣ በማንሽተር፣ በሌጎስ፣ በቢሎሲ…. መንገዶች ለእግዚአብሔር የተለየ የሚያደርጉ ናቸው፡፡

    ግን እነርሱም ከመጀመሪያውም የሰማይ ዜጎች ናቸው፡፡

 

 

 

 

የአድራሻ ለውጥ

ወዳጄ፤ከዚህ መፅሃፍ ከመውጣትህ በፊት ሕይወትን ሊለውጥ የሚችል ውሳኔ ልትወስን ይገባል፡፡

ዜግነትህን ከምድር ወደ ሰማይ ልትቀይር ይገባል፡፡

    ኢየሱስ ደቀ መዝሙርትን ትቶቷቸው ሊሄድ በዝግጅት ባለበት ጊዜ ስለዚያ ቦታ ተናገራቸው፡፡ የሚናገረውን ቃላቶቹን አድምጥ፡-

         “በአባቴ ቤት ብዙ መኖሪያ አለ፤እንዲህስ ባይሆን ባልኃችሁ ነበር፤ስፍራ

         አዘጋጅላችሁ ዘንድ እሄዳለሁና፤ ሄጄም ስፍራ ባዘጋጅላችሁ እኔ ባለሁበት

         እናንተ ደግሞ እንድትሆኑ ሁለተኛ እመጣለሁ ወደ እኔም እወስዳችኃለሁ፡፡”

                                                   ዮሐንስ 14፡2-3

    ኢየሱስ በሰማይ ስላለው ሁኔታ የገለፀባቸውን መንገዶችን አጢን፡፡ በሰማይ ስላለው ስለወርቅ መንገድ፣ ስለመላእክትና ቅዱሳን ስለሚቀመጡበት ዙፋን መናገር ይችል ነበር፡፡

    ኢየሱስ በሰማይ ያለው ነገር ከማናቸውም በበለጠ ሁኔታ በሚያስረዳበት ጊዜ ሰማይ… ቤት ስመሆኑ ለደቀ መዛሙርቱ መንገር ፈልጓል፡፡

    ሐዋሪያው ጳውሎስ በምድራዊ ማንነቱ ይሁዳዊ እና ሮማዊ በመሆኑ መኩራት ቢችልም ስለ ምድራዊ ማንነቱ ሳይሆን በሰማይ ስላለው ማንነት ነው የገለፀው፡፡ (ፊልጵስዮስ 3፡20) ከጌታ ጋር በሰማይ መኖር ከፍተኛ የሆነ ፍላጎት ያለው በመሆኑ መላ ሀሳቡ፣ እሴቶቹ እና በጊዜው አጠቃቀም በዚያው የተስተካከሉ ናቸው፡፡ የጳውሎስ ምርጫም አሁንም ያሉትም በምርጫቸው ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ በመፍጠር ይቀጥላል፡፡

    ኢየሱስ እግዚአብሔር የሚሸልመው ሕይወት አስመለክቶ የተናገረውን ከሰማህና ካስተዋልክ፤ ከዘሬም ጀምሮ የዘላለም ንሮ ለመኖር ዛሬ ብትጀምር አዲስ ዜግነትህ የሆንክ ስለመሆንህ ከእኔ ጋር ይህንን እንድታውጅ አበረታታሃለሁ፡-

ጌታ ኢየሱስ ሆይ፤ ስለ እቤቴ ያልከውን ነገር ጠንቅቄ ተረድቻለሁ፡፡ አምንሃለሁ፤

ከእንተ ጋር እያለሁ እዚህ መሆን አልፈልግም፤ከሚታየውና ከሚጠፋው ከዚህ ዓለም

ጋር መወዳጀቴን ትቻለሁ፤ ከእንተ ጋር አብሮ ለመጓዝ ወስኛለሁ፤ የሰማይ ንጉስ ከሆከው

ከአንተ ጋር፡፡ ከዚህ ቀን ጀምሮ ልክ እንደ ሰማይ ዜጋ እኖራለሁ፤ እውነተኛው ቤቴ፡፡

እንደታማኝ ባለአደራ ጠባቂ በእኔ እጆች ውስጥ ያደረካቸውን ማናቸውንም ስጦታዎች፣

እድሎች አና ሀብቶቼን ለአንተ አንዲበዙ አደርጋለሁ፡፡ በአንተ ፊት ቆሜ በዘላለም

ቀን አንተን አይህ ዘንድ እጓጓለሁ፤ ሽልማትህን ስወስድ፤ለዘላለምም ሳመልክህ፡”

 

የዘላለም ቤታችን እውን ሲሆን

የዘላለም ቤትህ መጥቶ መላእክትና ቅዱሳን ለአንተ ክብርን ሲሰጡ በአንተ ህሊናህ አስብ፡፡ እንተ ስትቆም አዳኝህ ለአንተ የሚናገረውን ለመስማት ፀጥ ሲሉ “መልካም አደረክ፤ጎበዝና ታማኝ ባሪያ” ከዚያ በኃላ ሰማይ ከምስጋና የተነሳ ትደበላለቃለች፤ ልክ የማይጠፋውን አክሊል ከኢየሱስ ስትቀበል፡፡

    ይህ ለአንተ የተለየች ክስተት ነች፤ እግዚአብሔር ልባዊ ምስጋናውን ሲሰጥህ፡፡ በዚያች ቀን የኢየሱስን ሞት በልዩ ሁኔታ ትልቅ ቦታ የሰጠኸው መሆኑን ትረዳለህ፤ በምትኩም አንተም ለእርሱ ያለህን ሕይወት መስጠትህ፡፡

    እግዚአብሔር ያችን ቀን ይፈልጋል፤ያልታዩ ዘላለማዊ ነገሮች ሲገለጡ፤ ለአንተም የተለየች የህይወትህ ቀን እስከምትሆን ድረስ፡፡

    ይህ መፅሃፍ ለዚያች ቀን ተብሎ የተሰጠ ስጦታ ነች፤ከትልቅ ደስታ ጋር፡፡